2011-08-18 10:32:20

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በ26ኛ ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በማድሪድ በሚካሄደው 26ኛ ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ ዛሬ ሐሙስ ጥዋት በሮም ሰዓት አቆጣጠር 9፣30 ከቻምፒኖ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ሮም እንደሚነሡና እኩለ ቀን ላይ ባራኻስ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ማድሪድ እንደሚደርሱ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል፣
ቅዱስነታችው ከሐዋርያዊ አደራሽ ካስተል ጋንደልፎ ተነሥተው በቻሚፒኖ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ወደ ማድሪድ ሴሄዱ የአከባቢው ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሰመራሮ የሚገኙባቸው ብዙ ባለሥልጣናት አሸኛኘት ያደጉላቸዋል፣
በማድሪድ እንደደረሱም በአየር ማረፍያው የእስፐይን ንጉሣውያን ቤተ ሰብ የሃይማኖት መሪዎችና የመንግሥት ባለሥልጣናት ታላቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸውና የተለያዩ ዲስኩሮች እንደሚቀርቡም ተመልክተዋል፣
ቅዱስነታቸው ከአየር ማረፍያ ተንሥተው አብሮአቸው ከሚጓዙ በማድሪድ በሚገኘው ሐዋርያዊ ኑንዝዮ (ልኡክ) ምሳ ይበላሉ፣
ማምሻውን በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር 19 ሰዓት ወደ ኢንዲፐንደሳ አደባባይ በመሄድ ከከተማው ከንቲባ የእንኳን ደህና መጡ ንግግርና ስጦታ ይቀርብላቸዋል፣ የረያል ኤስክወላ ደ ካባለርያ ፈረሰኞች ሰልፍና የተለያዩ ትእይንቶች ከተደረጉ በኋላ ከፈረሰኞቹ ስጦታ ይቀርብላቸዋል፣ ወደ ከተማው የመግባት ምልክት በሆነው በፑወርታ ደ አልካላ በር አልፈው ወጣቶቹ በጉጉት በሚጠባበቅዋቸው ወድ ሲበለስ አደባባይ ሲደርሱ ወጣቶች አቀባበል እንደሚያደርጉላቸውና ደማቅ በዓል እንደሚደረግ ቅዱስነታቸውም ሰፊ አስተምህሮ እንደሚያቀርቡ ተመልክተዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.