2011-07-14 16:43:15

ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ውሳኔ


ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. 2012 ዓ.ም. የዓቢይ ጾም መግቢያ ወቅት “ወንጌላዊ ተልእኮ በመዲና” በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ የሚፈጸም ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ እንደሚያነቃቃ የዚሁ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊሲከላ የባርቸሎና የኤስተርጎም ቡዳፔስት የመከለን ብራሰልስ የዱብሊን የኮሎን የሊስቦና የሊቨርፑል የፓሪስ የቶንሪኖ 00:03:21:19 የቫርሳቪያ እና የቪየና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ትላትና ቫቲካን በሚገኘው የዚሁ ምክር ቤት አዲስ ሕንጻ በመሰብሰብ እቅዱን በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ እንዳመለከቱ የቅስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ብፁዕ አቡነ ፊሲኬላ ወንጌላዊ ተልእኮ በርእሰ ከተሞች በሚል ርእስ ሥር ይህ በሳቸው የሚመራው ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ምክር ቤት የወጠነው እቅድ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በኤውሮጳ ተከስቶ ያለው ዘርፈ ብዙ ቀውስ በዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ አማካኝነት ተገቢ መልስ ለመስጠት እንዲቻል ከኤውሮጳ የአበይት ርእሰ ከተሞች ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመገናኘት በጋራ የተወጠነው ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ መሆኑ ጠቅሰው፣ እ.ኤ.አ. በ1991 ዓ.ም. ቀጥሎም በ1999 ዓ.ም. የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ያካሄዱዋቸው ሁለት ሲኖዶስ 2003 ዓ.ም. እንዲሁም ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ “ኤክለሲያ ኢን ኤውሮፓ- ቤተ ክርስትያን በኤውሮጳ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሓዋርያዊ ምዕዳን ፈር በማድረግ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የወጠነው እቅድ መሆኑ ገልጠዋል።
በነዚህ ከተጠቀሱት አበይት ከተሞች ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተካሄደው ስብሰባ የ2012 ዓ.ም. አቢይ ጾም በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ ሳይሆን በኤውሮጳ ደረጃ በነዚህ አበይት ከተሞች ወንጌላዊ ተልእኮ እርሱም ለኤውሮጳ ወቅታዊ ሁኔታ እና የተከሰተው ዘርፈ ብዙ ቀውስ የቤተ ክርስትያን ማህበራዊ ትምህርት ሥልጣናዊ ትምህርት እና ቃለ ወንጌል መሠረት መልስ ለመስጠት እንዲቻል አስፍሆተ ወንጌል ላይ ያነጣጠረ አንድ አይነት የጋራ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንዲረጋገጥ እና በዚህ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተልእኮ አገልግሎት ለሚሰጡት የውሉደ ክህነት አባላት ዓለማውያን ምእመናን እና የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ተገቢ ሕንጸት መስጠት የሚል መሆኑም ገልጠው፣ ይህ በሳቸው የሚመራው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ባካሄደው አንደኛው ምልአተ ይፋዊ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተገኝተው በኤውሮጳ ተከስቶ ያለው መከፋፈል ለመቅረፍ በቤተ ክርስትያን ደረጃ የውህደት እና የአንድነት ትእምርት መመስከር አስፈላጊ መሆኑ ላሠመሩበት አንገብጋቢው ነጥብ አቢይ ግምት የሰጠ መሆኑ አብራርተዋል። ይኸንን እቅድ ለመወጠን የተካሄደው ጉባኤ እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. ሊካሄደው ተወስኖ ባለው ሲኖዶስ ጭምር በኤወሮጳ መከፋፈል የሚያስወግድ አንድነተ እና ውህደትን የሚያነቃቃ በቤተ ክርስትያን ደረጃ በዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ላይ ያተኮረ ቀጣይ የጋራ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንዲኖር የሚል ሀሳብ እንደሚቀርብም ከወዲሁ ምልክት የታየበት ነው፣ ስለዚህ የኤውሮጳ ሰበካዎች እና አገረ ስብከተች ለጋራ ጥቅም በጋራ ዓላማ በጋራ እንዲጋጓዙ የሚያሳስብ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.