2011-06-27 15:30:21

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በ26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን


ሁሌ በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የሚዘጋጀው በየዓመቱ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የውጣቶች ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ዘንድሮ እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 18 እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በማድሪድ በሚከበረው የወጣቶች በዓል ተገኝተው ምስክርነት መሪ ቃል፣ ሥልጣናዊ ትምህርት እንደሚያቀርቡ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ነሐሴ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ማድሪድ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ እንደደረሱ እዛው የእንኳን ደህና መጡ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ከሰዓት በኋላ ማድሪድ በሚገኘው ሲበለስ አደባባይ ለሁሉም ለ26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፊዎች ለሚቀርበው የእንኳን ደሃን መጣችሁ ሥነ ሥርዓት እና መንፈሳዊ መርሃ ግብር በመሳተፍ ዓርብ ነሐሴ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ከስፐይን ንጉሣዊ ቤተ ሰብ ጋር በዛርዙዌላ ሕንፃ ከተገናኙ በኋላ፣ ከወጣቶች ገዳማውያን እና ካህናት ጋር ቀጥለውም ከመላ የመናብርተ ጥበብ አስተማሪዎች ጋር በመገናኘት መሪ ቃል ከሰጡ በኋላ፣ በስፐይን በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ሕንፃ ከሰፐይን መራሔ መንግሥት እና ከአገሪቱ የመንግሥት እና የፖለቲካ አበይት አካላት ጋር እንደሚገናኙ ከወዲሁ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ከሰዓት በኋላ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፊ ውጣቶች የሚሳተፉበት የመስቀል መንገድ እንደሚመሩ መግለጫው አክሎ አስታውቀዋል።

ቅዳሜ ጧት ቅዱስ አባታችን አንዳንድ ወጣቶች ካናዘዙ በኋላ በቅድስት ማሪያም ካቴድራል የዘርአ ክህነት ተማሪዎች የሚሳተፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው እንዳበቁም፣ ከስፐይን ብፁዓን ጳጳሳት ጋር የምሳ ማዕድ ግብዣ ተቋደሰው የ26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ጋር በቅዱስ ኾሴ ተቋም የጉባኤ አድራሽ ይገናኛሉ። እህድ ጧት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 20 ቀን 2011 ዓ.ም የወጣቶች ቀን መዝጊያ የሚቀርበው ጸሎተ ዋዜማ መርተው በኩራቶ ቪየቶስ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ አደባባይ እ.ኤ.አ. 21 ቀን 2011 ዓ.ም. የወጣቶች ቀን የመዝጊያ መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው መሪ ቃል እና ሥልጣናዊት ትምህርት ሰጥተው፣ ቅዳሴው እንዳበቃም ከስፐይን ብፁዓን ካርዲናላት እና ብፁዓን ጳጳሳት ጋር የምዛ ግብዣ ተቋድሰው እንዳበቁ በወጣቶች ቀን በማስተናገድ አገልግሎት ከሰጡትንም የበጎ ፈቃድ አገልጋይቶች ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል እና የምስጋና ቃል አስተምተው በመሰናበት፣ ወደ ቫቲካን እንደሚመለሱ የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.