2011-07-08 16:11:41

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የበጋው መርሃ ግብር


ትላትና በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ 11 ሰዓት ተኩል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለበጋው የዕረፍት ጊዜ በላዚዮ ክፍለ ህገር ወደ ሚገኘው ካስተል ጋንደልፎ ተብሎ በሚጠራው ከተማ ወዳለው ሐዋርያዊ ሕንፃ መዛወራቸው የቅስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ከሰጡት ጋዜጣዊ RealAudioMP3 መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።

ቅዱስ አባታችን ካስተል ጋንደልፎ በሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንፃ የበጋው የዕረፍት ጊዜ ሲያሳልፉ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜያቸው መሆኑ የገለጡት አባ ሎምባርዲ አያይዘውም፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አልፎ አልፎ ወደ ተራራማ የከተሞች ክልል በመሄድ የበጋው የዕረፍት ጊዜ ያሳለፉ እንደነበር ዘክረው፣ ሆኖም በካስተል ጋንደልፎ የሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንፃ ዘወትር የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የበጋው የእርፍት ጊዜ ሐዋርያዊ መንበር መሆኑ አስታውሰዋል። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተራራማ ከተሞች የበጋው የእረፍት ጊዚያቸውን እንዲያሳልፉ ከተለያዩ ከተሞች የተጋበዙ ቢሆንም ቅሉ ካስተል ጋንደልፍ ሐዋርያዊ ሕንፃ የሚገኝበት ለር.ሊ.ጳ. ዕለታዊ መርሃ ግብር የሚያመች ለሐዋርያዊ አገልግሎት ማስፈጸሚያ ታቅዶ የተገነባ ሕንፃ በመሆኑ ምክንያት ቅዱስነታቸው ለሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲያመቻቸው በበጋው የእረፍት ጊዜ ለሚያከናውኑት የአስተንትኖ የጸሎት በጠቅላላ ለመንፍሳዊው ተግባር ብሎም የሥነ ባህል እና ለሊቅነታዊ ሥራቸው ለማከናወን ካላቸው ፍላጎትም አንጻር በካስተል ጋንደልፎ ለማሳለፍ እንደመረጡ አባ ሎምባርዲ አብራርተዋል።

የቅዱስ አባታችን በካስተል ጋንደልፎ ቆይታቸው ሙሉ በሙሉ የእረፍት ወቅት ነው ብሎ በደፈናው ለመናገር አይቻልም። በጉጉት የሚጠበቀው ኢየሱስ ናዝራዊ በሚል ርእስ ሥር በተከታታይ የደረሱት መጽሓፋቸውን በመቀጠል “የጌታች ኢየሱስ የሕፃነትነት ሕይወት ታሪክ ላይ ያተኮረ ሦስተኛው የመጽሓፉ ክፍል የሚደርሱበት ወቅት መሆኑም አባ ሎምባርዲ ጠቅሰው፣ በዚህ የመጋው የዕረፍት ወቅት ቅዱስ አባታችን ምእመናን የሚሳተፉበት በየእሁዱ እኩለ ቀን የሚያቀርቡት አጭር አስተምህሮ የማቅረብ እና የሚያሳርጉት ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር እንደሚቀጥሉበትም በመግለጥ ነገር ግን የረቡዓዊ ይፋዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መርሃ ግብር እንዲሁም ይፋዊ ግኑኝነቶች በዚህ የበጋው የእረፍት ወቅት እንደማያከናወኑ አባ ሎምባርዲ አስታውቀዋል።

በመስከረም ወር የሚጀምሩት የተለመደው ሐዋርያዊ አገልግሎ እና የቅድስት መንበር መርሃ ግብሮች እጅግ ጥቅጥቅ ያለ እንደሚሆንም ሲገለጡ፣ በአንኮና የሚካሄደው የኢጣሊያ ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ምክንያት በተማይቱ የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ በዚያኑ ወር ማብቅያ በትውልድ አገራቸው ጀርመን የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት በመዘከር በጠቅላላ የካስተል ጋንዶልፎ ቆይታቸው ከሐምሌ ወር እስከ መስከረም ወር የሚዘልቅ መሆኑም አባ ሎምባርዲ ገልጠው የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ አጠናቀዋል።All the contents on this site are copyrighted ©.