2011-09-12 14:37:45

የሙዩኒክ ሊቀ ጳጳስ፥ ሰላምን ከመገንባት ተግባር አንቆጠብም


የዛሬ 25 ዓመት በፊት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በአሲዚ በተለያዩ ኃይማኖቶች መካከል መቀራረብ መተዋወቅ በመሪዎች ደረጃ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በአማኞች መካከል ጭምር እንዲኖር ያበረታታው ነቢያዊ መርሃ ግብር፣ ሁሌ በየዓመቱ ይኽ ቅዱስ ተግባር መሠረት ቅዱስ ኤጂዲያ የሚያካሂደው የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖች የባህል የፖለቲካ አካላት እና የመንግሥታት ልኡካን RealAudioMP3 ጭምር የሚሳተፉበት የተለያዩ ኃይማኖቶች የጋራ ውይይት መርሃ ግብር ከትላትና በስትያ በጀርመን ሚዩኒክ ከተማ መከፈቱ የቫቲካን ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

በዚህ አጋጣሚም የሙዩኒክ ሊቀ ጳጳስት ብፁዕ ካርዲናል ራይሃርድ ማርክስ ለተጋባእያኑ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. አሸባርያን የጣሉት ጥቃት ሳቢያ ሰለባ የሆኑትን መዘከራቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ጉባኤውን ሲያስጀምሩ ግጭት አመጽ የሰውል ልጅ ታሪክ የሚሸኝ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑ አስምረውበታል። ሆኖም ግን ይኽ ተግባር ሰላምን ለመገንባት ለመቀራረብ እና ለመወያየት ከመሻት እና ከመነሳት እንድንቦዝን ፈጽሞ አያደርገንም በማለት ሁሉም ሰላም ለመገንባት ተጠርተዋል እንዳሉ ሳባቲነሊ ያስተላለፉት ዘገባ ያመለክታል።

በዚህ የሶስት ቀን የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች የጋራ የውይይት መርሃ ግብር የፈደራላዊት ጀርመት ርእሰ ብሔር ክርስቲያን ዉልፍ የሙዩኒክ ሊቀ ጳጳስት ብፁዕ ካርዲናል ማርክስ የቅዱስ ኤጂዲዮ የካቶሊክ እንቅስቃሴ መሥራች የሥነ ታሪክ ሊቅ ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ ንግግር እንዳሰሙም ለማወቅ ሲቻል፣ እ.ኤ.አ. መሰክረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. የአሸባርያን ጥቃት ዒላማ ለሆነቸው ከተማ እና ሰለባ የሆኑትን ለመዘከር መልእክት ያስተላለፉት የኒውዮርክ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ቲሞትይ ዶላን ቅዱስ ኤጂዲዮ የካቶሊክ እንቅስቃሴ ላነቃቃው የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች የጋራው ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት ሁሉም ለመደጋገፍ እና ለመተባበር የተጠራ መሆኑ እና ማንም ከዚህ ጥሪ ውጭ ሊሆን እንደማይችል፣ ሁሉም ተስፈኛ ባህል የሕይወት የፍቅር ባህል ያነቃቃ ዘንድ መጠራቱ ገልጠው፣ ይኽ ጥሪ እንዳይዘነጋም ሁሉም ኃይማኖቶች ካለ መታከት ያንጹ ዘንድ አደራ ካሉ በኋላ ሰላም መንገሥ አለበት፣ ስቃይ እና መከራ ሰላምን ለማረጋገጥ ሰላም የመሻት እምቁ ሰብአዊ ኃይል ገቢራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውሳኔ እንዲሆን የማድረጉ ኃላፊነት የሁሉም ሃይማኖቶች እና የአማኞች ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ያስተላለፉት ዘገባ ያመለክታል።

የቅዱስ ኤጂዲዮ የካቶሊክ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓሊያዞ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ከዓለማችን ጨርሶ እየጠፋ ያለው ተስፋ ፍቅር ለማነቃቃት የሚያግዙ ክንዋኔዎች ባለፉት 10 ዓምታት ውስጥ ጎልቶ መታየቱ እና የሰው ልጅ በገዛ እራሱ ውስጥ ተዘግቶ በተገለለ ሕይወት በመኖር ይከተለው የነበረው ሌላውን ግድ አለ ማለት፣ ተዛማጅ ባህል የሰው ልጅ እና በጠቅላላ ዓለማችን ወዴት እየመራት መሆኑ ከፍተኛ ግንዛቤ ያደረበት መሆኑ አብራርተው፣ ይኽ የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች የጋራው ጉባኤ የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ነቢያዊው ተግባር በመከተል ሁሉም ለሰላም ለማነቃቃት ጥረት ከማድረግ ሳይቆጠብ፣ ተወደደም ተጠላም የሰው ልጅ በጋራ ለመኖር የተጠራ ነው። ስለዚህ በጋራ የመኖር ጥሪው ሰላም እና መቀራረብ የሚጠይቅ መሆኑ የሚያስገነዝብ ነው ካሉ በኋላ በመጨረሻም ይህ ጉባኤ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት አሸባርያን የዛሬ 10 ዓመት በፊት በጣሉት አሰቃቂው የሽበራ ጥቃት ሳቢይ ሰለባ የሆኑት ንጹሓን ዜጎች በሚዘከሩበት ዕለት በመሆኑም ለየት ያለ ጉባኤ እንዲሆን አእንዳደረገውም ገልጠው የሞት አደጋ ያጋጠማቸውን ዘክረው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.