2011-07-29 13:35:50

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በኢጣልያ የካላብሪያ ሐዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በኢጣሊያ ካላብሪያ ክፍለ ሃገር ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ቀደም ተብሎ ተገልጦ እንደነበር የሚዘከር ሲሆን፣ የዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር ትላትና የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ይፋ በማድረግ፣ ቅዱስ አባታችን በላሜዚያ ተርመ ጥቅምት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ 150 ሺሕ ምእመናን እንደሚገኙ ከወዲሁ ሲገለጥ፣ እስካሁን ድረስ 60 ሺሕ ምእመናን የተመዘገቡ ሲሆን፣ እንደሚባለውም ከሆነ የተሳታፊው ምእመን ብዛት ወደ 250 ሺሕ ከፍ ሊል እንደሚችል የከተማይቱ መስተዳድር ምክር ቤት ያሰራጨው መግለጫ የጠቀሰ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ካላብሪያ የተለያየ ማኅበራዊ ችግር የሚፈራረቅባት ክፍለ ህገር ስትሆን የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ጉብኝት ለክልሉ ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃ እና በዚሁ ረገድ በተለያየ መልኩ ተስፋው ያመነመነ ለሚመስለው ልክክሉ ወጣት ትውልድ የሚደገፍ ፍትህ የሚያነቃቃ መሆኑ ከወዲሁ ሲገለጥ፣ በጉጉት የሚጠበቅ እና ብዙ ትኩረት የሚደረግበት ሐዋሪያዊ ጉብኝት እንደሚሆን ሲር የዜና አገልግሎት ያስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.