2011-07-29 13:34:53

የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት እና የውጭ ዕዳ ጫና


የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የውጭ ብድር ጫና ለመክፍል ትችል ዘንድ የወጪ እቅድ ከፍ በማድረግ አገሪቱ ያለባት የውጭ ብድር ጫና የመክፈል አቅሟ ከፍ ለማድረግ ሁለቱም የፖለቲካ ሰልፎች ያነጣጠሩበት ዓለማ ቢሆንም እቅዱ መከተል በሚገባት የኤኮኖሚ ሥልት በመምራት ላይ ባለው እና በተቃቅዋሚው የፖለቲካው ስልፍ መካከል አለ መግባባት ከማሰከቱሉም አልፎ ሁለቱ አፖለቲካ ሰልፎች በውሳኔአቸው የጸኑ ነው የሚመስለው።

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የዕዳው ጣራ ከፍ ለማድረግ የሚል ስምምነት እንዲደረስ በዚሁ ሐሳብ ላይ ሁሉንም ለማሳመን ጥረት እደረጉ ቢሆንም እሳቸው አስታራቂ የሚሉት ሐሳብ ብዙሃን መቀመጫ የረፓብሊካውያን በሆነበት የሕዝብ ተመራጮች ምክር ቤት ዘንድ ተቃውሞ ካየለበት እና ለማረጋገጥ ካልተቻለ ርእሰ ብሔሩ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት በርእሰ ብሔርነት ሥልጣን የመወሰን እርሱም ድምጽ በድም የመሻር መብት ለመጠቀም እንደሚገደዱ አስታውቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የሕዝብ ተመራጮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር ጆን ቦህነር ያቀረቡት ሐሳብ ለውይይት እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችለዋል።

የሥነ የተባበሩት አመሪካ መንግሥታት ሊቅ ደኒስ ረድሞንት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የኤኮኖሚው ጥያቄ በአገሪቱ በ 2012 ዓ.ም. ለሚካሄደው የርእሰ ብሔር ምርጫ ወሳኝ ይሆናል፣ ሆኖም የአገሪቱ ማእከላዊው ችግር የሥራ አጥነት ጉዳይ ነው። ይህ በሰኔ ወር የሥራ አጡ ሚዛን 9.2% መሆኑ ተገልጦ እንደነበር አስታውሰው ይህ የሥራ አጡ ብዛት ወደ 5 እና 6% ዝቅ ካላለ ለኤክኖሚው ፖለቲካ አቢይ ችግር ይሆናል ብለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.