2011-08-23 11:33:06

የ26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ፍጻሜ


በእስፓኛ ማድሪድ ላይ ለአንድ ሳምንት የተካሄድው 26ተኛ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ዕለት በትናትና ዕለት ተፈጽመዋል፣ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ዕለት ከ26 ዓመታት በፊት በብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መጀመሩ የሚታወስ ነው፣
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ የዚሁ ዕለት ተሳታፊ መሆናቸው የሚታወስ ነው፣ በነዲክቶስ የዓለም አቀፍ የወጣቶች ዕለት ተሳትፊ ሲሆኑ የማድሪዱ ሶስተኛ መሆኑ ይታወቃል፣ ትናትና ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በብዙ ካርዲናላት ሊቀ ጳጳሳት ፓጳሳት እና ካህናት ተሸንተው ማድሪድ በኩአትሮ ቪየንቶስ ትልቅ ሜዳ ዓለም ኣአቀፍ ዕለተ ወጣቶች ትኩረት የሰጠ ሥርዓተ ቅዳሴ መርተዋል፣ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ሁለት ሚልዮን ወጣቶች ተሳታፊ ሁነዋል፣ የእስፓኛ ንጉስ ኹወን ካርሎስ እና ባልት ቤታቸው ሶፊያ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ መሳተፋቸው ይታወቃል፣
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፡ ወጣቶቹን ወደ መላ ሄዳችሁ ቃለ ሰናየ ቅዱስ ወንጌል አብስሩ፣ ቅድስነታቸው በማያያዝ እነሆ ዛሬ ዕለም አቀፍ ዕለተ ወጥቶች ፍጻሜ ደርሰናል ከመላ ዓለም የተውጣጡ በሚልዮን የሚቀጠሩ ወጣቶች ሲመለከት ጥልቅ ደስታ ይሰማኛል፣ ለዚሁ ዕለት የተነበብውን ወንጌል ማርቆስ እንደሰማነው መድኅን ዓለም ክርስቶስን ለማወቅ የተለያዩ መንገዶች አሉ እሱን አረጋግጠን ለማወቅ ወደ ሱ ጋር መቅረብ እንደ ሚያስፈልግ እንረዳለን፣
እምነተ ሃይማኖት የአግዚአብሔር ስጦታ መሆኑ ጠቅሰው እምነተ ሃይማኖታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት በከፊል ሳይሆን በጥልቅ ያስረዳናል ይህ የሚሆነው ግን ሃይማኖታችን ገቢራዊ ስናደርገው መሆኑ ቅድስነታቸው ገልጸዋል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያቱን እስቲ እኔ ማን ይመሰላችሁል፡ ማን ነው ብላችሁ ታስባላችሁ ብሎ የጠየቃቸው ከሱ ያላቸውን ግኙነት ለመረዳት እንደሆነ ጠቅሰው። ቅዱስ ጰጥሮስ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነህ ብሎ ምላሽ መስጠቱን በማያያዝ አስገንዝበዋል፣
እምነተ ሃይማኖት እና ኢየሱስ ክርስቶስ የተሳሰሩ ናቸው እና እምነት ጸንቶ ማደግ መበርታት ያለበት ሆኖ ከክርስቶስ ያለው ትስስር ጸንቶ የሱ ምስክሮች መሆን ይጠበቅብናል ቅዱሳን ጰጥሮስ እና ጳውሎስ ክርስቶስ ሞት እና ሐጢአት አሸንፎ ከተገለጠላቸው በኃላ ዓይኖቻቸው ለሙሉ እምነት እና ብርሃን ክፍት መሆናቸው ቅዱስ አባታችን በነዲክቶስ አስታውሰዋል፣
የተወዳዳችሁ ወጣቶች እነሆ ዘሬም ክርስቶስ በተመሳሳይ መልኩ እየጠየቀ ነው ማን ነኝ ብላችሁ ታስባላችሁ ፡ የህያው እግዚአብሔር ልጅ መሆንህን እናውቃለን ብለን ምላሽ ለመስጠት ብቁ መሆን ይጠበቅብናል ብለውል ቅድስነታቸው፣
ክርስቶስ እናን ለማዳን ሕይወቱ አስላፎ የሰጠ ነ እና በእምነት እንከተለው እንመስክርለት ያሉት በነዲክቶስ 16ኛ ሕይወታችን ባንተ ላይ አኑረናል እንበለው
እሱ ኀይላችን ነው እና በማለት በስብከታቸው ላይ ገልጠዋል፣
ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አንድ ተቋም ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር የተሳሰረች ቤተ እግዝአብሔር መሆንዋ የክርስቶስ ቃለ ሰና ቅዱስ ወንጌል ለማሰማት ራሱ ክርስቶስ የመሰረታት መሆንዋም አስታውሰዋል፣
በክርስቶስ ብሎም በሐዋርያት የተላለፈው እምነታችን የሕወታችን ማእከል መሆንዋ መዘንጋት አይገባንም ምድራዊ ሕይወት ሐላፊ መሆኑ ተገንዝበን ዘለዓለማዊ ሕይወት ለመቀዳጅት ዝግጁ መሆን አለብን ያሉት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሁለት ሚልዮን ለሚሆኑ የዓለም ወታቶች እና ምእመናን ለሁላችሁም በዕለታዊ ጸሎቴ አስታውሳችሁለሁኝ ብለዋል፣
ቅድስት ማርያም ወላዲተ አምላክ የክርስቶስ ቃል የታመናችሁ እንድትሆኑ ታግዛችሁለች እየሱስ ክርስቶስ መድኅን ዓለም የሕይወት የተስፋ የሰላም የብርሃን ምንጭ መሆኑም አስገንዝበዋል፣
በዚሁ ማድሪድ ላይ በሚገኘው የድሮ አውሮፕላን ማረፍያ ኩአትሮ ቪየንቶስ በተካሄደው ሥርዓተ ቅድሴ ዕለም አቀፍ ወጣቶች በጣልያንኛ በቻይና በዓረብ በየፖላንድ እና ጀርመን ቋንቋዎች ጸሎተ ምአመንና ተካሄደዋል፣
ሥርዓተ ቅዳሴው እንደተፈጸመ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እዚያው ከተገኙ ሁለት ሚልዮን ምአናን ጋር አብረው የዕለተ ሰነብት መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል፣
ቀጣዩ ዕለም አቀፍ የወጣቶች ዕለት እኤአ 2013 በብራዚል ሪዮዲጃነሮ እንደሚከናወንም ይፋዊ መግለጫ እና ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ከምአመናን ጋር ተሰናብተዋል፣
ከዚያ ወደ ሚቆዩበት ቤተ ጵጵስና ሐዋርያዊ ወኪል ተመልሰው ከስፓኛ ካርዲናሎች እና ከሸንዋቸው ለምሳ ተቀምጠዋል፣
ከቀትር በኃላ ወደ ግዙፍ አዲስ የማድሪድ የትርኢት ቦታ ተጉዘው በጋዛ ፈቃዳቸው በዚሁ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ዕለት በስራ ተሰማርተው ከነበሩ 12 ሺ ሰዎች ተገናኝተዋል፣
ባለ በጎ ፈቃዶቹ ለሰሩት መልካም ስራ አወድሰው አመስግነው ሐዋያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋቸውል፣
ባማድሪድ ሰዓት አቆጣጠር 18 ሰዓት ተኩል ወደ ባራያስ ማድሪድ ዕለም ኣአቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ተጉዘው እዚያው ይጠባበቅዋቸው ከነበሩ የቤተ ክርስትያን የመንግስት ባለ ስልጣናት ጋር ተሰናብተው አምሻቸው 21 ሰዓት ተኩል በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው በሰላም ተመልሰዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.