2011-07-05 13:51:19

የእምነት ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ሸፍለር አዲስ ብፁዕ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን


እ.ኤ.አ. በ1942 ዓ. እስከ 1952 ዓ.ም. በሮማኒያ ሳቱ ማሬ ሊቀ ጳጳስ በመሆን ያገለገሉት የእግዚአብሔር አገልጋይ ብፁዕ አቡነ ዣኖስ ሸፍለር ትላትና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት እና ቅዱስነታቸው በወከሉት የቅዱሳን ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ በመሩት በሃንጋሪ ኤስተርጎም ቡዳፐስት ሊቀ ጳጳስ የሃንጋሪ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት RealAudioMP3 ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኤርዶ በሮማኒያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል በአገሪቱ የካቶሊክ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት በኅብረት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ቅዱስት ኩላዊት ቤተ ክርስትያን ብፅዕና እንዳወጀችላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ አቡነ ዣኖስ ሸፍለር ገና በልጅነታቸው ንቁ፣ ብሩህ ልባም ቁጡብ እና ጥንቁቅ እንደነበሩ በተወለዱበት ክልል የሚነገርላቸው፣ ገና የመንበረ ጥበብ ተማሪ እያሉ ሊቅነት በተማሪዎች እና በመንበረ ጥበብ አስተማሪዎች ሊቅ የሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸው ሆነው የክህነት ማዕርግ ተቀብለውም ልቅነታቸው እና በሳልነታቸውንም ጭምር በትምህርተ ክርስቶስ አገልግሎት ትጉህ አቢይ የቃለ እግዚአብሔር መስካሪ እና አስተማሪ በመሆን በክርስትናው እምነት ሕጽነት በማገልገል ደከምኝን የማያውቁ የእምነት አብነት እንደነበሩም ብፁዕ ካርዲናል አማቶ ባሰሙት ስብከት ገልጠው፣ እ.ኤ.አ. በ 1947 ዓ.ም. በሮማኒያ የኮሙኒዝም ሥርዓት ተከታይ መንግሥት አማካኝነት በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ላይ የደረሰው ስደት እና መከራ ካቶሊክ ምእመናን በአገሪቱ መንግሥት እወቅና ወደ ነበራት ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን እንዲታከሉ ብፁዕ አቡነ ዣኖስ ሸፍለር ወደ ኦርቶዶክስ ቤተ ርክስታይን ገብተው ፓትሪያርክ እንዲሆኑ የሚፈቅድ ሰነድ ሪማቸውን በማኖር እንዲቀበሉት ባስገዳጅ ቢጠየቁም በሮማኒያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለማጥፋት እና ከቅድስት መንበር የነበረው ግኑኝነት በማቋረጥ ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር የነበረው ውኅደት ለማሰናከል ለወጠነው እቅድ እምቢ ያሉ፣ በዚህ ውሳኔያቸው መሠረት ከብዙ ሌሎች የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ውሉደ ክህነት አባላት እና እሳቸውም ጋር በጁላቫ ውህኒ ቤት በእስር እና በጉልበት ሥራ ማቀው የደም ሰማዕትነት የተቀበሉ መሆናቸው ብፁዕ ካርዲናል አማቶ አስታውሰው፣ የተቀበሉት ሥቃይ ገና ከማግስቱ አንደ ሐዋርያዊ አግልግሎት እና የትምህርት ክርስቶስ ሐዋርያዊ አግልግሎት እና ጸሎት መሆኑ በእምነታቸው የመሰከሩት መሆናቸው የእኚህ አዲስ ብፁዕ ሕይወት ታሪክ ጠቀስ ብፁዕ ካርዲናል አማቶ በማብራራት፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድረ በዳ በክፋት መንፈስ መፈተኑ እና የዚህ ዓይነት ፈተና በቤተ ክርስትያን ልጆች ላይ የሚደጋገም መሆኑ ገልጠው ልክ እንደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለክፋት መንፈስ ሥለቶች እጅ ሳይሰጥ ለእግዚአብሔር አብ ያሳየው እና የኖረው የተሰዋው ፍቅር አብነት በመከተል ተሳታፊ ሆነው በመገኘታቸውም እነሆ ቅድስት ቤተ ክርስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ውሳኔ መሠረት በይፋ ብፅዕና እንዳወጀችላቸው በመግለጥ፣ የሮማኒያ ሕዝብ እና ቤተ ክርስትያን ለእምነት ሰማዕት አቡነ ብፁዕ ዣኖስ ሸፍለር ጥበቃ ጸልየው ያሰሙት ስብከት እንዳጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.