2011-07-06 14:37:26

ደቡብ ሱዳን የሉአላዊነት ነጻነት ይፋዊ አዋጅ መቃረብ


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ውሳኔ ያረጋገጠው የሉአላዊነት ፍላጎት በማክበር ደቡብ ሱዳን 54ኛውይቱ የአፍሪቃ አገር በመሆን ይፍዊ ሉአላዊነቷ የሚታወጅበት ቀን ዋዜማ በክልሉ ውጥረት እና ግጭት እያየለ RealAudioMP3 መሆኑ ሱዳን በሰላም እና በጦርነት መካከል በሚል ርእስ ሥር ትላትና በሮማ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢጣሊያ በሱዳን የሰላም መረጋገጥ ዘመቻ ተሳታፊዎች የተለያዩ የሰላም አነቃቂ ማኅበራት እና የሰላም ጠረጴዛ የተሰየመው ማኅበር በጋራ ባዘጋጁት መድረክ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሱዳን ይፋዊ የሉአላዊነት አዋጅ ቀነ ቀጠሮው እየተቃረበ በመጣበት ቁጥር በክልሉ ውጥረት እና ግጭት እየከረረ መሆኑ ሲገለጥ፣ የኢጣሊያ በሱዳን የሰላም መረጋገጥ ዘመቻ ተሳታፊ ማኅበሮች ውስጥ የተዘረጉ እጆች የተሰኘው ሰላም እና በሰላም እጦት ለሚሰቃዩት ዜጎች የድጋፍ ዘመቻ የሚያነቃቃው ማኅበር አባል ጆቫኒ ሳርቶር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ መጪው የደብብ ሱዳን ረፓብሊካዊት አገር መረጋገጥ በርግጥ የክልሉ ሕዝብ ነጻው ፍላጎት የጠራው ውሳኔ ቢሆንም፣ በሰሜን ሱዳን እና በደብብ ሱዳን ለተሟላ ሰላም መረጋገጥ ፈታኝ የሆኑት ችግሮች ሊያጋጥም እንደሚችል ነው ሆኖም ግን ይህ ሊመጣ ይችላል የሚባለው ችግር የደቡብ ሱዳን ሉአላዊነት ለማግለል ምክንያት አድርጎ ማቅረብ አይገባም ካሉ በኋላ፣ አንዳንድ በሁለቱ ማለትም በሰሜን ሱዳን እና በደቡብ ሱዳን አወዛጋቢ ሊሆኑ የሚችሉ ከተሞች አሉ። እነዚህ ከተሞች ገና ከወዲሁ ውጥረት እና ግጭት እየታየባቸው ነው። ሁለቱም ሱዳኖች ድንበራቸውን ለመለየት በሚል ውሳኔ የይገባኛል ጥያቄው ማእከል ያደረገ ግጭት ተቀስቅሰዋል፣ ይህ ችግር ሁለቱ አገሮች በውይይት ሊፈቱት ይገባቸዋል። ሆኖም ግን እነዚህ በይገባኛል ጥያቄ ዙሪያ ለውጥረት ምክንያት ሆነው ያሉት ከተሞች እና ክልሎች በተፈጥሮ የማእድን ሃብት የታደሉ በመሆናቸውም ምክንይት ውዝግቡ በስተጀርባ ያነገበው ኅቡዕ ዓላማ ለመለየት አያዳግትም። ስለዚህ የዓለም አቀፍ ማኅበረስብ ሰሜን ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በመገናኘት ችግሩን ለመፍታት የክብ ጠረጴዛ ውይይት ማፋጠን ይገባዋል።

ልኡላዊነቷ በምታውጀው ደቡብ ሱዳን የሚቀረበው ሕገ መንግሥት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የሚያከብር መሆን አለበት። ሰሜን ሱዳን በክልሉ የሚገኙት በመንግሥት መሥሪያ ቤት ተቀጥረው የሚሠሩት የሰሜን ሱዳን ዜጎች እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ከሥራ ለማሰናበት አለ የሚባለው እቅድ በዚህ ክልል ለሚኖረው በጠቅላላ የደብብ ሱዳን ዜጋ የሚያጋጥመው አቢይ ችግር ከወዲሁ ይጠቁማል። ስለዚህ ይህ ጉዳይ የዜግነት መብት የሚመለከት ጥያቄ መሆኑ ገልጠው። በደቡብ ሱዳን መሠረታዊው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የሚያከብር ሕገ መንግሥት ማረጋገጥ ለክልሉ መረጋጋት ወሳኝ ይሆናል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.