2011-08-03 11:46:55

የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ


በክሮአዚያ የፓረንዞ እና ፖሎ ሰበካ በኢጣልሊያ ቨነቶ ክፍለ ሃገር ፓዶቫ አውራጃ ተኦሎ ከተማ የሚገኘው አቢይ ቅርስ ተብሎ የሚነገርለት ብሔራዊ ቤተ መዝገብ እና መጻሕፍት ጭምር በሚገኝበት ታሪካዊው የበነዲክቶስ ፕራሊያ ገዳም መካከል ተከስቶ የነበረው የንብረት ይገባኛል ጥያቄ ጉዳይ፣ እርሱም በቀድሞ ዩጎስላቪያ የኮሙኒዝም ሥርዓት የተወረሰው በፕራሊያ በነዲክቶስ ገዳም በወቅታዊት RealAudioMP3 ክሮአዚያ የሚገኘው ንብረት መንግሥት የተወረሱት ንብረት ለባለቤት ካሳ ወይንም ንብረት እንዲመለስ የሚል ያጸደቀው ሕግ መሠረት ለበነዲክቶስ ፕራሊያ ገዳም የሚገባው ንብረት ሆኖ ነገር ግን በክርአዚያ የሚገኝ በመሆኑ የተወረሰው ንብረት ለክልሉ ሰበካ እንዲመለስ ያደረገ ሲሆን፣ የፕራሊያ በነዲክቶስ ገዳም ንብረቱ በተመለከተ የይገባኛል ጥያቄ በማቅረቡ ምክንያት የቀሰቀሰው አለ መግባባት በተመለከተ እና ቅድስት መንበር የወሰደችው ውሳኔ በተመለከተ ትላትና ከቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ መሰጠቱ ለማወቅ ተችለዋል።

የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ እንደሚያመለክተውም በቅድሚያ ተቀስቅሶ የነበረው አለ መግባባት የቤተ ክርስትያን ጉዳይ በቤተ ክርስትያን ውስጥ መፍትሔ ማግኘት የሚገባው ጥያቄ ነው። ስለዚህ ጥያቄው በተመለከተ ፖለቲካዊ አዝማሚያ ያለው የፖሊቲካ መሣርያ በማድረግ በክሮአዚያ እና በኢጣልያ ስለ ጉዳዩ የተላለፉት ዜናዎችን እና የተሰጡት አሰያየቶች በማስተባበል፣ የቅድስት መንበር ውሳኔ በቤተ ክርስትያን ውስጥ ያለው ፍትሐዊነት የሚያጎላ መሆኑ በማብራራት፣ ቅድስት መንበር እ.ኤ.አ. ከ 2004 ዓ.ም. ካለ ማቋረጥ በክሮአዚያ የፓረንዞ - ፖላ ሰበካ እና በኢጣልያ የፕራሊያ በነዲክቶስ ገድማ መካከል የተቀሰቀሰው የንብረት ይገባኛል ጥያቄ መፍትሔ እንዲያገኝ በቅርብ በመከታተል እና ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር በተናጥልም ሆነ በጋራ ውይይት በማካሄድ እ.ኤ.አ. ህዳር 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የይገባኛ ጥያቄ መፍትሔ እንዳያገኝ ከሚመለከተው አካል ጋር የሚመክር በካርዲናሎች ጉባኤ የጸና አንድ ድርገት እንዲመለመል በማድረግ ጥያቄው በጥልቀት ከመረመሩ በኋላ ባንድ የጋራው ስምምነት እንዲደረስ ጥረት በማድረግ ላይ እያለ ሆኖም በፓረንዞ-ፖላ ሰበካ በአንድዮሽ የተወሰደው ውሳኔ ቢኖርም ቅሉ፣ በመጨረሻ ሁለቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እና የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ድርገት ተመርቶ በተካሄደው የጋራው ውይይት አማካኝነት የተደረሰው የጋራው የስምምነት ሰነድ፣ እ.ኤ.አ. ነሐሴ ወር 2010 ዓ.ም. ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተላልፎ ቅዱስነታቸውም የተደረሰው ስምምነት እንዳጸደቁት የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም መግለጫ ያብራራል።

ሆኖም የፓረንዞ-ፖላ ሰበካ ጳጳስ በተደረሰው የስምምነት ሰነድ ፍሪማቸውን ከማኖር በመቆጠባቸው ምክንያት ስምምነቱ ቤተክርስያናዊ ብቻ ሳይሆን በፍትኃ ብሔር ደረጃ ጭምር ዋጋ ያለው መሆን ስላለበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሰበካውን ወክለው ፊርማቸው እንዲያኖሩ እ.ኤ.አ. ሰነ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ብፁዕ አቡነ ሳንቶስ አብሪል ይ ካስተዮ ሰበካውን የሚወክለው ድርገት ልዩ ባለ ሥልጣን ሪርማ ለማኖር ለሚያስፈገው የጊዜ ገደብ የሰበካው ጳጳስ በመሆን የተደረሰው ስምምነት ቤተ ክርስትያናዊ እና በፍትኃ ብሔር ደረጃ ክብሩን ለማስጠበቅ መቻሉ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ ያመለክታል።

የቅድስት መንበር ውሳኔ ፍትሃዊ እና ሚዛኑ የጠበቀ ለማንም የማያዳላ ነው። ስለዚህ ውሳኔው ያዳለ ነው ተብሎ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የተሰራጨው ዜና እና አስተያየት መሠረት የሌለው መሆኑ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ ያረጋግጣል።








All the contents on this site are copyrighted ©.