2011-07-13 13:47:52

ቅዱስ በነዲክቶስ ዘኖርቻ፦ የኤወሮጳ አባት ለኤውሮጳ ኅብረት መሠረት ምክንያት


የኤውሮጳ ኅብረት ተረኛ ሊቀ መንበር በመሆን ኃላፊነቱን የተረከበው የፖላንድ መንግሥት ኃላፊነት የተዋጣለት እንዲሆን የእግዚአብሔር ጥበቃ እንዳይለው ከትላትና በስትያ የኤውሮጳ ቅዱስ ጠባቂ ቅዱስ በነዲክቶስ ዘኖርቻ ዓመታዊ በዓል በተከበረበት ዕለት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርት በቅድስት መንበር የፖላንድ RealAudioMP3 ልኡከ መንግሥት እና የተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት ጭምር የተሳተፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 24 ቀን 1964 ዓ.ም. ቅዱስ በነዲክቶስ ዘኖርቻ የኤውሮጳ ጠባቂ ቅዱስ የሰላም መልእክተኛ ውህደት እና አንድነት እግብር ላይ ያዋለ የሥልጣኔ መምህር በማለት ገልጠዉት እንደነበር ብፁዕ አቡነ ዶሚኒክ ማምብርት ባሰሙት ስብከት አስታውሰው፣ የኤውሮጳው ኅብረት እውነተኛው አንድነቱን ለመመስከር እና ላስተማማኝ ውኅደት መሠረት በሆነው ጽኑ ባህልዋ ላይ መልሕቅዋን ታኖር ዘንድ ወሳኝ ነው። አንድነትዋ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ ገጽታ ያለው ከመሆኑ በፊት ባህልዋ ላይ የጸና ክርስትያናዊ መሠረት ያለው ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

የዘመኑ ሰው በወቅቱ እድገት እና ብልጽግና እንዲሁም በምቾት ሕይወት ታውሮ ወደ ላይ የሚያቀናው ከነገ ባሻገር ቀና እንዲል የሚገፋፋው ባህርዩ በማግለል ወደ ታች እርሱም ወደ መሬት የሚያተኩረው ባህርዩን ብቻ በመከተል በዚሁ ተጨባጭ ዓለም ላይ ገዛ እራሱን እና ሕይወቱን በመገንባት ስለ እግዚኣብሔር ፈቃዱንም ጭምር ግድ የማይል መለኮታዊ ባህርይ የሚዘነጋ እና የሚረሳ በጠቅላላ እግዚአብሔር እንደሌለ በውስጠ ታዋዊነት አንግቦ የሚኖር ባህል በመከተል የሚኖር በመሆኑ ምድራዊ ሕይወት እንደ ጣዖት በማምለክም ሲኖር በመጨረሻ ተደናግሮ ይቀራል ምክንያቱም መልህቁ ያኖረበት ጊዚያዊ ባህል እውነተኛው እርካታ ሳይሰጠው ሲቀር ተታሎ እንደኖረ ይረዳል። ስለዚህ የእግዚአብሔር ወደ እውነት በእውነት እንድንኖር ይጠራናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.