2011-07-08 16:12:54

ቫቲካን፣ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. አንዳንድ ፁዓን ጳጳሳትን ለአዲስ የሥራ ኃላፊነት ሰየሙ


ቅዱስ አባታች የቅድስት መንበር የቁጠባ ማስታወቂያ መርሃ ግብር ባለ ሥልጣን ብፁዕ ካርዲናል አቲሊዮ ኒኮራ የሐዋርያዊ መንበር የንብረት ሃብት የሚቆጣጠረው የመስተዳዳር ቢሮ ሊቀ መንበር በመሆን ከሚያገለግሉበት ኃላፊነት እንዲነሱ ያቀረቡት ጥያቄ ቅዱስ አባታችን በመቀበል አወንታዊ ምላሽ እንደሰጡበት ለማወቅ ሲቻል፣ በምትካቸው የሳቮና ኖሊ ሊኂቅ ሊቀ ጳጳስ RealAudioMP3 ብፁዕ አቡነ ዶመኒኮ ካልካኞ፣ በዋና ጸሓፊነት ደግሞ በቫረሰ ከተማ የሚገኘው በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ስም የሚጠራው የማኅበረ አምብሮዚዮ የሥነ ሃይማኖት ተቋም እንዲሁም የሚላኖ ርእሰ ሰበካ ለቤተ ክርስትያን የኤኮኖሚ ድጋፍ የሚያነቃቃ ማኅበር ዋና አስተዳዳሪ ሆነው በማገልግል ላይ የሚገኙትን ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ሚስቶን መሾማቸው የቅስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ ካርዲናል ኒኮራ ከተደራቢው የሥራ ኃላፊነት እንዲነሱ ያቀረቡት ጥያቄ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አወንታዊ ምላሽ ስለ ሰጡበትም ይኸው ብፁዕነታቸው ሙሉ በሙሉ ቅዱስነታቸው ባላቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ሥልጣን መሠረት እ.ኤ.አ. ታሕሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ የወንጀል ቡድኖች አለ ሕግ የሚያካብቱት የገንዘብ ሃብት ሕገ ወጥነቱን ለመጋረድ በሕጋውያን የኤኮኖሚ ዘርፎችን ለማዋል የሚፈጽሙት ደባ ለመቆጣጠር እንዲቻል እና የወንጀል ብዱኖች የሚያዘዋውሩት የገንዘብ ሃብት ለመቆጣጠር በሚል ፍላጎት የጸደቀው ዓለም አቀፋዊው ሕግ ጋር የሚስማማ ባጸደቁት ሕግ መሠረት ለተቋቋመው የቅድስት መንበር የቁጠባ ማስታወቂያ ጉዳይ ቢሮ በመምራት እንደሚያገልግሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወቅ፣ የወንጀል ብዱኖች የሚያንቀሳቅሱት የገንዘብ ሃብት ለመቆጣጠር ታልሞ ሕግ በማጽደቅ በሚደረገው ጥረት ቅድስት መንበር ከሚጠቀሱት አገሮች ውስጥ ቀዳሚው ሥፍራ ይዛ እንደምትገኝም ይነገራል።







All the contents on this site are copyrighted ©.