2011-06-27 15:31:36

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ “ቅዱስ ቍርባን ዓለማዊነት የፍቅር ምልክት”


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና እና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል ከትላትና በስትያን ቅዱስ ቍርባን ለዓለማዊ ትሥሥር የፍቅር ምልክት ነው በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ሐሙስ እ.ኤ.አ. ሰኔ 23 ቀን 2011 ዓ.ም. RealAudioMP3 በቅዱስ ዮሐንስ ዘ ላተራኖ ካቴድራል ለበዓለ ቅዱስ ቍርባን ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ቅዱስ ቍርባን የቤተ ክርስትያን ኅልውና ማእከል ብቻ ሳይሆን የዓለም ማእከል መሆኑ በማብራራት፣ ነገሮችን የሚለውጥ አንቀሳቓሽ ኃይል፣ ተፈጥሮ፣ ሰብአዊ እና ታሪካዊ አድማስ ያለው የፍቅር ሥነ እንቅስቃሴ አመክንዮ ከእግዚአብሔር ሦስትነት ሕይወት የመነጨ በልበ ክርስቶስ አማካኝነት እኛ ጋር የሚደርስ መከፋፈልን በማግለል ወደ እዚአብሔር ሕይወት ቅርብ የሚያደርገን እኛነታችንን ከሚወረው ግለኝነት እና ከእኔ ባይነት ግፊት ነጻ የሚያወጣ እና ክፍት የሚያደርግ ኃይል ነው በማለት ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. እንዳብራሩ በርእሰ አንቀጹ በማበከር፣ በቅዱስ ቍርባን አማካኝነት በቤተ ክርስትያን እና በዓለም ፍቅርን የሚያስፋፋ የቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ኅልውና እና የማኅበረ ክርስትያን ማኅበራዊ አገልግሎት የሚያጎለብት እና የሚያጸና፣ ፍትህ መደጋገፍ መቀራረብ እና ወንድማማችነት የሰፈነበት ዓለም እውን የሚያደርግ የፍቅር ኃይል ነው። በዚህ ግለኝነት እና አንድ በአንዱ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ እና ልቆ ለመገኘት አሊያም ለመታየት በመራወጥ ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት እየተስፋፋ ያለው ዓለማዊ ትሥሥር በእውነተኛው ፍቅር እንዲለወጥ የሚያደርግ ኃይል መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ አብራርተዋል።

በዓለማችን የተሰበኩ እና ያከተመላቸው የሰውን ልጅ በምድራዊ ተስፋ አጥር ሥር የከለሉ የፖለቲካ ሥነ ሐሳቦች ያረማምዱት የማኅበራዊ ሥልት ከእውነተኛው መሠረት በመነጠል ሰላም ፍትህ ለማጽናት የሞከሩ የሰውን ልጅ መፍነሳዊው ባህርይ ግድ ያልሰጡ እንዳውም ይኸንን የላወቅ መሆናዊው ባህርዩ ለመሰረዝ የሞከሩ በጠቅላላ ውድቅ ሆነዋል። እውነተኛው የሰው ልጅ ተስፋ ከቅዱስ ቍርባን የሚመነጭ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በበዓለ ቅዱስ ቍርባን የሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ የሚያረጋግጠው ነው በማለት አባ ሎምባርዲ በማብራራት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.