2011-07-06 14:35:29

ምሥጢራዊ የቫቲካን ቤተ መዝገብ ወገግታ - “Lux in Arcana”


እ.ኤ.አ. በየካቲት ወር 2012 ዓ.ም. የቫቲካን ምሥጢራዊ ቤተ መዝገብ ለመጀመኢያ ጊዜ ከቫቲካን ከተማ ውጭ ሮማ በሚገኘው ካፒቶሊና ቤተ መዘክር ሉክስ ኢን አርካና-ምሥጢራዊ የቫቲካን ቤተ መዝገብ መከፈት በሚል ርእስ ሥር ለትርኢት እንደሚቀርብ ትላትና እኩለ ቀን በቫቲካን የዜና እና ማኅተም ጉዳይ ሕንጻ በሚገኘው በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የጉባኤ አዳራሽ የቅድስት RealAudioMP3 መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ፣ የቅድስት ሮማዊት ቤተ ክርስትያን ቤተ መዝገብ እና ቤተ መጻሕፍት ሓላፊ ብፁዕ ካርዲናል ራፋኤለ ፋሪና፣ የቫቲካን ምሥጢራዊ ቤተ መዝገብ ኅየንተ ብፁዕ አቡነ ሰርጆ ፓጋኖ፣ የሮማ ከንቲባ ጃኒ አለማኖ የሮማ ከተማ ነዋሪዎች ምክር ቤት የባህል ፖለቲካ እና የከተማይቱ የታሪክ እና የባህል ማእከላዊ ቦታዎች ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት ተጠሪ ዶክተር ዲኖ ጋስፓሪ እና የሮማ ከተማ ነዋሪዎች ማኅበር የባህል እና የቅርስ ሃብት ጉዳይ ተጠሪ ዶክተር ኡምበርቶ ብራኮሊ በጋራ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲና ታርቺዚዮ በርቶነ ይኽ የቫቲካን ምሥጢራዊ ቤተ መዝገብ ለሁሉም ክፍት ለማድረግ በሚል እቅድ መሠረት ቅድስት መንበር ውሳኔ በማስመልከት በሰጡት መግለጫ፣ የቫቲካን ምሥጢራዊ ቤተ መዝገብ ከለዮናዊት ከተማ ማለትም ከቫቲካን ውጭ የሮማ ከንቲባ የካምፒዶሊዮ ሕንጻ ለሰባት ወር ተዛውሮ ለሁሉም ክፍት እንዲሆን የሐዋርያዊ መንበር ውሳኔ በሮማ ከተማ እና በመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ መካከል ያለው የተዋጣለት ግኑኝነት የሚያመለክት ነው ካሉ በኋላ፣ ስለዚህ ይህ ትርኢት ለሥነ ምርምር እና ለሥነ ባህል አቢይ ጥቅም ያለው እንዲሁም ስለ ክርስትናው ባህል ጉዳይ ብዙ የሚተርክ በመሆኑም ከዚህ አኳያ ያለው ዘረፈ ብዙ ጥቅም ለመገመቱ አያዳግትም ብለዋል።

በመቀጠልም የቅድስት ሮማዊት ቤተ ክርስትያን ቤተ መዝገብ እና ቤተ መጻሕፍት ሓላፊ ብፁዕ ካርዲናል ራፋኤለ ፋሪና በሰጡት መግለጫ፣ ቤተ መዝገቡ ከቫቲካን ውጭ ለትርኢት እንዲቀርብ የተወጠነው እቅድ አለ ምንም ፍራት እና ሥጋት በተለይ ደግሞ የዚህ የቫቲካን ምሥጢራዊ ቤተ መዝገብ የተቋቋመበት 400ኛው ዓመት ምክንያት እና ቤተ ክርስትያን ለባህል ጉዳይ የምትሰጠው አቢይ ትኵረት የሚመሰክር በሥነ ባህል ዘርፍ ያላት ሃብት እና የምትሰጠው የላቀው አገልግሎት የሚያጎላ የባህል ታሪካዊ ሂደት እና ለውጥም ጭምር የሚያወሳ እቅድ ነው ሲሉ፣ የቫቲካን ምሥጢራዊ ቤተ መዝገብ ኅየንተ ብፁዕ አቡነ ሰርጆ ፓጋኖ በቫቲካን ምሥጢራዊ ቤተ መዝገብ ከሚገኙት በሚሊዮን የሚቆጠሩት መዝገቦች እና ሰነዶች ውስጥ በዚህ ትርኢት ለማቅረብ የማይቻል ቢሆንም፣ ከመቶ በላይ የሚገመቱ ከሰነዶቹ እና መዝገቦች መመረጣቸውና ከእነዚህ ከተመረጡት መዝገቦች እና ሰነዶች ውስጥ የር.ሊ.ጳ. ጎርጎሪዮስ ሰባተኛ እርሱም በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣን አመልካች ውሳኔ እ.ኤ.አ. የ1600 ዓ.ም. የቅድስት መንበር ሕገ ቀኖና ጋሊለዮ ጋሊለይ የተወገዘበትና የችሎቱ ሂደት ብሎም ስለ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ላይ ያተኵሩ ሰነዶች ያጠቃለለ መሆኑ አብራርተዋል።

በርግጥ ይህ ትርኢት ልዩ እና የላቀ ሁነት መሆኑ የሮማ ከተማ ከንቲባ አለማኖ በበኵላቸው በሰጡት መግለጫ በመግለጥ፣ ለባህል ለታሪክ ሊቃውን በጠቅላላ በሥነ ምርምር ዘርፍ ለተሰማሩት ሊቃውንት እና አጥኚዎች መስህቦ ብቻ ሳይሆን፣ ለማወቅ ለሚሻ ሁሉ ማራኪ እንደሚሆን አያጠራጥርም ካሉ በኋላ፣ የሰብአዊ ታሪክ ለማወቅ እና ለመተረክ የሚያግዝ አቢይ ትርጉም እና የላቀ ክብር ያለው እቀድ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ፓጋኖ በጣም ሩቅ ባልሆነ የዓመታት ገደብ ውስጥ እርሱም በሶሥት ግፋ ቢል ከአራት ዓመት በኋላ ስለ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጉዳይ የሚያወሱ ጠቅላላ ሰነዶች ግልጽ ሆነው ለሁሉም ክፍት ለማድረግ እቅድ እንዳለ ገልጠው፣ ውሳኔው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይሆናል ካሉ በኋላ፣ አክለውም በቫቲካን ምሥጢራዊ ቤተ መዝገብ የታቀቡት የምሥክርነት ታሪካዊ ሰነዶችን ዋቢ ያደረገ አንደኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ወቅት በቱርክ በአርመናውያን ላይ የተፈጸመው እልቂት የሚያወሳ የታሪክ መጽሓፍ ባጭር ጊዜ ውስጥ ለንባብ እንደሚቀርብ ከገለጡ በኋላ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መጠናቀቁ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.