2011-08-12 11:31:09

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለሚሳተፉ የሙሉ ሥሬ ኃጢአት ሰጡ


ከነሐሴ 16 እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓም በማድሪድ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች በነጋድያን መንፈስ ለሚሳተፉ ሁሉ የሚያደርጉት ንግደት ጸሎትና ምግባረ ሠናይ ሙሉ ሥሬት ኃጢአት እንደሚያስገኛቸው ቅዱስነታቸው እንደፈቀዱ ሐዋርያዊ የምሥጢረ ንስሐ ጽህፈት ቤት ትናንትና ባወጣው አዋጅ አሳወቀ፣
አዋጁ አያይዞም በየቦታው የሚገኙ ምእመናን ለዚሁ የወጣቶች ጉባኤ መንፈሳዊ ጽኑ ፍቃዶች የሚጸልዩም ከፊላዊ ሥሬተ ኃጢአት እንደሚያገኙ ገልጠዋል፣
በላተራነንሰ ጳጳዊ መካነ ጥበብ የክሪስቶሎጂ አስተማሪ ለሆኑት ለአባ ማሲሞ ሶረቲ ስለ ሥሬተ ኃጢአት ሊያብራሩ የቫቲካን ጋዜጣ ጠይቆአቸው ይህንን ማብራርያ አቅርበዋ፣ የሥሬተ ኃጢአት አሳብ የመታደስ የመንጻት ጉዞ ነው። ስለሆነም የቅድስና ጉዞ ልንለው እንችላለን፣ ለዚህም ወጣቶቹ በዚህ የመታደ ጉዞ ወደ ማድሪድ የሚያደርጉት ንግደት ሰብአዊና ክርስትያናዊ ኑሮአቸው እንዲያስተካክሉና ከጌታ ጋር ዕርቀ ሰላም በማድረግ በጓደኝነት እንዲኖሩ ይጠራሉ፣ በዚህ ዓለም እያለን ጌታን የሚጻረርና ከእርሱ የሚያርቀን አንድ ነገር ብቻ ነው፣ ይኸውም ኃጢአት ነው፣ ከጌታ ጋር ለመታረቅ ከኃጢኣት መራቅ ከኃጢአት ያለንን ግኑኝነት መቊረጥ ያስፈልጋል።። ኃጢኣት ትንሽም ይሁን ትልቅ ከጌታ ስለሚያርቀን ሁሉን ማስወገድ አለብን፣
ጌታ በወንጌሉ “ልብ ንጹሐን ብፁዓን ናቸው። ጌታን ያዩታልና” ይለናል፣ ይህ የንጽሕናና የቅድስና ጉዞ ከእርሱ ጋር እንድንስማማ እንድንወሃሃድ አንድ እንድንሆን የምናካሄደው ጉዞ ነው፣ ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን እውን ማድረግ ካለባቸው ዓለማዎች ዋነኛውና አንደኛው ይህ ነው፣ ግኑኝነቱ እውነተኛ ኃያልና ሙሉ መሆን አለበት፣ በዚህም መሠረታዊ የሕይወት ለውጥ በማድረግ በመንፈስ ለመታደስ ነው፣
ሥሬተ ኃጢአት የምሕረት ምልክት ሆኖ ለዚህ የሕይወት ለውጥ ልባችንን የሚከፍት ነው፣ በዚህም የሕይወታችን ለውጥ ሙሉ አጠቃላይ እና ፍጹም ሊሆን ይችላል። ሲሉ አብራርተዋል።።








All the contents on this site are copyrighted ©.