2011-08-10 15:43:22

ቅድስት ተረዛ በርናርደታ ዘመስቀል


በናሲዝም ግዜ ኤዲት ሽታይን በሚል ስም ትታወቅ የነበረች ያኔ ለእግዚአብሔርና ለሕዝብዋ ፍቅር ስትል ሰማዕት የሆነች ቅድስት ተረዛ በርናርደታ ዘመስቀል ትናንትና በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ግጻዌ በዓልዋ ተክብረዋል፣
ይህች በትውልድዋ ዕብራዊት የሆነች ጀርመናዊት ባለ ትልቅ ፍልስፍናዊ ዕውቀት በ1921 የቅድስት ተረዛ ዘአቪላ የሕይወት ታሪክ ካነበበች በኋላ የክርስትና ሃይማኖት ተቀበለች፣ በ1942 ዓም ደግሞ ከእኅትዋ ሮዛ ጋር በአውስኪዝ መታጐርያ በሰማዕትነት ሞተች፣
ቅዱስ አባታችን በሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ስለ ቅድስትዋ ብዙ ግዜ አስተምረዋል፣
ቅዱስነታቸው በወርኃ ግንቦት 2006 ዓም አውስኪዝ በጐበኙበት ወቅት። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በቦታው የተፈጸመውን ግፍ አስታውሰው እንዲህ ብለው ነበር፣ “በአሰቃቂው የሁለተኛ ዓለም ጦርነት ወቅት ኤዲት ሽታይን በሕይወትና ፍቅር ጌታ በሆነው በእግዚአብሔር የነበራትን ተስፋ በፍጹም አላጨለመችም፣ እርስዋ የዘመናችን ሰማዕት ናት፣ ሰማዕት የሆነችበት ምክንያትም ጌታ ኢየሱስን እስከ ሕይወትዋ ፍጻሜ ስለተከተለች ጥላቻና ዓመጽን አሸነፈች፣ ኤዲት በሆላንድ የቀርመሎሳውያን ደናግል ገዳም ውስጥ ስለነበረች ከናዚው ጭፍጨፋ ለመሸሽ ትችል ነበር፣ ሆኖም ግን ሕዝብዋን ለመካድ አልፈለገችም፣ የካቶሊክ ሃይማኖት ብትቀበልም የእስራኤል ልጅ መሆንዋ በጽኑ ስላመነችበት እስራኤላውያንን ያገኘ እንዲያገኛት ከሕዝብዋ ጋር በአውዝኪዝ ታጐረች፣
እንደ ክርስትያንና ዕብራዊት ኤዲት ከሕዝብዋ ጋር እና ለሕዝብዋ ለመሞት ፈለግች፣ በአውስኪዝ የታጐሩ ሁሉ የጀርመን ዜጎች እንደ የሀገሩ እድፍ ይታዩ ስለነበር ሁሉም ተገድለዋል፣ አሁን እኛ ግን እንደ የእውነትና የመልካም ነገር ምስክሮች እናከብራቸዋለን፣ ይህ የሚያመለክተው እውነትና በጎ ነገር ምንም ቢከፋ እንደማይሸነፉ ነው፣ እነኚህን ሰዎች አሁንም ቢሆን ለመጥፎ ነገር እጃቸውን ስላልሰጡ እንዲሁም ባለነው የሌሊት ጨለማ ቀድመውን እንደ ብርሃን ስለሚመሩን እናመሰግናቸዋልን፣” በማለት አስታወሰው ነበር።።
ኤዲት ሽታስን ፍልስፍና ስታጠና የታዋቂው ሁሰርል ተማሪ ነበረች፣ ፍላስፋ እንደመሆንዋ መጠንም እውነትን በሙሉ ልብዋ ትሻ ነበር።። እውነትን በመጨርሻ በኢየሱስ መስቀል አገኘችው፣ መስቀልን በመሸከም እውነት የሆነውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለማግኘት እንችላለን በማለትም አሰቃቂ በሆነ ችግር ሲገጥምም የጌታን ፍቃድ መፈጸም እንደሚቻል በተግባር አስተማረች፣ በመጨረሻም አከባብያችን እጅግ በጨለመ ግዜ ልባችንን ከላይ ለሚመጣው እውነተኛ ብርሃን መክፈት አለብን ብላ ታስተምር ነበር፣
በዕለታዊ ማኅደርዋ “ምሥጢር በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ ልረዳው ባልችልም በመስቀል ምልክት የጌታ ሙሽራ መሆን ምን ማለት መሆኑ ዛሬ ይገባኛል፣ ብላ ጽፋ ነበር፣
እንደ እርስዋ ሰማዕት የሆነው አባ ማክስሚልያኖ ኮልበና እርስዋ የሰማዕትነት ትርጉም ሲገልጡት የጌታ የላቀ የፍቅር መስዋዕት ይሉታል፣
ቅድስነታቸው ሰማዕት ማለት ምን ማለት መሆኑ ሲገልጡ። “ሰማዕት በዓለም ሥልጣን ፊት ፍጹም ነጻነት ያለው ሰው ነው፣ ይህ ነጻነት ሁለመናውን ለእግዚአብሔር በመስጠት ላንዴና ለመጨርሻ በታላቅ የሃይማኖት የተስፋና የፍቅር ተግባር ሕይወቱን ይሰዋል፣ ሁለመናውን በፈጣሪውና በአዳኙ ጌታ እጅ ያኖራል፣ በዚህም በመስቀል ላይ ስለኛ መስዋዕት ከሆነው ክርስቶስ ጋር ይወሃዳል፣ በሌላ አነጋገር ሰማዕትነት ለዘለዓለማዊው የእግዚአብሔር ፍቅር የሚሰጥ የፍቅር መልስ ነው፣” ሲሉ ገልጠውታል።።








All the contents on this site are copyrighted ©.