2011-08-19 17:26:46

መካነ ጥበብ ወይም ዪኒቨርሲቲ እውነትን የምንሻበትና ከገዛ ራሳችን ጀምሮ ስለሁሉ የሚመለከት የእውነት ምንጭ መሆን አለባቸው፣


ቅዱስነታቸው ከወጣት መንኲስያት ከተገናኙ በኋላ በገዳሙ አጠገብ ከሚገኙ የቅዱስ ሎረንዞ ዲ ኤል ኤስኮርያል ባዚሊካ ከወጣት የመካነ ጥበብ ወይንም ዪኒቨርሲቲ አስተማሪዎች ጋር በተገናኙበት ወቅት በሙዚቃ የተሰኘ ታላቅ አቀባበል ተደረገላቸው፣ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒኦ ማርያ ሮውኮ ቫረላ መግብያ ካደረጉ በኋላ ከዪኒቨርሲቲው ወጣት አስተማሪዎች የእንኳን ደህና መጡ ንግግር በአንድ ወጣት አስተማሪ ቀርቦ እንደገና የሙዚቃ ትዕይንት ለክብራቸው ቀርበዋል፣
ቅዱስነታቸው ባደረጉት ንግግር ሁሉንም አመስግነዋል፣
ከጠቅላላው የእስፐይን ወጣት ፕሮፈሰሮች ለመገናኘት በትልቅ ጉጉት እጠባበቀው ነበር፣ ልባዊ ሰላምታየን በማቅረብ አመሰግናችኅዋለሁ፣ በዚሁ ትእምርታዊ ቦታ የሆነው ዛሬ አእምሮና እምነት ተወሃህደዋል፣ ሁላችሁንም ሰላምታየን አቅርባለሁ፣ በተለይ ደግሞ ባለፉት ቀናት የካቶሊካውያን ዪኒቨርስቲዎች ማንነትና ተልእኮ በሚለው ርእስ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት ለተሳተፋችሁ አመሰግናለሁ፣
ዛሬ እዚህ ከእናንተ ጋር በምገኝበት ወቅት ገና ወጣት ሳለሁ በቦን ፕሮፈሰር ሆኜ ያሳለፍክዋቸው ግዝያት ትዝ ይሉኛል፣ ያኔ ገና የዓለም ጦርነት ቊስሎች አልዳኑም ነበር፣ ያኔ ከነበረው ቁሳዊ ችግር ባሻገር የተለያዩ ክፍሎች አስተማሪዎችና ተማሪዎች አብረን ያደረግነው ነገር ቢኖር አልፎንሶ 10ኛ እንዳለው “አስተማሪዎችና ተማሪዎች በብርቱ ፍላጎትና ቅኑ ዓላማ ጥበብን ለመረዳት ይደረጉ የነበሩ ግኑኝነቶች” ነበሩ፣
የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አርማ “በክርስቶስ ሥር ሰዳችሁና ተመሥርታችሁ በእምነት ጽኑ” የሚለው ሲሆን በዚሁ የእናንተው ማንነትና የእናንተው ተልእኮ በበለጠ ለመረዳት ትችላላችሁ።። እነኚህ ቃላት በመልእክቴ እንዳልኩት ለሕይወት የሚሆኑ ጽኑ መሠረቶች የሚገኙበትን መንገድ ያሳያሉ፣
ዛሬ ወጣቶች ብዙ ችግር ይገጥምዋቸውል፣ በተለይ የዘመንችን ዩኒቨርሲቲዎች የዓለም ገበያ የሚጠይቃቸውን ዓይነት ተማሪዎች ለማሰልጠን ሲርዋርዋጡ ማየት ያሳዝናል፣ ያም ሆኖ ይህ እናንተ በዪኒቨርሲቲ የኖራችሁ ጌናም እዛ በመሆን የምታስተምሩና የምታሰለጥኑ ሁሉንም ወደ ሰው ልጅ እንዲያተኩር በማድረግ ከፍ ያለ የሰው ልጅ መቋቋም ማእከል ብታደርጉ ይሻላል፣ ለጥቅም ብቻ የሚደረገው ምርምርና ጥናት ከቁጥጥር ውጭ በመሆን አደገኛ ነገር ሊያስከትል ይችላል፣እንዲሁም በፖሎቲካና በልዩ ልዩ ርእዮተ ዓለም የተመረዙ ሥነ ሀሳቦች የሚያስከትክዋቸው ችግሮችም ብሩህ ናቸው፣ ዪኒቨርሲቲዎች ግን የሰው ልጅ ከእንዲህ ዓይነት አድጋዎች ለመዳን መጣር አለባቸው፣
ቤተ ክርስትያንም ይህን ስለተረዳች ነው በእግዚአብሔር አምሳልና መልክ ለተፈጥረው የሰው ልጅ ስለ ሥጋ የሆነው ቃልና ዓለም ሁሉ በእርሱ የተፈጠረው ክርስቶስ ለማሳወቅና የክርስትናን እምነት ለማስተማር ዪኒቨርሲቲዎች የምታቋቊመው፣ የዚሁ መልካም ዜና ትርፍ ለተፈጥሮ አመክንዮ በመስጠት ሁሉን ነገር ለመረዳትና ምክንያት እንዳለውና ትርጉም እንደሚሰጥ ለመረዳት ይረዳል፣
ስለዚህ የዪኒቨርሲቲዎች ጥቅም አለምንም የርእዮተ ዓለም ጭፍን አስተያየት ወይንም ጥቅም የመፈለግ የገበያ ትርፍ ከሚመለከት አስተሳሰብ ነጻ በሆነ መንገድ በክፍት አእምሮ እውነትን መሻት ነው፣
የዪኒቨርሲቲ ወጣት አስተማሪዎች ተልእኮ እምነትን በሰዎች አእምሮ ፊት አነጥሮ ማሳየት፣ ማስተማር ብቻ ሳይሆን ደግሞ በተግባር ሊኖሩት ያስፈልጋል፣፣ ሲሉ የዛሬ ወጣቶች እውነተኛ አስተማሪዎች ማለትም የሚያስተምሩትን በተግባር የሚያሳዪና የሕይወት አርአያ የሆነ አስተማሪዎች እንደሚያስፈልጉ ይህም ከእነዚህ ወጣት አስተማሪዎች ካልተገኘ ከሌላ ማንም ሊገኝ ስለማይችል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አደራ ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን በመቀጠል ዪኒቨርሲቲዎች እውነትን ለማግኘት አሰሳና ጥናት የሚካሄድባቸው ነፃ የአእምሮ ሥራ የሚያድግባቸው ቦታዎች መሆን እንዳለባቸውና ይህንንም በፍቅር ሲደረግ አመርቂ ውጤት እንዳለው ገልጠዋል፣፣ እውነት ሁሉን ልናውቅ አንችልም፣ በእውነት እውነትን የሚሻ ሰው በስተመጨርሻ እውነት ራስዋ ትውጠዋለች፣ የእርስዋ ወገን ታደርገዋለች፣ እውነት ራሱ ክርስቶስ ስለሆነ ደግሞ እርሱን መከተል ያስፈልጋል፣ በሌላ አነጋገር በወጌለ ዮሐንስ እውነት ሕይወትና መንገድ እኔ ነኝ እንዳለው እውነትን በንፁሕ ልብ የፈለግነው እንደሆነ በስተመጨረሻ በእርሱ ስጠመን ከእርሱ ጋር አንድ እንሆናለን፣
ቅዱስነታቸው በንግግራቸው መደምደምያ ላይ ለሁሉም አስተማሪ በተለይ ደግሞ ለወጣት አስተማሪዎች አደራ ያሉት እውነተኛ አስተማሪ ትሕትና የተላበሰ መሆን አለበት፣ ትሕትና የተላበሰ አስተማሪ እንደ አለ ምንም ድምጽ የሚያበራ ሸማ እርሱም አለምንም ትዕቢት ስሕተትና ማሳሳት ወንጌል እንዳለው የዓለም ብርሃን ይሆናል፣፣ በማለት ንግግራቸውን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.