2011-08-23 11:37:44

የቅድስት መንበር ቃል አቅባይ አባ ፈድሪኮ ሎምባርዲ ቃል


የቅድስት መንበር ቃል አቅባይ አባ ፈድሪኮ ሎምባርዲ ማድሪድ የታካሄደው ዕለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን በየወጣቶች ብዛት ብቻ ሳይሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ያስተላለፉት ግልጽ የሆነ መልእክት እና መንፈሳዊ ይዘታው አለፌታ መኖሩ ገልጸዋል፣
መልእክቱ ወጣቶቹ የሕይወታቸው መሠረታዊ እምነት እንድያፈላልጉ የክርስትና ምስክሮች እናዲሆኑ በቅድስነታቸው የተላለፈውን መልእክት መረዳታቸው ጠቅሰው ማራኪ እና መንፈሳዊ የወጣቶች ቀናት ለማስተዋል መቻሉም አክለው አመልክተዋል፣
በኩአትሮ ቪየንቶስ የተካሄደው የሥርዓተ አምልኮ ለሊት ፍጹም ግሩም መንፈሳዊ እና የክርስትና ምስክርነት ያሳየ የወጣቶች መንፈሳውነት አዲስ የእምነት መንፈስ ቀስቃሽ መኖሩ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ መግለጫ ሰጥተዋል፣
ወጣቶቹ፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የተመረተ ሕይወት ፡ የህልውና እና የመኖር ትርጉም እንደሚሰጥ በነዲክቶስ 16ኛ ያስተላለፉት መልእክት በሚገባ ተረድተው ገቢራዊ እንደሚያደርጉት ያላቸው ተስፋ ከፍተኛ መሆኑም ቃል ኣቀባዩ አመልክተዋል፣
በሩስያ ሞስኮ ላይ በሚገኘው የወላዲተ አምላክ ካቶሊካዊ ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፓኦሎ ፐጺ በዚሁ ማድሪድ ላይ የተካሄደው ዕለም አቀፍ የወጣቶች ዕለት ይተሳተፉ ሲሆን፡ ሁለት ሚልዮን ወጣቶች እንደ ኣአጋጣሚ የተገናኙ ሳይሆን የእነታቸው ጽናት መንፈሳውነታቸው በክርስቶስ ተጠርጠው የተሰበሰቡ ናቸው የሚል ጥልቅ አስተሳሰብ መቅሰማቸው ፍጹም መልካም መኖሩ ገልጠዋል፣
ሁለት ሺ የሩስያ ካቶሊካውያን ወጣቶች በዚሁ የማድሪድ የወጣቶች ቀን ተሳታፊ መሆናቸው የሚታወስ ነው፣ ከኢትዮጵያም 30 የሚሆኑ ወጣቶች ተሳትጋፊ መሆናቸው ተመልክተዋል፣
በዚሁ ማድሪድ ላይ የተካሄደው እና ትናትና የተጠናቀቀው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ካርዲናሎች ሊቀ ጳጳሳት ጳጳሳት ካህናት እና ደንግሎች ተሳታፊ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፡ በፖላንድ የኩራኾቭያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሳንሳላው ዲቪጽ በአውስትራያ የቪይን ሊቀ ጳጳስ ብጹኦ ካርዲናል ክሪስቶፍ ሾንቦርን እንደገለጡት፡ በማድሪድ የታየው ጥዕንተ ወጣቶች እና ይዘታው፡ የአዲስ ስብከተ ቅዱስ ወንጌል ጅማሬ ነው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.