2011-08-03 11:48:29

የኢጣልያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር ድጋፍ እና ትብብር


በቀንድ አፍሪቃ የተከሰተው ድርቅ እያስከተለው ያለው አሰቃቂው እርሃብ ለማስወገድ በመካሄድ ላይ ባለው መሠረታዊ የእርዳታ አቀርቦት የድጋፍ እና የትብብር ሂደት ካሪታስ የተሰየመው የኩላዊት ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር ቀዳሚ ተሳታፊ በመሆን ሰብአዊ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑ በኢጣልያ የኩላዊት ቤተ ክርስያን የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫፍ አስተዳዳሪ አባ ቪቶሪያ ኖዛ RealAudioMP3 ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀው፣ በቀንድ አፍሪቃ የሚገኙት ለኡካነ ወንጌል ገዳማውያን በጠቅላላ ሰበካዎች እያካሄዱት ባለው መሠረታዊ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት በመደገፍም ሆነ እርዳታ የማቅረቡንም እቅድ እግብ በማድረሱ ሂደት አቢይ ዳጋፍ እየሰጠ መሆኑ አመልክተዋል።

የሚቀረበው የሰብአዊ እርዳታ በተገባ ሁኔታ ለሚገባው ሕዝብ እንዲዳረስ በቀንድ አፍሪቃ ከሚገኙት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር ቅንርጫፎች ጋር ጭምር በመተባበር አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ገልጠዋል።

በቀንድ አፍሪቃ የተከሰተው በጠቅላላ 12 ሚሊዮን የክልሉ ነዋሪ ሕዝብ ለእርሃብ ያጋለጠው ችግር ባስቸኳይ ተገቢ መፍትሔ እንዲያገኝ የሚደረገው ርብርቦሽ በዚያ ክልል ባለው አለ መረጋጋት እንቅፋት እያጋጠመው ነው። ሆኖም ግን የእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስያን በካሪታስ የሚጠራው የተራድኦ ማኅበር በሰላም እና በችግር ጊዜም ከክልሉ ሕዝብ ጋር የሚኖር በመሆኑም፣ እርዳታ በማቅረቡ ሂደት ብዙ ችግር ሳያጋጠውም አቢይ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ አስታውቀው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው እሁድ እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባቀረቡት ስብከት፣ በእርሃብ እየተጠቃ ያለው የቀንድ አፍሪቃ ሕዝብ በማሰብ የተራቡት እና የተጠሙት ስቃይ እያየህ እንዳላየህ ሆነህ መኖር አይቻልም፣ ሰብአዊ እና ክርስትያናዊ ኃላፊነት እና ግዴታም ነው በማለት ያቀረቡት ጥሪ፣ መርህ ያደረገ ድጋፍ እና ትብብር መሆኑም አብራርተው፣ በጠቅላላ የኢጣሊያ ሰበካዎች በእርሃብ ችነፈር ለሚሰቃየው የቀንድ አፍሪቃ ሕዝብ ድጋፍ የሚውል ቅዱስ ቁርባን እለታዊ ምግብ መሚል መርህ ቃል የሚመኣ እርዳታ የማሰባሰብ የግብረ ሠናይ ቀን እ.ኤ.አ. መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚረጋግጥ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.