2011-07-05 13:55:16

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ አገልጋዮች ሳይሆን ወዳጆቼ ናችሁ


በሳምት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ እ.ኤ.አ. ሰነ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በዓመታዊ በዓለ ቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ጋር ተያይዞ በመላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ታስቦ የዋለው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. 60ኛው ዓመት ክህነት ላይ በማተኮር፣ ታማንኝነት አለ ትዕቢተኛ RealAudioMP3 የድል አድራጊነት መንፈስ በሚል ርእስ ሥር በመቀጠል፣ ቅዱስ አባታችን 60ኛው የክሀንት ዓመት ምክንያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጆቼ እንጂ አገልጋዮች አይደላችሁም በማለት ለደቀ መዛሙርቱ በጽርሃ ጽዮን የገለጠው የቅርበት የውህደት እና የአንድነት መንፈስ ላይ ያተኮረ ባሰሙት ስብከት፣ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚጸናው የግል ወዳጅነት ግኑኝነት እና ጓደኝነት የሁሉም ጥሪ መሠረት መሆኑ በማብራራት፣ ክህነት በግል የሚሰጥ የጥሪ መልስ ነው። የተጠራው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለውጥ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል እና ቅዱሳት ምሥጢራትን በመኖር የሚደግም ማለትም ቅሳዊ ድግምግሞሽ የሚኖርበት ሕይወት ማለት ሳይሆን፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅላዌ የሚያረጋገጥ ቃሉ እና ቅዱሳት ምሥጢራት ቀጣይነት ባለው የኅዳሴ መንፈስ የሚደግም በቅዱሳት ምሥጢራት በተለይ ደግሞ የምኅረት ምሥጢር እና ቅዱስ ቁርባን ሲሠራ ገዛ እራሱ እንደ ክርስቶስ የሚኖርበት ሕይወት መሆን ማብራራታቸው አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በማስታወስ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የጥሪ ታሪክ ትእግሥት የተሞላበት በተለያዩ የቤተ ክርስትያን ተልእኮዎች የተኖረ እና በመጨረሻውም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ተመርጠው በሚኖሩት የታማኝነት እና የእምነት መንገድ የተከተለ እንጂ በሚታበይ የድል አድራጊነት መንፈስ የሚኖር እልዳልሆነ የሚያረጋግጥ ነው። የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ የክሀንት ጥሪ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የቅርብ ጓደኛ መሆን በተለይ ደግሞ ከእርሱ ጋር በሚጸናው ኅያውነት እና ፍሬያማነቱ ከሚያረጋገጠው ቀጣይነት ያለው ግኑኝነት የመሰከረ ሐዋርያዊ አገልግሎ የሚኖር መሆኑ በማብራራት ርእሰ አንቀጹን አጠቃለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.