2011-09-05 17:10:31

600ኛው የቅዱስ ቊርባን ተአምር ማስተወሻ በዓል


ብፁዕ ካርዲናል ቶምኮ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ተወካይ ሆነው በክሮአጽያ ለሚካሄደው 600ኛው የቅዱስ ቊርባን ተአምር ማስተወሻ በዓል ተሳትፈዋል፣
የክሮአጽያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትናንትና በሉድብረግ የተፈጸመ ተአምረ ቅዱስ ቊርባን 600ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ያወጁትን የአንድ ዓመት ኢዮቤል መዝግያ ሥርዓት ፈጸመች፣
ይህ ተአምር በ1411 ዓም ሥርዓተ ቅዳሴ በማሣረግ ላይ እያሉ በጽዋዕ የነበረው ወይን ወደ ደም የተለወጠበት ነው፣
ለዚህ አጋጣሚ ቅዱስነታቸው የአሕዛብ ስብከተ ወንጌል ማኅበር ኃላፊ የነበሩትን ብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ቶምኮ እርሳቸውን ወክለው የእርሳቸው ልዩ መልእከተኛ ሆነው በበዓሉ እንዲሳተፉ እንደላክዋቸው የሚታወስ ነው፣
መለስ ብለን ታሪኩን የተመለክትን እንደሆነ በ1411 በካተሎ ዘባትያንይ አንድ በቅዱስ ቊርባን እውነትኛነት የሚጠራጠር ቄስ መሥዋዕተ ቅዳሴ እያሳረጉ በጽዋዕ ውስጥ የነበረው ወይን ወደ ደም ተለወጠ፣ ወዲያውኑ ወሬው በሉድብረግ አከባቢ ተዛመተ፣ በአክባቢው የሚገኙ ምእመናን ወደ ሉድብረግ መጒረፍ ጀመሩ፣ ብዙ ሕዝብ ከበሽታ ሕመም የመዳን ተአምር አገኙ፣ በ1513 ዓም ር.ሊ.ጳ ልዮን 10ኛ ዕውቅና በመስጠት ምእመናን እንዲነግዱና የተለወጠውን ደም እንደ ቅዱስ ቅርስ ለዑደትም ይሁን ለቡራኬ እንዲጠቀሙት ፍቃድ ሰጡ፣ አንዴም በሮም ለዑደት ተወስዶ ነበር፣ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ሰሜናዊ ክሮአጽያ በወረርሽኝ ተችገረው ወደ እግዚአብሔር እሪ ሲሉ የመንግሥቱ ፓርላማ ተሰብስቦ የሕዝቡ ልመና ተሰምቶ ወረርሽኙ የቆመ እንደሆነ በሉድበርግ ለጥቀ ቅዱስ ደመ ኢየሱስ ቤተ መቅደስ እንዲሚሰሩ ስለት ገቡ፣ ወረርሽኙ አቆመ ቤተ መቅደሱም ብ1994 ተፈጸመ፣ ይህንን ለማስታወስና ለማመስገን የክሮአጽያ ቤተ ክርስትያን ከአምና መስከረም 5 ቀን ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ኢዮቤል ያወጀችው፣ በዚሁ ዓመት ብዙ ጸሎት ንግደት የተለያዩ ጥናቶች ሱባኤዎች ጥቀ ክቡር ደሙን በሚመለከት ብዙ አስተምህሮዎች በጽሑፍ በቪድዮና በድምጽ አዘጋጅተው ከተለያዩ ቊምስናዎች ገዳማትና የቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴ ቡድኖች ለመጡ ነጋድያን አቅርበዋል፣
ቅዱስነታቸው ባለፈው ሰኔ ወር ሰኔ 5 ቀን 2011 ዓም ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ይህንን ተአምር በማስታወስ ምእመናን ወደ ቅዱስ ቊርባን እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርበው ነበር፣








All the contents on this site are copyrighted ©.