2011-07-13 13:49:22

ብፁዕ አቡነ ኩሳላ፦ ብቃት ያለው ግልጽ እና የተገባ መንግሥት በደቡብ ሱዳን


በደቡብ ሱዳን የቶምቡራ ያምቢዮ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድዋርዶ ሂቦሮ ኩሳላ የዚህች አገር ሕዝብ ባለፉት ረዥም እና አሰቃቂ የ21 ዓመት ጦርነቶች ወቅት በሩቅ ይመለከተው የነበረው ተስፋው የደቡብ ሱዳን ሉአላዊነት በማረጋገጥ እና ነጻነቱን RealAudioMP3 በማወጅ ቢጨብጠውም የነጻነት መንገድ በመከተል መከባበር የተካነው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የሚረጋገጥበት ማኅበራዊ ሕይወት እንዲኖር ከጎረቤት አገሮች እና ከሁሉም አገሮች ጋር በሰላም ለመኖር የሚያበቃው ሰላም እንዲጸና የሚያበረታታ እና የሚደገፍ በክልሉ የሚታየው ድኽነት ለመቅረፍ የሚያስችል የዓለም አቀፍ ድጋፍ እጅግ ያስፈልገዋል፣ የተቋቋመው አገር ዘርፈ ብዙ ችግሮች የተከናነበው አዲስ አገር በመሆኑም ገና ማኅበራዊ ሰብአዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጥገና እንደሚያስፈልገው የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተገንዝቦ፣ ከዚህ ሕዝብ እና አገር ጎን በመሆን የሚሰቃዩት አቢያተ ክርስትያን የሚደግፈው የግብረ ሠናይ ማኅበር የሚያደርገው ርብርቦሽ አብነት ያደረገ ድጋፉ እንዲያቀርብ አደራ በማለት ግልጽ እና የተገባ መንግሥት ያላት አገር እንድትሆን የዓለም አቀፍ መንግሥታት ድጋፍ እንዳይለየውም ጥሪ ማቅረባቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.