2011-07-01 14:32:53

ካሪታስ ኢን ቨሪታተ-ፍቅር በሐቅ አዋዲ መልእክት ለንባበ የበቃበት ሁለተኛው ዓመት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ሰኔ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. ካሪታስ ኢን ቨሪታተ-ፍቅር በሐቅ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ለንባብ የበቃበት ሁለተኛው ዓመት ምክንያት የኤኮኖሚ ሊቅ በጳጳሳዊ ላተራነንሰ RealAudioMP3 መንበረ ጥበብ የሥነ ኤኮኖሚ መምህር ካሪታስ ኢን ቨሪታተ-ፍቅር ብሐቅ አዋዲ መልእክቱን ማእከል ያደረገ በዚሁ ጳጳሳዊ መንበረ ጥበብ ሥር ለተቋቋመው ዓለም አቀፍየ ሥነ ኤኮኖሚ የምርምር ተቋም አስተዳዳሪ ፕሮፍፈሶር ፍላቪዮ ፍፈሊቸ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ካሪታስ ኢን ቨሪታተ ዓዋዲ መልእክት በርግጥ የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ የማኅበራዊ ትምህርት ሰነድ መሆኑ ገልጠው። የማህበራዊ እና የኤክኖሚ ነክ ጥያቄዎች ላይ በማተኮር በኤኮኖሚው በኤኮኖሚው ፖሊቲካ በኤኮኖሚው ስነ ምርምር በስታቲስቲክስ በተለያዩ የጥናት ዘርፎች ሥነ ምግባር የተከተለ የሰው ልጅ ማእከልነት ላይ እንዲተኮር የምታሳስብ እና ይኸንን መመሪያ ለማረጋገጥ ምን መደረግ እንዳለበት መንገዱንም ጭምር የሚያመለክት የሥልጣናዊ ትምህርት ሰነድ ነው ብለዋል።

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮነ 13ኛ ረሩም ኖቫሩም አዳዲስ ነገሮች የተሰየመው ዓዋዲ መልእክት፣ የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የረሩም ኖቫሩም ዓዋዲ መልእክት 90 ዓመት መታሰቢያ ምክንያት ላቦረም ኤክስርቸንስ- ሰብአዊ (ተግባር) ሥራ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት እና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሐቅ በተኘው ዓዋዲ መልእክት አማካኝነት የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ሥልጣናዊ ትምህርት በማጉላት ቀጣይነቱ እና ወቅታዊነቱ ያረጋገጡባት መሆንዋ በማብራራት። ጀርመናዊው የሥነ ኤኮኖሚ ሊቅ ዊልሄልም ሮፕከ ኤኮኖሚ፦ ከጥያቄ እና አቅርቦት ባሻገር በሚልር ርእስ ሥር ከዚህ ዓለም በሞት ከመለያታቸው በፊት በደረሱት መጽሐፍ እንደተመለከተው፣ የንግዱ የኤኮኖሚው ዓለም ከአቅርቦት እና ከጥያቄ ባሻገር ሲባል ባሻገር በሚለው ቃል የሰው ልጅ የሚያመለክት መሆኑ ገልጠው፣ ስለዚህ በኤኮኖሚው ዘርፍ የሰው ልጅ ማእከልነት ላይ እንዲተኮር ጥሪ የቀረበባት እና ይኽ ጥሪ ለማረጋገጥ የሚያግዘው መንገድ የምትጠቁም ነች። ብዙ የኤኮኖሚ ሊቃውን በሚያቀርቡት ጥናት በነዚህ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ያረጋገጡት እና የሚያመለክቱት እውነት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.