2011-08-10 15:42:15

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (10.08.11)


ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ። በተለያዩ ዘመናት ይኖሩ የነበሩ የእግዚአብሔር ሰዎች ማለትም መላ ሕይወታቸውን በጸሎት ለመኖር ለእግዚአብሔር የሰው መነኮሳንና መንኮሳት ገዳሞቻቸውን ልዩ በሆኑ ቦታዎች ። በገጠር በሚገኙ ኮረብታዎች በተራሮች ጫፍ በባህር ወይም ሐይቅ አከባቢ በደሴቶች ቈርቊረዋል፣ እነኚህ ቦታዎች በገዳማዊና ሰቂለ ኅልናዊ ሕይወት ሁለት ነገሮች ያጣምዳሉ፣ በአንድ በኩል ወደ ፈጣሪ የሚያመነጥቅ የፍጥረት መልካምነት በሌላ በኩል ደግሞ ከትላልቅ ከተሞችና ከተለያዩ የመገናኛ አውታሮች በመራቅ ጸጥታ የሰፈነበት ሁኔታ ይፈጥራሉ፣ ጸጥታ እግዚአብሔርን ለማዳመጥ ለማስተንተንና ለመረዳት ይጠቅማል፣ ጸጥታን ማሰላሰል ማለትም ሐሳብን ከሁሉ ነጻ አድርጎ ጸጥ ማለት ራሱ ለጸሎት ዝግጁነትን ያመለክታል፣ ትልቁ ነቢይ ኤልያስ በሆሬብ ተራራ ማለትም በደብረ ሲና አውሎ ነፋስ ርእደ መሬት እንዲሁም እሳተ ጎመራ አከባቢውን ሲያናውጥ ይመለከታል ሆኖም ግን በእነዚህ ፍጻሜዎች የእግዚአብሔር ድምጽ ሊያገኝ አልቻለም፣ በመጨረሻ ግን ለስለስ ያለ ድምጽ በሰማ ግዜ እግዚአብሔር በጸጥታ ሲናገር አስተዋለና እርሱን በጸጥታ ለማዳመጥ ፊቱን ከደነ፣ (1 ነገ 19።11-13) እግዚአብሔር በጸጥታ ይናገራል፣ ሆኖም ግን እንዴት ልንሰማው እንደምንችል ማወቅ ያስፈልጋል፣ ስለዚህ ገዳማት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሲናገር ሳለ የምንሰማበት ደሴቶች ናቸው፣ በእነዚህ ቦታዎች ክላውዙራ ወይም ዝግ ቦታዎች እናገኛለን፣ እነዚህ ዝግ ቦታዎች ለሰማይ ክፍት የሆኑ ምልክቶች ናቸው፣
ውዶቼ ነገር የቅድስት ክያራ ዘአሲዚ በዓል እናከብራለን፣ ለዚህም እላይ ከጠቅስናቸው የመንፈስ ደሴቶች አንዱን ለማስታወስ እወዳለሁ፣ ይህ የመንፈስ ደሴት ወይንም ገዳም ከቅዱስ ፍራንቸስኮስ ገዳማት አንዱ የሆነ የቅዱስ ዳምያኖ ትንሽ ገዳም ነው፣ ገዳሙ ለፍራንቸስካውያን ብቻ ሳይሆን የሁሉ ክርስትያኖች ዕሴት ነው፣ ገዳሙ ከአሲዚ በታች የሚገኝ በወይራ በተሸፈነው ወደ የመላእክት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን በሚወስደው መንገድ ይገኛል፣ ይህች ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ፍራንቸስኮ ከተለወጠ በኋላ ያሳደሳት ቤተ ክርስትያን ናት፣ በዚች ቤተ ክርስትያን ቅድስት ክያራና የእርስዋ የመጀመርያ ጓደኞችዋ ገዳማቸውን መስርተዋል፣ ትናንሽ ሥራዎች እየሠሩ በጸሎት ተጠምደው ይኖሩ ነበር፣ “ድሆች ደናግል” ተብለው ይጠሩ ነበር፣ የገዳማቸው ደንብም እንደ ንኡሳን አኃው ካፑቺኒ ነበር፣ የደንባቸው የመጀመርያ አንቀጽም “የእርስ በእርስ መፍቀር አንድነትን በመጠበቅ በተለይ ደግሞ ጌታ ኢየሱስና እናቱ ድንግል ማርያም በሕይወት የኖሩዋቸውን የድህነትና የትሕትና ሕይወት በማዘውተር የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌልን መከተል። ” የሚል ነበር፣
የገዳሙ ማኅበር የሚኖሩበት ቦታ ጸጥታና ቊንጅና ግዳሙ ሊቀዳጀው የሚፈልገውን መንፈሳዊ ውኅደትን ያንጸባርቃል፣ እነኚህ መንፈሳውያን ደሴቶች ወይንም ገዳማት በዓለማችን ላይ እንደ ከዋክብት ያሸብርቃሉ፣ በኤውሮጳ ብዙ ጥንታውያንና ዘመናውያን ገዳማት ይገኛሉ፣ አንዳንዶቹም በአዳዲስ ገዳማውያን እንደገና ታድሰዋል፣ በመንፈሳዊ አመልካከት እነኚህ ቦታዎች ለዓለማችን ከሚያስፈልጉ ነገሮች ዋነኞች ናቸው፣ ብዙ ሰዎች በተለይ ደግሞ በዕረፍት ግዜ እነዚህ ገዳማትን በመጐበኘት ለጥቂት ግዜ እዛ የሚቆዩ አንዳንዶቹ ለቀናትና ለሳምንታት ይቆያሉ፣ ይህም ለነፍሳቸው ጉዳይ ነው፣ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ለነፍስ የሚያስፈልጉ ነገሮችም ይገኛሉ።።
ስለዚህ ቅዱስ ክያራን በዚህ መንፈስ እናስታውሳት፣ እርስዋን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቅዱሳንና ቅዱሳትም ማስታወስ አለብን፣ እነኚህ የእግዚአብሔር ሰዎች ሰማያዊ ነገሮችን ማሰብ እንዳለብን ይነግሩናል፣ ኣንደ ምሳሌ ያህል ክብረ በዓልዋ ትናንተ የተከበረ ቅዱስት ተረዛ በነደታ ዘመስቀል ቀርመሎሳዊትዋ ቅድስት ኤዲት ሽታይን የኤውሮጳ ጠበቃም አለች።። ዛሬ የምናስታውሰው ቅዱስ ሎረንዞ ዲያቆንና ሰማዕትም አለ፣ ቅዱስ ሎረንዞ የከተማ ሮማ ጠባቂ በመሆኑ ለሮማውያን መልካም ምኞቴን ለመግለጥ እወዳለሁ፣
በመጨረሻም ጸጥታን በማፍቀር ጸሎት እንድንማር ትረዳን ዘንድ እመቤታችን ድንግል ማርያምን እንማጠን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.