2011-07-22 16:44:37

ቅድስት መንበር የተባበሩት መንግሥታትን ሕገ ወጥ የጦር መሳርያ ልውውጥ እንዲገቱ አሳሰበች፣


በዓለም ተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ቅድስት መንበርን ወክሎ የተሳተፈ ቡድን ሕገ ወጥ የጦር መሣርያ ልውውጥን አስመልክቶ። “የጦር መሣርያ እንደ ማንኛውም የንግድ ዕቃ የሚሸጥና የሚለወጥ ሳይሆን ብዙ የሰው ሕይወት እያጠፋ ያለ አደገኛ በመሆኑ በተለይ ደግሞ በሕገ ወጥ የሚሸጥና የሚለወጡ የጦር መሣርያዎች ዓለማችንን ስለሚያንውጥ የዓለም የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ሕገ ወጥ የጦር መሣርያ ልውውጥ እንዲገቱ ኃላፊነታቸው መወጣት አለባቸው” በማለት አሳስበዋል።። ጉባኤው ከሐምሌ 11 እስከ 15 ቀን 2011 በተባበሩት መንግሥታት ጽሕፈት የተካሄደ ሲሆን መርሐ ግብሩም በ2012 ዓም በሚካሄደው ኮንፈረንስ ድምፅ ለሚሰጠው የጦር መሥርያ ንግድ ውል በሚመለከት ለመወያየት ነበር፣ ቅድስት መንበርን የወከለው ቡድን አባላት በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ወኪል ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ ሹሊካት በቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ከመንግሥታት ጋር የሚገናኝ ክፍል አባል ፓውሎ ኮንቨርሲ። የቡድኑ ጸሐፊና የጦር መሣርያ አዋቂ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ቾኒኒ እና ሌሎች ተወካዮች እንደነበሩ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል።።







All the contents on this site are copyrighted ©.