2011-08-08 16:39:26

የነፍሰ ኄር ር.ሊ.ጳ ጳውሎስ 6ኛ 33ኛው የዕረፍት ዝክር


ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካና በካስተን ጋንዶልፎ በቅዱስ ቶማስ ቊምስና የነፍሰ ኄር ር.ሊ.ጳ ጳውሎስ 6ኛ ዕረፍት 33ኛው ዓመት ተስታውሰዋል።።
በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መሥዋዕተ ቅዳሴን የመሩት የትርየስተ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጃምፓውሎ ክርፓልዲ ናቸው፣ ብፁዕነታቸው በሰጡት ስብከት “ነፍሰ ኄር ር.ሊ.ጳ ጳውሎስ 6ኛ መንፈሳውነታቸውን በቅዱስ ቊርባን ላይ እንደመሰረቱት፣ ይህም በመሥዋዕተ ቅዳሴ በሚያርገው ቅዱስ ቊርባን እንዲሁም በመንበረ ታቦት ካለው ቅዱስ ቊርባን በሚደረግ ስግደት ነበር፣ በሐዋርያዊ ጉዞ ወይም ሐውጾተ ኖልዎ ካልሄዱ በስተቀር ዘወትር እሁድ ከቀትር በኋላ በቤተ ጸሎታቸው በቅዱስ ቊርባን ፊት በመንበረ ታቦት ተንበርክከው ሲጸልዩና ሲያስተንትኑ ያሳልፉት ነበር፣ በዚህም የነበራቸውን ችግር ሁሉ በቅዱስ ቊርባን ላለው ኢየሱስ ያካፍሉት ነበር፣ ስለቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ መታደስም ይጸልዩ ነበር፣ ሌላው ዋነኛ የጸሎት መሣርያቸው ደግሞ ጸሎተ መቊጠርያ ነበር፣ እነኚህ ሁለት መንፈሳዊ ተግባሮች ሕይወታቸውን ሙሉ ያዘወተርዋቸው ነበር፣” ሲሉ ነፍሰኄር ር.ሊ.ጳ ጳውሎስ 6ኛ በቃልና በተግባር ነዋሪ አብነት እንደተውልን አሳስበዋል፣ በጳጳሳዊ የቅዱስ ቶማስ ቊምስና በቪላ ኖቫ ካስተንጋንደልፎ ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት ደግሞ የአልባኖ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሰመራሮ ሲሆኑ ለምእመናን ከትምህርታቸው በመጥቀስ ሰፊ ስብከት አቅርበዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.