2011-07-11 13:51:06

ማድሪድ 2011 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን


ሁሌ በየዓመቱ በእተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ቸርነት እና አሳቢነት የሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዘንድሮ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት በስፐይን ርእሰ ከተማ ማድሪድ እ.ኤ.አ. ከ ነሐሴ 16 ቀን እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. RealAudioMP3 እንደሚካሄድ በተደጋጋሚ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ይኸው በዚህ ዓቢይ ዓለም አቀፍ በዓል ለመሳተፍ በመመዝገብ ላይ የሚገኘው የተሳታፊ ወጣት ብዛት በዓሉ እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከፍ እያለ መምጣቱ ሲነገር፣ እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. ይኸንን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ያስተናገደችው የአውስትራሊያ ዜጋ ተሳታፊ ወጣት ብዛት አራት ሺህ መድረሱ የሲድነይ ረዳት ጳጳስ የ2008 ዓ.ም ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የአዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉት ብፁዕ አቡነ ጆን ፖርተውስ ገልጠዋል። ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ወጣቱ ትውልድ በጋራ ኩላዊው እምነቱን እንዲመሰክር የሚደግፍ መሆኑ ጠቀሰው፣ በዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከነሐሴ 18 እስከ ነሓሴ 21 ቀን በመገኘት መሪ ቃል በሚሰጡበት ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ ከተመዘገቡት የአውስትራሊያ ወጣት ዜጎች ውስጥ ለበዓሉ ወደ ማድሪድ ከመነሳታቸው በፊት በቅድስት መሬት መንፈሳዊ ንግደት እንደሚያከናወኑም ገልጠዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.