2011-06-29 15:38:38

አመታዊ በዓለ ቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ


ዛሬ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዓመታዊ በዓለ ቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ማክበርዋ ሲገለጥ፣ ከዚህ ዕለት ጋር ተያይዞም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ማዕርገ ክህነት የተቀበሉበት 60ኛው ዓመት በኵላዊት ቤተ ክርስትያብ ታስቦ ውሎአል።

ይኸንን ዓመታዊው በዓለ ቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. RealAudioMP3 የቅዱስ ጴጥሮስ የቃለ ተኣምኖ ምልክት አክሚም እርሱም ክጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለሚጸናው ምልክት ማቴ. 11,29-30 “ቀንበሬን በጫንቃችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ እኔ የዋህና ትሁት ነኝ፣ ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ…ቀንበሬ ልዝብ ነው ሸክሜም ቀላል ነው” የሚለውን ቃለ ወንጌል የሚገልጥ የፈቃዱ እና የፍላጎቱ ቀንበር የእውነት እና የፍቅር ፈቃድና ፍላጎት የሆነው የክርስቶስ ቀንበር የጓደኝነት ምልክት የማኖር ቅዱስ ሥነ ሥርዓትና ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ከፈጸሙላቸው 41 ከተለያዩ አገሮች በተወጣጡ ሊቃነ ጳጳሳት ታጅበው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፣ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ “አገልጋዮች አልላችሁም…ወዳጆቼ ብያችኋለሁ” (ዮሐ. 15.15)፣ ልክ የዛሬ 60 ዓመት በፊት በበዓለ ቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ከካርዲናል ፋውልሃበር እጅ የክህነት ማዕርግ የተቀበሉበት ዕለት ዘክረው፣ ያህች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለክህነት ለጠራቸው በትክልል አገልጋዮች አይደላችሁም…ወዳጆቼ ብያችኋለሁ የሚለው ቃል ያሰማበት መሆኑ በማብራራት፣ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለጠራቸው ለእያንዳንዳችን በምሥጢረ ጥምቀት፣ በሜሮን የእዚአብሔር ቤተሰብ አባላት ሲያደርገን የሚያሰማው የሚደግመው ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጽርሃ ጽዮን የደገመው ቃል ኅያው የሚያደርግ እርሱም ለክህነት ለጠራቸው ዳግም የሚያሰማው ቃል ጓደኛዮ በማለት በግል ለጠራው የሚያሰማው መሆኑ አብራርተዋል።

የእግዚአብሔር ፍቅር ታላቅነት እና ጥልቅ መሆኑ ለመኖር እና ለመግለጥ የሚያስችለው የውሰው ልጅ ስቃይ እና አዘቅት በጥልቀት ለማተኮር እና ለመቃኘት የዚሁ ሰብአዊ ሁኔታ ተሳታፊ ለመሆኑ የምኅረት ምሥጢር እና ቅዱስ ቁርባንን ለመሥራት የሚያበቃ ጸጋውን በመስጠት ቃሉን በትክክል እና በተገባው ሥርዓተ እና ደንብ ለማስተማር ወደ ሰዎች ሁሉ ለማድረስ ብቁ ብሎ በመተማመን በጠራቸው ላይ ያኖራል። እግዚአብሔር አምኖ ይኸንን ሁሉ በኋላፊነት ሲሰጥ ውስጣዊ ደስታ የሚሰጥ ቢሆንም፣ ምሥጢሩ አቢይ ጥልቅ በመሆኑም ምክንያት በገዛ እራስ ኃይል ያማይገባህ መሆንህና ውስንነትህ እና ደካማነትህን ስታውቅ የሚያርበደብድ ነው። ቢሆንም የእርሱ ማለቂያ የሌለው መኃሪነት እና መልካምነት ምክንያት የጥልቅ ደስታ ምክንያትም ነው ብለዋል።

በመቀጠልም የክህነት ህይወት ውስጣዊ መሆንን የሚገልጠው እርሱም አገልጋዮች አይደላችሁም…ወዳጆቼ ናችሁ የሚለው ቃል መሆኑ በመጥቀስ ጓደኛ የሚለው ቃል ላይ በማነጣጠር ሲያብራሩ፣ አንዳዊ ፍላጎት እና አንዳዊ አለ መፈለግ የሚያዋህድ አስተሳሰብን እና ፍላጎትን የሚያጣምር አንዳዊ የጋራ አስተሳስብ እና ፍላጎት ትሥሥር ማለት ነው ካሉ በኋላ፣ በጥልቅ ጓደኛ የሚለው ቃል የእኔ የሆኑትን አውቃችኋለሁ፣ እኔንም ያውቁኛል “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፣ እኔ በጎቼን ዐውቃለሁ በጎቼም እኔን ያውቁኛል” (ዮሐ. 10,14) እውነተኛ መተዋወቅን የሚያመልክት ነው ብለዋል። እንዲሁም (ዮሐ. 10,3) መልካም እረኛ ማለት ደግሞ “የራሱን በጎች በየስማቸው ይጥራቸዋል” ተብሎ በተጻፈው ቃል የሚገለጥ ነው። ስለዚህ ጓደኝነት ጥልቅ መተዋወቅ፣ በጠለቀ መተዋወቅ ማደግ፣ እያንዳንዳችን በቅዱሳት ምሥጢራት በቃሉ በጸሎት በቅዱሳን ውህደት በእያንዳንዱ ሰው ዘንድ እንዲሁም በምንገናኛቸው ዘንድም እርሱን በማወቅ ማደግ ማለት ነው።

እራስን ለእርሱ ፈቃድ ማስገዛት ማለት ጓደኛ መሆን ማለት ነው። ስለዚህ ፈቃዱ ባይተዋር የሚወር ውጫዊ ኃይል አይደለም። የእኔ ፈቃድ እና ፍላጎት እርሱን ለመከተል በሙላት እነሆኝ ወደ ሚለው ሙሉ እሺታ ማሳደግ ማለት ነው። ስለዚህ ፈቃድህን እና ፍላጎትህን ለእርሱ ፈቃድ ለማስገዛት ማስገደድ ማለት ሳይሆን ጓደኝነት የእኔ ፍላጎት እና ፈቃድ ወደ እርሱ ፍላጎት እና ፈቃድ እየቀረበ እንዲያድግ በማድረግ ብሎም ከእርሱ ፈቃድ እና ፍላጎት ጋር ማዋሃድ ማለት ነው። ከእርሱ ጋር በጥልቀት መገናኘት ማለት ከራስ እውነተኛ መሆን ጋር መገናኘት ነው በማለት ካስረዱ በኋላ የእርሱ ጓደኝነት እና እወተኛው ጓደኝነት ዮሐ. 15,3፣ 10,15 እንደሚገለጠው “ሰው ሕይወቱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለውም”፣ “እኔ እነርሱን የማውቃቸው አብ እኔን እንደሚያውቀኝና እኔም አብን እንደማውቀው ዐይነት ነው። እኔ ስለ በጎቼ ሕይወቴን አሳልፌ እሰጣለሁ” በሚለው እራስ አሳልፎ እስከ መስጠት የሚገፋፋ ነው ብለው፣ ጌታ ሆይ በበለጠ እንዳውቅህ እርዳኝ ከእንተ ፈቃድ እና ፍላጎት ጋር እወሃድም ዘንድ ደግፈኝ፣ ሕይወቴን ስለ ገዛ እራሴ ሳይሆን ከአንተ ጋር ስለ ሌሎች አኖራት ዘንድ አበርታኝ፣ ዕለት በዕለት የአንተ ጓደኛ በመሆን እያደግኩ እሄድም ዘንድ ደግፈኝ በማለት ጸልየዋል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጓደኝነት ሲናገር፣ ኃላፊነትንም ጭምር የሚያስከትል ወይንም የሚያሰማም መሆኑ ዮሐ. 15,16 “እኔ መረጥሁአችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፣ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምሁአችሁ…።” ያረጋግጥልናን። ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርት የተሰጠው የመጀመሪያው እና ቀዳሚው ኃላፊነት ማቴ. 28, 19 “ወደ ዓለም ሕዝብ ሁሉ ሂዱ በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው የእኔ ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው።” በሚለው ቃለ ተመልክቶ ይገኛል። ስለዚህ ጓደኝነት አጥር አገር ቋንቋ ባህል ሳያግደው ወደ ሁሉ የሚገፋፋ የእግዚአብሔር መንግሥት ለዓለም ክፍት የሚያደረግ መሆኑ የሚገለጥ ተልእኮ ነው። ይኽ ደግሞ እግዚአብሔር ከገዛ እራሱ በመውጣት ወደ ፍቅሩ እና ብርሃኑ ሊስብን እኛን ለመፈለግ ግርማውንና ክብሩን ተወ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእያንዳንዳችን የሚጠባበቀው ፍሬ፣ ልክ እንደ የአንድ የወይን ተክል እንደሚሰጠው ወይን ነው። ስለዚህ ከወይን ተክል የሚገኘው መልካሙ ወይን እንዲሁ የሚገኝ ሳይሆን የወይኑ ተክል ለማደግ እና የደረሰ እንዲሆን ቀን ሌሊት ዝናብ ብርሃን ይፈራረቅበታል። በብሉይ ኪዳን የመልካሙ ወይን ትርጉሙ ፍትህ ማለት መሆኑ ገልጠው፣ የእግዚአብሔር ፍትህ የእርሱ ትእዛዝ ከመከተል እና የእርሱ ፈቃድ እና ፍላጎት ከመፈጸም የሚረጋገጥ ነው። የእርሱ ትእዛዝ ደግሞ የፍቅር ትእዛዝ ወይንም ሕግ መሆኑ ቅዱስ አባታችን አስረድተው፣ ፍቅር ሲባል ገዛ እራስህን መተው ስለ ሌላው ገዛ እራስህን አሳልፈህ ለመስጠት መቆም መዘጋጀት በሕይወትህ ትእምርተ መስቀል ማስከተል ማለት ነው ካሉ በኋላ፣ ቅዱስ ጎርጎሪዮስ አቢይ ወደ እግዚአብሔር ያቀናችሁ ወይንም ያዘነበላቸሁ ከሆነ ለብቻችሁ መድረስ ከሚለው ፈተና ገዛ እራሳችሁን አቅቡ/ጠብቁ ያለውን ቃል ከጠቀሱ በኋላ በዚህ ዓቢይ ዓመታዊ በዓል ቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተሳታፊዎችን በተለይ ደግሞ የቍስጥንጥኒያ የውህድት ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ ብፁዓን ካርዲናሎች በቅብአተ ጵጵስና ቅርብ ለሆኑት ሊቃነ ጳጳሳት ልኡካነ መንግሥታትን የመንግሥት የበላይ አካላት፣ ካህናት ገዳማውያን ዓለማውያን ምእመማን ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር በበዓሉ ለመሳተፍ እና ለመካፈል ለተገኙት ሁሉም አመስግነዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.