2011-07-01 14:30:44

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለበርሊን ሰበካ የሐዘን መግለጫ መልእክት አስተላለፉ


በ75 ዓመት ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት የበርሊን ልሂቅ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ጊዮርግ ስተርዚንስክይ ምክንያት ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ለበርሊን ሰበካ የሐዘን መግለጫ መልእክት አስተላለፉ።

ብፁዕ ካርዲናል ስተርዚንስክይ በከባድ ሕመም ለረዥም ዓመት ሲሰቃዩ RealAudioMP3 ቆይተው፣ ከትላንትና በስትያ ጧት ከዚህ ዓለም በሞት በመለያቸው ምክንያት ቅዱስ አባታችን ለበርሊን ሰበካ ረዳት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ሃይንሪኽ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልእክት ለሰበካው እና ለሰበካው ምእመናን በመንፈስ ቅርብ በመሆን የሐዘኑ ተካፍይ መሆናቸው በማረጋገጥ፣ ብፁዕ ካርዲናል ስተርዚንስክይ ጀርመን ለሁለት ተከፍላ በነበረችበት ዘመን የበርሊን ሊቀ ጳጳስ በመሆን ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ያላቸውን ኅብረት ሳይዘነጉ ዘወትር በመኖር ሕዝበ እግዚአብሔርን በመምራት ለጀርመን ውኅደት ሳይታክቱ አቢይ ሚና በመጫወት ውህደት የዕርቅ መንጭ መሆኑንም በቃል እና በሕይወት ያስተማሩ የቤተ ክርስትያን ልጅ መሆናቸው ዘክረው፣ ነፍሰ ኄር ካርዲናል ስተርዚንስክይ ለስደተኞች ለተፈናቃዮች ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መረጋገጥ እና በቤተ ክርስትያን የቤተሰብ መንፈስ እንዲሰማቸው በማድረግ የፈጸሙት ሐዋርያዊ አግለግሎት ቅዱስ አባታችን ጠቅሰው፣ ይህ በሳቸው የተኖረ የፍቅር አገልግሎት ኃያው እንዲሆን አደራ ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲፍናል ስተርዚንስክይ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ እ.ኤ.አ. በ 1946 ዓ.ም. ወደ ቱሪንገን ተሰደው በ1950 ዎች ዓ.ም. በበርሊን የኤርፉርት ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት የፍልስፍና እና የቲዮሎጊያ ትምህርታቸው አጠናቀው በ 1960 ዓ.ም. ማእርገ ክህነት ተቀበለው ከ 1966 እስከ 1981 ዓ.ም. በየና የቅዱስ ዮሓንስ መጥምቅ ቤተ ክርስትያን ቆመስ በመሆን እንዳገለገሉ ከዛም የኤርፉርት-ማይኒንገን ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ በመሆን በማገልገል ላይ እያሉ እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 1989 ዓ.ም. የበርሊን ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ ተሹመው እ.ኤ.አ. በ 1990 ዓ.ም. የጀርመን ውኅደት ከተረጋገጠ በኋላ እ.ኤ.አ. ሰኔ 28 ቀን 1991 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለካርዲናል ማእርግ መሾማቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ገልጦታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.