2011-08-02 13:45:07

ለቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ 60ኛው የክህነት ዓመት ክብር


ባለፈው ቅዳሜ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የክህነት ማዕርግ የቀበሉበት 60ኛው ዓመት ምክንያት ለበጋው ዕረፍት በሚገኙበት በካስተል ጋንዶልፎ ሐዋርያዊ ሕንፃ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 8 ቀን 1951 ዓ.ም. የመጀመሪያ መሥዋዕተ ቅዳሴ ካሳረጉባት ባቪየራ ከምትገኘው ትራኡንስታይን ከተማ የተወሃደ የሙዚቃ ትርኢት ገጸ በረከት እንዳቀረበላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

የተወሃደው የሙዚቃ ትርኢት በመምህር ኦራፎ አውጉስት ፐርኸርማየር የተመራ መሆኑም ሲገለጥ፣ በጠቅላላ በከተማይቱ መስተዳድር ሊቀ መንበር ሄርማን ስታይንማስል የተመራው 250 የሙዚቃ ባለ ሙያዎች ያጠቃለለው ልኡካን፣ ለቅዱስ አባታችን ክብር የተለያዩ ባህላዊ እና የተወሃደ የሙዚቃ ትርኢት በማቅረብ እና እንዲሁም የክብር ቀለቤት ጭምር ገጸ በረክበት እንዳቅረበም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ቅዱስ አባታችን የሙዚቃው ትርኢት ፍጻሜ ባሰሙት ንግግር፣ በእናንተ አማካኝነት የተወለድኩባት ባቨሪያ እዚህ ኅያው ነች፣ በእናንተ አማካኝነት ያች ከተማ ባቀረበችልኝ የቀለቤተ ገጸ በረከት እና የተወሃደ የሙዚቃ ትርኢት አማካኝነት የባቪየራ ከተማ ባህል እና ውበት ተመልሼ በመቓኘት በደስታ ዳግም መለስ ብየ እንድኖረው ስላደረጋችሁኝ ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁኝ ካሉ በኋላ አክለውም ባቪየራ አለ ባህላዊ ሙዚቃዋ አለ አረንጓዴው ልምላሜ ሃብትዋ ጭምር ባቪየራ ባልሆነች ነበር። በክርስቶስ ላይ ጸንተን ክርስትያናዊ እምነታችንን በመኖር በፍቅር ላይ በተመሠረተው የእርስ በእርስ መቀራረብ እና በደጋገፍንም በማጎልበት የአንድ አባት ልጆች ከሚለው እምነት በመንደርደር ለሁሉም ሰው ዘር ቅርብ እንሁን እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

የሰማዩ ግርማ እና ወበት እኛ ዘንድ ደርሶ ዓለምን ውበት በማልበስ የበለጠ ግርማ የሞላውም እንዲሆን በእምነት እንድንነካ ዘንድ እንፍቀድ፣ እምነትን እንኑር በማለት ይኸ የዘወትር ጸሎቴ ነው በማለት ያሰሙትን ንግግር እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.