2011-06-27 15:29:13

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ክህነት የእግዚአብሔር ጸጋ/ስጦታ ለቤተ ክርስትያን አገልግሎት


እንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. እፊታችን ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ 60ኛ ዓመተ ክህነት ለማክበር በመዘጋጀት ላይ መሆንዋ ሲገለጥ፣ የቅዱስ አጐስጢኖስ አባቶች ማኅበርሰብ እና የቫቲካን ጳጳሳዊ የቅድስት ሃና ቁምስና ቆሞስ የቫቲካን ኅየንተ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ እሁድ ባቀረቡት መሥዋዕተ ቅዳሴ በማስታወስ RealAudioMP3 እግዚአብሔር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለቤተ ክርስትያኑ ስለ ሰጠ ምስጋና አቅርበዋል። ለዚህ ለኵላዊት ቤተ ክርስትያን አቢይ እለት የሆነው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. 60ኛው ዓመተ ክህነት በተለያዩ አገሮች በመንፈሳዊ እና በባህላዊ መርሃ ግብሮች ተሸኝቶ እየተዘከረ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ክህነት የተቀበሉበት 60ኛው ዓመት ምክንያት በማድረግ በኢጣሊያ የኪየቲ ቫስቶ ሊቀ ጳጳስ የቲዮሎጊያ ሊቅ ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ፎርተ የቅዱስነታቸው ማእርገ ክህነት እግዚአብሔር ለቤተ ክርስትያኑ ምንኛ እንደሚያስብ የሚያረጋገጥ ምስክርነት ነው።
ቀኑ በደረሰ እና በተገባው ዕለት እግዚአብሔር በተለያየ መልኩ ለሚቀርበው ጥያቄ እና ለሚከሰተው ሁኔታ መልስ ይሰጣል። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ገና የዘርአ ክህነት ተማሪ ብሎም ካህን ከዛም ብፁዕ ካርዲናል በመሆን እውቅታቸው ሊቅነታቸው በሙላት ለእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት እንዲያተኩር በማድረግ በዓለማችን ተከስቶ ለነበረው አምባገነናዊ ሥርዓተ መንግሥት፣ አመጽ እና ጦርነት በተፈራረቀባት ኤወሮጳ የእግዚአብሔርን ቃል በማገልገል የኅያው እግዚአብሔር መግለጫ በመሆን የቃሉ እውነተኛ ተስፋ በማበሠር የጀመሩበት ጥሪ አሁንም በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ተልእኮአቸው ጎልቶ እያንጸባረቀ ነው። እርሱም የእግዚአብሔር ቃለ ተስፋ ምስክርነት የጎላበት ሕይወት ነው።
ካህን በክርስቶስ እና በወንድሞች አባሪነት ታጅቦ ሲኖር ብቻ ነው ሌሎችን ለመደገፍ የሚበቃው የሌሎች መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ጥያቄ የገዛ እራሱ በማድረግ ለመሸከም ኃይል የሚያገኘው ከፍቅር የመነጩ ቃላቶች በመጠቀም፣ በአዲስ ቃል የሰው ልጅ ጥማት የሆነው ዘለዓለማዊ የእምነት እውነት ሲያበሥር ነው፣ በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያሉትን ሐሳብ በማስታወስ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.