2011-07-11 13:49:50

ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት፦ ለደቡብ ሱዳን


ብሩህ እና ሰላም የተካነው የወደፉት ሕይወት ለደቡብ ሱዳን የተመኘው ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት፣ የአገሪቱ የምሥረታ ቀን ምክንያት በማድረግ በምክር ቤቱ ጠቅላይ ዋና ጸሃፊ መጋቤ ኦላቭ ፍይክሰ ትቫይት አማካኝነት ለአዲሲቱ RealAudioMP3 አገር ርእሰ ብሔር ሳልቫ ኪር ማያርዲት ባስተላለፈው መልእክት፣ ታሪካዊው የነጻነት ቀን ታላቅ ደስታ መሆኑ በመጠቀስ፣ ቀኑ በደረሰ ጊዜ የማይረጋገጥ ሁኔታ የለም ካሉ በኋላ፣ በዚሁ ክልል ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ለሰላም እና እርቅ የሰጠው አገልግሎት ዘክረው፣ ሰላም እና እርቅ ከመቼውም በመለጠ ለክልሉ ለተሟላ መረጋጋት እና እድገት ወሳኝ መሆኑ አብራርተው፣ የነጻነቱ ቀን ሁሉም በተለያዩ ግጭቶች የተሳተፉት ታጣቂ ኃይሎች በጋራ ለተሟላ እርቅ መረጋገጥ ተግተው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው በመግለጥ የሰብአዊ መበት እና ፈቃድ ፍትሕ እና ሰላም ዋስትና የሚሰጥ ሁኔታ በመፍጠር ለዜጎች እና ለአገር ጥቅም ይጠመዱ ዘንድ አደራ ብለዋል።

ይህ ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ያስተላለፈው መልእክት ቅዳሜ በተካሄደው የደቡብ ሱዳንን የነጻነት በዓል ቀን ምክር ቤቱን ወክለው በተገኙት እ.ኤ.አ. ከ 2003 ዓ.ም. እስከ 2009 ዓ.ም. ምክር ቤቱን በዋና ጸሓፊነት በመሩት ምጋቤ ሳሙኤል ኮቢያ በኩል በይፋ መነበቡ ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.