2011-07-04 17:02:53

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (03.07.2011)


ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ ዛሬ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥሩ አድርገን የምናቃቸው ሆኖም ግን ዘወትር ልባችንን የሚያራሩ ቃላት በዕለቱ ወንጌል እንደገና ይነግረናል፣ ኢየሱስ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና፣” (ማቴ፣11፣28-30) ይላል። እንዲሁም “ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር፣ ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።” (ማቴ፣9፣35-36) ይላል። ኢየሱስ ያኔ ያሳየው ርኅራኄ አሁን ባለነው ዓለማችንም ሳይቀር እስከ ትውልዳችን ይዘረጋል። ዛሬም ቢሆን ኢየሱስ በሕይወት ጭግር ተጨቁነው በሚገኙ እንዲሁም ኑሮ የመረራቸውንና የሕይወት ትርጉምና ስሜት አጥተው በሚጭነቁ ወገኖች በርኅራኄ እየተመለከተ ነው። በድሆች አገሮች ብዙ የተራቈቱና የተቸገሩ እንደሚገኙት ሁሉ በበለጸጉና በሃብታም ባይ አገሮች መሠረታውያን ነገሮች በማጣት የሚሰቃዩና በአእምሮ ጭንቀት እየተቸገሩ ናቸው፣ ከሁሉም በላይ ግን በጦርነት ድህነትና ሰው ሰራሽ ጭቆና ተገደው ሕይወታቸው ለአደጋ በማጋለጥ በየቦታው ስለሚገኙ ስደተኞችና መጠለያ አልባ ድሆንችን ያሰብን እንደሆነ ኢየሱስ በርኅራኄ እንደሚመለከታቸው ለእያንዳንዱ በሰማይ ያለው እግዚአብሔር ልጅ “እናንተ ሁላችሁ ወደኔ ኑ” በማለት ደጋግሞ እየጠራ ነው፣
ኢየሱስ ለሁላቸው ዕረፍት እንደሚሰጥ ቃል ይገባል፣ ከዚህ ጋር ደግሞ መፈጸም ያለበት አንድ ውል ያያይዛል፣ “ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝ” ይለናል። ይህ ከመክበድ የሚቀለው ጫና ከመሆን ነፃነትና ዕረፍት የሚሰጥ ምን ዓይነት ቀንበር ነው፤ ዮሐንስ በወንጌል 13፣34 እና 15፣12 እንደሚያመልክተን የክርሶስ ቀንበር የፍቅር ሕግ ነው፣ ይህም ለሐዋርያቱ የተወላቸ ትእዛዝ ነው፣ ይለናል፣ ረሃብና ኢፍትሐውነት ከመሰሉ የሰው ልጆች ቊሳዊ ቊስሎች እና እውነተኛ ካልሆነ መልካም ኑሮ የመነጩ ሥነ አእምሮአዊና ሞራላዊ ቁስሎች የሚፈውስ በወንድማማዊ ፍቅር የተመሠረተ ከእግዚአብሔር ፍቅር የሚመነጭ የፍቅር ሕግ ነው። ስለዚህ የእብሪት ጐዳናንና የበላይ ሥልጣን ለመቀዳጀት የምንጠቀመው ዓመጽን እንዲሁም ድልን ለመቀዳጀት የተከፈለው ይከፈል ለሚለው አቅዋም እርግፍ አድርጎ መተው ያስፈልጋል፣ እንዲሁም በዘመናችን በአከባቢ ላይ የምንፈጽመው ዓመጽ ማለት ተፈጥሮን አለአግባብ መበዝበዝን ትተን ትሕትና እንልበስ፣ ከሁሉም በላይ ግን ሰው የመሆንን ክብር የሚያሳዩ ግላዊና ኅብረተሰባዊ ግኑኝነቶቻችን በሚመለከት ዓመጽና ኃይል መጠቀምን ትተን ለሰው ልጅ የወደፊት ሕይወት ዋስትና የሚሰጥ ግኑኝነት እንፍጠር፣
የተከበራችሁ ጓደኞቼ፤ ትናንትና በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላዊ ሥርዓተ አምልኮ እግዚአብሔርን ጥቀ ቅዱስ ልብዋን ስለሰጠን አመሰገነው፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከኢየሱስ ትሕትናን እንድንማርና ቀላል ቀንበሩን ለመሸከም እንድንወስንና ውሳጣዊ ሰላምን በማጣጣም እኛም በበኩላችን በብርቱ ድካምና ትግል በሕይወት ጉዞ እየተቸገሩ ላሉት ሌሎች ወንድሞቻችንና እኅቶቻችንን ለማጽናናት እንድንችል ትርዳን፣
ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ፣
ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ ዛሬ በሳቱ ማረ ማኅበረ ክርስትያን በ1952 ዓም በሰማዕትነት የሞተውን የሃገረ ስብከቱ ጳጳስ የነበሩትን አቡነ ጃኖስ ሸፍለር ብፅዕና በማጅዋ የሮማንያ ቤተክርስትያን ደስታ ተካፋይ ነኝ፣ የብፁዕ አቡነ ጃኖስ ሸፍለር ምስክርነት በፍቅር ለሚያስታውስትና ለአዲሱ ትውልድ እምነታቸውን ያዳብር፣
All the contents on this site are copyrighted ©.