2011-08-02 13:46:02

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ሦስተኛው ትውልድ


ሁሌ እንደተለመደው በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ሦስተኛው ትውልድ በሚል ርእስ ሥር ቅዳሜ ባቀረቡት ርእሰ ዓንቀጽ፣ ሁሌ በየዓመቱ በእተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ቸርነት እና አሳቢነት የሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን፣ ዘንድሮ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በስፐይን ርእሰ ከተማ ማድሪድ እ.ኤ.አ. ከ ነሐሴ 16 ቀን እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ቅዱስ ጳውሎስ ለቆላስያስ በጻፈው መልእክት ምዕራፍ ሁለት ቁጥር ሰባት ባለው “በክርስቶስ ተመሥርታችሁና ታንጻችሁ በተማራችሁት መሠረት በእምነታችሁ ጸንታችሁ ኑሩ” በሚለው ቃል ተመርቶ እንዲካሄድ መወሰኑ ማእከል በማድረግ፣ በዚህ 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመት የወጣት ብዛት ተሳታፊ እንደሚሆን ከወዲሁ ግምት መሰጠቱንም ጠቅሰው፣ የዚህ የወጣቶች ቀን አስተናጋጅ የሆነቸው የማድሪድ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ሩዎኮ ቫረላ በዓሉ ምክንያት በማድረግ በሰጡት መግለጫ የዛሬ 20 ዓመት በፊት በስፐይን በሳንቲያጎ ደ ኮምፖስተላ ከተማ መካሄዱ ዘክረው ስፐይን ስለ በዓሉ ተመኩሮ ያላት መሆንዋ ገልጠው፣ የዘንሮው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ሦስተኛው ትልውድ የሚያስተናግድ እርሱም የመጀመሪያ ወጣት ትውልድ የሚባለው እ.ኤ.አ. የ1968 ዓ.ም. በመቀጠልም ሁለተኛው የ 1989 ዓ.ም. እርሱም የበርሊን ግንብ የፈረሰበት እና የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሥልጣናዊ ትምህርት አድማስ የጎላበት ሶስተኛው ትውልድ ደግሞ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለት ሺሕኛው የኢዮቤል አመት ቅዱስ በር የከፈቱበት ዓመት ጀምሮ ያለ መሆኑ በማስታወስ፣ ስለዚህ ይህ ሦስተኛው ትውልድ የድረ ገጽ እና የማኅበራዊ ድረ ገጽ እርሱም በሥነ አኃዝ በተራቀቀው እደ ጥበብ እውቀት እና የአጠቃቃም ብቃት የተካነው ወጣት የሚመለከት መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በማብራራት፣ አጠር አድርጎ እና ጠቅለል ባለ መልኩ ትውልድ በዚህ መልኩ በመለየት፣ በባህል በእደ ጥበብ እና በአስተሳሰብ የተለወጠው የዓለም የማኅበረሰብ ሁኔታ በወጣቱ ትውልድ ዘንድ ጎልቶ የሚነጻበርቅ መሆኑም ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን በመገኘት መሪ ቃል ሥልጣናዊ ትምህርት በሚለግሱበት 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የሚሳተፈው የወጣት ትልውድ ብዛት ብቻ ሳይሆን ያለው ባህላዊ ለውጥ ጭምር ለመገመቱ አያዳግትም ስለዚህ ለዚህ ለሁት ሺሕኛው ወጣት ትውልድ በሁሉም ደረጃ ተመስሎ እና ቀርቦ ክርስቶስን ማቅረብ እና ማበሰር ለሚለው ተልእኮ መንገድ የሚያመለክት ነው።

በተራቀቀው ዓለም ለሚኖር ወጣት በክርስቶስ ተመሥርተን እና ታንጸን በተማርነው መሠረት በእምነት ጸንትን በመኖር አስፍሆተ ወንጌል እግብር ላይ ማዋል፣ ትልውድ ቢለዋወጥ የማያልፈው የማይለወጠው እና የማያረጀው ለሁሉም የሚናገር በክርስቶስ ላይ የጸናው እምነት በመመስከር በዚህ ሂደትም ወጣት ትልድ በማነጽ መጪው ሕይወት ተስፋ እና ደስታ ያተካነው ሆኖ ከወዲሁ ለመገንባት የሚያግዝ መሪ ቃል የሚለገስበት ዓቢይ በዓል ነው በማለት አባ ሎምባርዲ ያቀረቡትን ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.