2011-09-12 14:36:20

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፥ ሕይወትን እና ሰላምን ማገልገል


በሳምንት መገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ ትላትና እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. አሸባሪያ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የጣሉት አሰቃቂው የአጥፍተህ ጥፋ ጥቃት ማእከል በማድረግ በተጣለው የአሸባርያን ጥቃት ሳቢያ ከተለያዩ 90 አገሮች RealAudioMP3 የተወጣጡ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች ኒውዮርክ በሚገኘው የንግድ ማእከል የአሸባሪያን ጥቃት ሳቢያ በጠቅላላ ሶስት ሺሕ ሕዝብ ለሞት መዳረጉ አባ ሎምባርዲ አስታውሰው፣ በርግጥ የተጣለው የአሸባርያን ጥቃት እና ጥቃቱ ያስከተለው ቁጣ አዲሱ ሚለኒዩም የሰላም ጊዜ እንደማይሆን በተለያየ ሰው ልጅ ልብ ተስተጋብቶ፣ የጥላቻው መንፈስ ኃይሉን ከፍ የሚያደርግበት እንደሚሆን ተሠግቶ፣ ጸረ አሸባርያን ዓላማ የወለደው ጦርነት ያላበቃ ከመሆኑም ባሻገር፣ ችግሮችም እንዲፈቱ አላደረገም። የአሸባርያኑ መሪ ቢን ላደን ቢገደልም በእውነቱ ሽብርተኝነት ከእርሱ ጋር ተቀብረዋል ብሎ ለማሰብ የሚቻልም አይደለም።

እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. ሕይወት ለማዳን እና ሕይወትን በመሰዋት የሌላውን ሕይወት ከአደጋው ለማዳን የላቀ የፍቅር ትርጉም የተኖረበት ታሪክ፣ የእሳት አደጋ የመከላከያ ኃይል አባላት ሌሎች ተራ ዜጎች በተጣለው የአሸባርያን ጥቃት ለሞት አደጋ የተጋለጡን የቆሰሉትን እና ሰለባ የሆኑትን በመፈለግ ሕይወትን በመሠዋት ሕይወትን አድነዋል፣ የሰላም ጥማት ያጎላ ሁሉም ለሰላም እንዲጸልይ የባህሎች እና የተለይዩ ኃይማኖቶች መካከል ጭምር የሚደረገው ውይይት ያሳየለ እና በተለይ ደግሞ ከመበቀል ፍላጎት ሕዝቡን ነጻ ለማውጣት አቢይ ጥረት የተረጋገጠበት መሆኑ አብራርተዋል።

የአሸባሪያኑ ጥቃት፣ የቀሰቀሰው የጥላቻ መንፈስ ነው፣ ወይንም በሰው ዘር መካከል ፍቅር እንዲያይል ነው ያደረገው? የተኛው ነው ከፍ ብሎ የታየው? እየተስፋፋ የሚሄደው የትኛው ነው? የሚል ጥያቄ በርእሰ ዓንቀጹ በማስቀመጥ፣ ሰለባ የሆኑትን ከመዘከር ተግባር ሊቀሰቀስ የሚገባው ሁሉም እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ሕይወትን ለማገልገል እንጂ የሞት ባህል ለማስፋፋት እንዳልተጠሩ የሚያሳስብ ሁኔታ፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ስም ሞትን መዝራት ጸረ እግዚአብሔር መሆኑ የሚያስገነዝብ መንፈስ ያረጋገጠ መሆኑ በማብራራት ያቀረቡት ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.