2011-07-11 13:48:52

የሁሉም ድጋፍ በተለይ ደግሞ በእግዚአብሔር መታመን


በደቡብ ሱዳን የዋው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሩዶልፍ ደንግ የደቡብ ሱዳን ነጻነት በማስመልከት በሰጡት መግለጫ፣ አዲሲቷ አገር የሁሉም ድጋፍ እንደሚያሻት ከገለጡ በኋላ፣ ከሁሉም በላይ የሁሉም መሠረት የሆነው በእግዚአብሔር RealAudioMP3 መታመን በእጅጉ እንደሚያስፈልገው ነው እንዳሉ ቺሳል የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የተረጋገጠው የነጻነት ቀን ምክንያታ እግዚአብሔርን አመስግነው፣ ይህ ቀን እንዲረጋገጥ የአገሪቱ ዜጎች በተለያየ ዘርፍ የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦ አበርከተዋል። የስንቱ ሕይወት መሥዋዕት የተከፈለበት፣ ስቃይ እና ድኽነት ስደት እና መከራ የተፈራረቀበት ጉዞ ቢሆንም፣ ይህ ሁሉ ስቃይ ያስገኘው ወጤት አቢይ ጸጋ ነው። በውስጥ እና በውጭ አገር የሚኖሩት የዚህች አዲሲቷ አገር ዜጎች ለዚህች አገር ልማት የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ብፁዕነታቸው ጥሪ እንዳቀረቡም የዜና አገልግሎት ያመለክታል።

የዚህ ክልል የተሟላ እድገት የቤተ ክርስትያን አስተዋጽኦ እጅግ አስፈላጊ ነው። በተለይ ደግሞ በዚሁ የአገሪቱ ሉአላዊነት መረጋገጥ ወዲህ በክልሉ ልኡካነ ወንጌል ገዳማውያን ካህናት እና ደናግል የበጎ ፈቃድ አገልጋዮች የአለማውያን ምእመናን ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ ነው። አገሪቱ የሁሉም ድጋፍ የሚያሻት መሆኑ በመጥቀስ ከሁሉም በላይ የእግዚአብሔር ድጋፍ መሆኑም ዘክረው፣ የቀንድ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት የተመሠረተበት 50ኛው ዓመት ምክንያት በናይሮቢ ባካሄደው 17ኛው ይፋዊ ጉባኤው ድጋፉን ለደቡብ ሱዳን ማረጋገጡንም እንዳስታወሱ ቺሳል የዜና አገልግሎት አመለከተ።All the contents on this site are copyrighted ©.