2011-08-08 16:38:23

ኢየሱስ በትሑታንና በድሆች ይናገራል። እናዳምጠው፣


የላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ የምትከተል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ባለፈው ቅዳሜ የደብረ ታቦር በዓል አከበረች።። ቅ.አ.ር.በነዲክቶስ 16ኛ የደብረ ታቦር በዓል ከእግዚአብሔር የሚዘሩ ደስታዎች የሚያሳይ በዓል መሆኑን በማመልከት እነኚህ ደስታዎች እንደ መድረሻ ነጥብ ሊወሰዱ እንደማይገባ ገልጠዋል፣ ምክንያቱም ይላሉ ቅዱስነታቸው። ምክንያቱም እነኚህ ደስታዎች እግዚአብሔር በዚህ ምድር ሕይወት ጉዞ እያለን የሚሰጠን ብርሃናት ናቸው፣ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት የዚህ ምድር ኑሮአችን የሚመራ ኢይሱስ ብቻ በመሆኑ ነው ሲሉ አብራርተዋል፣
በደብረ ታቦር ጴጥሮስ ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታን ክብር ሲያስተነትኑ መንግሥተ ሰማይን ትንሽ አጣጣሙ፣ ይህ ዓይነት ሥጦታ እግዚአብሔር ከብርቱ ፈተና በፊት የሚሰጠን ነው፣ ሆኖም ግን በዚህ ምድር እያለን ከእነዚህ በቀር ለማንም አልተሰጠም፣ የሰው ልጅ ሕይወት በዚህ ምድር የእምነት ጉዞ ስለሆነ በትልቁ ብርሃን ነጸብራቅ ይጓዛል፣ በዚህ ጉዞ ግን አንዳንድ ግዜ ጨለም ሊል ይችላል፣ ፍጹም ጨለማም ሊወር ይችላል፣ በዚህ ምድር እስካለን ድረስ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግኑኝነት ከማየት ይልቅ በመስማት ይጠናቀቃል፣ የዚህ ዓይነት ኑሮ ዓይኖችን ጨፍኖ በሚደረግ አስተንትኖ ሊደረግ ይችላል፣ ለዚህ መሪ የሚሆነን ደግሞ በልባችን ውስጥ በእግዚአብሔር ቃል በተሰጠን ብርሃን ነው፣
ቅዱስ ጴጥሮስ በደብረ ታቦር ብዙ ሊቀመጥ ፈልጎ ነበር፣ እንዲያው እዛ ለመኖርም እቅድ አወጣ፣ ግጆዎች እንዲሠራም ሐሳብ አቀረበ፣ ሆኖም ግን የደብረ ታቦር የጌታ መለወጥ የትንሣኤ ዋዜማ ነበር፣ እዛ ለመድረስ ግን ሞትን ተሻግሮ ማለፍ የግድ ነው፣ ጌታ ለምን የደብረ ታቦር ተአምር ለሐዋርያት አሳየ ያልን እንደሆነ። ሐዋርያት የመስቀል ዕንቅፋትን ተሻግረው እንዲችሉ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ ፈተና ማለፍ የግድ መሆኑን እንዲረዱ ነው፣
እንታድያ የደብረ ታቦር የጌታ መለወጥ ትርጉሙ ምንድር ነው፤ ብለን የጠየቅን እንደሆነ። ቅዱስነታቸው ባለፈው ወርኃ ሚያዝያ 20 ቀን 2011 ዓም ባቀረቡት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ “የደብረ ታቦር ተአምር የኢየሱስ መለኮታዊነት መገለጥ እንጂ የኢየሱስ ፊት መለወጥ አይደለም፣ ይህም የሚያመለክተው ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ፍጹም አንድነት እንደነበረው ነው፣ ይህ አንድነት ብርሃን ሆነ፣ ለዚህም ነው በጸሎተ ሃይማኖት ዘተወልደ አኮ ዘተገብረ አሐዱ በመለኮቱ ብርሃን ዘእምብርሃን ከመልኮቱ ጋር አንድ የሆኑ ብርሃን ከብርሃን” ብለው አስተምረው ነበር።።
ሌላው በደብረ ታቦር የታየ ምልክት ከሰማይ “ይህ በእርሱ ደስ ያለኝ ልጄ ነው እርሱን ስሙት” የሚል ነበር።።
ኢየሱስን መስማት። እንደ ማርያም በመጽሐፍ ቅዱስ በታቀበው ቃሉ እርሱን መስማት ማለት ነው፣ እንዲሁም በዕለታዊ ሕይወታችን የሚገጥሙንን በመፈሳዊ ዓይን በማንበብ የእግዚአብሔር አሳቢነትን ማንበብ መስማት ማስተዋል ያመለክታል፣ በመጨረሻም በወንድሞቻችንና በእኅቶቻችን በተለይም ደግሞ ተጨባጭ የፍቅር ተግባራችንን ማሳየት ባለብን በትናንሽና በድሆች የሚለንን መስማት ማለት ነው፣ እንግዲህ የደስታና የፍቅር ሙላት የሚሰጥ ዋነኛው መንገድ ይህ ነው፣ ክርስቶስን መስማትና ለድምጹ መታዘዝ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.