2011-08-31 14:30:06

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (31.08.11)


ውድ ወንድሞችና እኅቶች። ዛሬም ደጋግሜ እንዳመለከትኩት በዚሁ የዕረፍት ግዜ እያንዳንዳችን ከሚያስቸግሩን ዕለታዊ የሕይወታችን ተግባሮች ጐን ለጐን ለእግዚአብሔር የሚሆን ግዜ ለጸሎት የሚሆን ግዜ ማግኘት እንዳለብን አሳስቤ ነበር፣ ጌታ ራሱ ስለእርሱ እንድናስታውስ ብዙ ምልክቶችና አጋጣሚዎች ያቀርብልናል፣ ዛሬ ከእነዚህ ኅልናችን ወደ እግዚአብሔር ለማሳረግ የሚጠሩን እርሱን ለማግኘትም ሊረዱን ስለሚችሉ ነገሮች ለመናገር እወዳለሁ፣ እነዚህ ምልክቶች የኪነ ጥበብ ውጤቶች ናቸው፣ በተለይ ንጹሕ መንገድ በማለት የሚታወቀው የኪነ ጥበብ የውበት መንገድ ከአሁን በፊትም ብዙ ግዜ ተናግሬ ነበር፣ የዘመናችን ሰው ጥልቅ የሆነውን የእነዚህ የኪነ ጥበብ ተግባሮች ትርጉም እንደገና ሊገነዘበው ያስፈልጋል፣
ምናልባት አጋጣሚ ሆነ በኪነ ጥበብ ውጤት የሆኑ ቅርጻ ቅርጽ ወይም ሥዕል አይታችሁ የሆነ እንደሆነ ወይንም አንድ ሥንኝ የግጥም የቅኔ ያነበባችሁ ወይንም አንድ ጥሩ ጣዕም ያለው ዜማ ሙዚቃ የሰማችሁ እንደሆነ ምን ዓይነት ጥልቅ ስሜት እንደሚፈጥር የደስታ ስሜት ሆነ በጥልቀት ለመረዳት የሚገፋፋ ስሜት ነው፣ እርግጥ በእንዲህ ያለ አጋጣሚ እፊታችሁ ተደቅኖ ያለው ቊሳዊው ሐውልት ወይም የፊደሎች ስብስብ ወይም በቀለም የተቀባ ጨርቅ ወይም የድምጾች ስብስብ አይደለም፣ እነኚህ የኪነ ጥበብ ውጤቶች የሚናገሩ ልብ መንካት የሚችሉ ስሜት የሚቀሰቅሱ ልዩ መልእክት በማስተላለፍ ነፍሳችን ከፍ የሚያሰኙ ናቸው፣ ማንኛው የኪነ ጥበብ ውጤት የሰው ልጅ ፈጠራዊ ችሎታ የሚያሳይ የሥራው ውጤት ነው፣ የሰው ልጅ በነገሮች ፊት ቆሞ ይመራመራል። ጥልቅ ምሥጢሩን ለመረዳት ይሞክራል። የተቻለውን ያህል ደግሞ በኪነ ጥበብ ቋንቋ ማለትም በቅርጻ ቅርጽ በሥዕል በዜማ ወዘተ። መልእክቱን ለሌሎች ሊያስተላልፍ ይጥራል፣ ኪነ ጥበብ የሰው ልጅ በእጅ ከሚዳሰሰውና በዓይን ከሚታየው ባሻገር ላለው የዕውቀት ጥማትና መጨረሻ የሌለውን የመፈለግ ሁኔታ የመግለጥ ችሎታ አለው፣ እንዲያው ኪነ ጥበብ ከዕለታዊ ገጠመኝ ወዲያ በመሻገር ለውበትና ለእውነት አለገደብ የተከፈተ በር ነው ለማለት እንችላለን፣ አንድ የኪነ ጥበብ ተግባር የኅልናችንና ልባችን ዓይነት ከፍ ወዳለ ነገር ሊከፍታቸው ይችላል፣
ከእነዚህ ሥራዎች ወደ እግዚአብሔር ሊያደርሱ የሚችሉ እውነተኛ ጐዳናዎች አሉ፣ ለምሳሌ ያህል የላቀው ውበት(በጎነት መልካም) በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግኑኝነት እንዲያድግ ይረዳዋል፣ እንደ ምሳሌ አንድ እጅግ ቆንጆ የሆነ ካተድራል ስንጎበኝ ወደ ላይ መጥቀው የሚወጡ የሕንጻው መስመሮችን አሻቅበን ወደ ላይ ስንመለከት ልባችንና ኅልናችንም ወደ ሰማይ ይመጥቃል። ልክ ይህን ስናደንቅ ምንኛ ያህል ትናንሽ መሆናችን ይሰማናል ወይም ሙላት የምንፈልግ ሆኖ ይሰማናል። ወይንም ጸጥታ በሰፈነበት ገዳም በሚገኘው ቤተ ክርስትያን የገባን እንደሆነ ለአስተንትኖና ለጸሎት እንጓጓለን፣ በእነዚህ አስደናቂ ሕንጻዎች ከትውልድ ለትውልድ ሲተላለፍ የነበረው እምነት እንደታቀበ እንመለከታለን፣ ወይንም የልባችን አውታሮች የሚቀሰቅስ መንፈሳዊ ዜማ የሰማን እንደሆነ መንፈሳችን ወደ እግዚአብሔር ለመብረር ከፍ ይላል፣ ትዝ ይለኛል በሞናኮ ዲ ባቭየራ የሰባስትያን ባኽ የዜማ ቅኝት በጥልቅ በሰማሁበት ወቅት በአእምሮየ ሳይሆን በልቤ ነው የሰማሁት። የሰማሁትም እውነት ነበር። ይህ እውነት ወደ ከፍተኛው የእውነት ደራሲ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር እንዳስብና እርሱን እንዳመስግን ገፋፋኝ። አጠገቤ ሆኖ አብሮኝ ዜማው ይሰማ የነበረውን የሞናኮ የሉተራውያን አቡን “ይህንን ሲሰሙ እምነት እውነተኛ መሆንዋ ይታወቃል የእርስዋ ብርታትና የዜማው ጣዕብ የእግዚአብሔር እውነትን ይገልጣል አልኩት፣” እርሱም ተስማማበት፣ ይሁንና ስንቱን ግዜ የኪነ ጥበባዊ የእምነት ፍሬ የሆኑት ሥዕሎች በቅርጻቸው በቀለማቸው በብርሃናቸው ሃሳቦቻችን ወደ እግዚአብሔር ያላሳረጉት ስንቱን ግዜስ በውስጣችን ያለውን በጥበብ ምንጭ በሆነው እግዚአብሔር እንድንጠጋ ፍላጎት ያላነሳሱ። ማርክ ሻጋል የተባለው ትልቁ ኪነ ጥበባዊ “ሰአሊዎች ብዕራቸውን ቀለማዊ በሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ፊደል ለዘመናት አጥልቀዋል፣ ስለዚህ የኪነ ጥበባውያን መግለጫዎች እግዚአብሔርን ለማስታወስ የሚያገልግሉ አጋጣሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ፣ ጸሎታቸን ለመርዳት እንዲሁም የልባችን መለወጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ” ያለው እውነት ነው፣ ፓውል ክላውደል የሚባል ትልቁ ፈረንሳዊ ባለ ቅኔ ደራሲና ዲፕሎማት በ1886 ዓም በኖትረ ዳም ባዚሊካ በፓሪስ ከተማ የልደት ቅዳሴ እየሰማ ሳለ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጸሎት ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር በላቲን ሲዘመር በሰማ ግዜ እዚህ እግዚአብሔር በእርግጥ አለ ብሎ ነበር፣ በቫዚሊካው ወይም ቤተ ክርትያኑ የተገኘው በእምነት ምክንያት ማለት አማኝ ሆኖ አይደለም። ክርስትያንን የሚከስበት ምክንያት ያገኘ እንደሆነ ነገር ፍለጋ ነው ሄዶ የነበረው፣ ሆኖም ግን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ጌታ በልቡ ሰራ፣
ውዶቼ። ይህንን መንገድ የምናደርገው ከእግዚአብሔር ጋር ሕያው ግኑኝነት ለሆነው ለጸሎትም ስለሚያገለግል አስፈላጊነቱን እንድትገነዘቡ አሳስባችኋለሁ፣ የመላው ዓለም ከተሞችና አገሮች እምነት የሚገልጡና ከእግዚአብሔር ጋር ግኑኝነት እንድናደርግ የሚጠሩን የኪነ ጥበብ መዝገብ ይገኝባቸዋል፣ በኪነ ጥበብ መዝገቦች የምናደርገው ጉብኝት የባህል ዕውቀታችን ብቻ ለማበልጸግ ሳይሆን። ከውጫዊና ቊሳዊ ነገር ጥልቅ የሆነውን መንፈሳዊ ነገር ልክ እንደ ብርሃን ነጸብራቅ ልባችንና መንፈሳችንን ቀስቅሶ ወደ እግዚአብሔር ከፍ ለማለት የሚያስችል። የጸጋ ግዜም ሊሆን እንደሚችል በመረዳት ከእግዚአብሔር ጋር ላለን ትስስራችን ኃይል በመስጠት ከእርሱ ጋር እንድንወያይና ለአስተንትኖ እንድንቆም ይሁን፣
የዛሬ ትምህርትየን በመዝሙረ ዳዊት ጸሎት ለመዝጋት መዝ 27 የተመለከትን እንደሆነ “አንድ ነገር ብቻ እንዲሰጠኝ እግዚአብሔርን ለመንሁት። የምፈልገውም አንድ ነገር ብቻ ነው። ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እንድኖር፣ በዚያም ሆኜ የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደንቅ፣ አመራሩንም እንድጠይቅ ነው” ይላል፣ ጌታ ውበኡንና በጎነቱን በተፈጥሮ እንዲሁም በኪነ ጥበብ ሥራዎች ለማሰላሰል ይርዳን፣
በዚሁ የብርሃን ገጽታ ተነክተን ለጓደኞችን ብርሃን ለመሆን ያብቃን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.