2011-09-12 14:35:15

የኒውዮርክ ሊቀ ጳጳሳት፥ ፍቅርን እና መተሳሰብን ያነቃቃው አሰቃቂው የአሸባርያን ጥቃት፣ ብቀላ ፈጽሞ ጥቅም የሌለው ተግባር መሆኑ ያረጋግጥልናል።


ትላትና እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት እርሱም በኒውዮርክ በሚገኙት ሰማይ ጠቀስ መንትየ ፈቆች በዋሽንግተን በፐንታጎን ሕንፃ ብሎም በፐንስልቫኒያ አሸባሪዎች የጣሉት አሰቃቂው ያጥፍተህ ጥፋ ጥቃት ሳቢያ ለሞት የተዳረጉት ዝክረ ንፁሓን ዜጋዎች በአገሪቱ እና በተለያዩ አገሮች መከናወኑ ተገለጠ። RealAudioMP3 በዝክርረ ዕለቱ የአገሪቱ የጸጥታ እና የደህንነት ድርጅት በሰጠው የአሸባሪያን የጥቃት ሥጋት መረጃ መሠረትም የጸጥታው እና የደህንነት ቁጥጥር እጅግ ከፍ ብሎ መታየቱም ለማወቅ ተችለዋል።

ቀኑን ምክንያት በማድረግ የኒውዮርክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቲሞትይ ዶላን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የሟቾች ቤተሰቦች በኃዘን እና በጥልቅ ስቃይ ተነክተው ሲያበቁ ሆኖም ግን እርስ በእርሳቸው ሲደጋገፉ እና መጽናናትንም በመለዋወጥ ያሳዩት የትብብር መንፈስ እጅግ የሚደነቅ ነው። ብዙ የአገሪቱ ዜጋ ሌላውን ለመርዳን የሕይወት መሥዋዕት ጭምር የከፈለበት ዕለት መሆኑ አውስተው፣ በዚያኑ አሰቃቂው ግብረ ሽበራ ሳቢያ ለተለያየ ችግር ለተጋለጡት ቤተሰብ ጭምር ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ደጋፍ የማቅረቡ መርሃ ግብር የሚመሰገን መሆኑ ጠቅሰው፣ እንዲህ ዓይነቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ እና ተሰምቶ ለማይታወቀው ዓይነት ጥቃት ሊሰጠው የሚገባው የተስተካከለ ግብረ መልስ ለእግዚአብሔር ፈቃድ በመተው እርሱም ጥላቻ እና አመጽ በግብረ ሠናይ እና በፍቅር ላይ የተመሠረተ ሆኖ ሕዝብ እርስ በእርሱ በመደጋገፍ ፍቅር በመኖር ያሳየው ምሥክርነት የሚደነቅ ነው። ቤተ ክርስትያን እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር በማቅረብ በዚሁ ዘርፍ በማነጽ ሕዝቡን በመደገፍ ብቀላ ትርጉም የሌለው ጸረ ሰላም መሆኑ በማስተማር ለምህረት ይቅር ለመባባል በታደሰ መንፈስ ሰውን እና አገርን ዳግም ለማነጽ በማነቃቃት፣ በጥቃቱ ሳቢይ ለሞት አደጋ የተጋለጠውን ማሰብ ሆኖም ግን የሟቾችን ቤተሰብ ለብቻቸው እንዳይተዉ ቅርብ በመሆን ሰላም በፍቅር በይቅር መባበል እና በመቀራረብ በመደጋገፍ የሚታነጽ መሆኑ በኔውዮርክ የምተገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አስተምራለች እያስተማረችም ነው ብለዋል።

አመጽ እና አሰቃቂ አደጋ በሰው ዘር መካከል ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ እንጂ፣ ከእግዚአብሔር የሚያርቅ፣ ክብር ያለው ሰብአዊ መንፈስ ወይንም የጥላቻ መንፈስ ሊቀሰቅስ ይችላል፣ ቤተ ክርስትያን ይኸንን በመለየት በሰው ዘር ያለው መልካም ባህርይ እንዲጎላ በማነጽ፣ ሰለባ የሆኑትን በመዘከር የተጎዱትን በመደገፍ የምትገኝ ስትሆን፣ ሕዝቡ ያሳየው አቢይ ትብብር እና የከፈለው መሥዋዕት ጭምር የታሰበበተ ዕለት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.