2011-06-24 16:02:13

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ክህነት የእግዚአብሔር ጸጋ/ስጦታ ለቤተ ክርስትያን አገልግሎት


እንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. እፊታችን ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ 60ኛ ዓመተ ክህነት ለማክበር በመዘጋጀት ላይ መሆንዋ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን 150ኛው ዝክረ ዕረፍት ቅዱስ ጆቫኒ ማሪያ ቪያነይ ምክንያት እ.ኤ.አ. 2010 ዓ.ም. የክህነት ዓመት በማለት ሰይመው በዚያኑ ዓመት በተለያየ ወቅት ስለ ክህነት በማስመልከት ባቀረቡት RealAudioMP3 አስተምህሮ፣ ክህነት እግዚአብሔር የለገሰው በዋጋ የማይተመን የላቀ ክብር ያለው ጸጋ መሆኑ ሲያብራሩ፣ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በሳምንታዊው የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሲያቀርቡ፣ ካህን በዚህ መደናገረው እና በአቅጣጫ ቢስነት ተጠቅቶ በተዛባው ዓለም የእግዚብሔር ቃለ ብርሃን እርሱም ክርስቶስ ኅያው የሚያደርግ እንጂ የገዛ እራሱ ሥነ ሐሳብ ወይንም በገዛ እራሱ ፈጠራ ውጤት የሆነው ወይንም ደስ የሚለው የሌሎች ፍልስፍናዊ አመለካከት የሚሰብክ አይደለም። ካህን የሚወድሱት እና የሚከተሉት የሚያደንቁት ለማግኘት ለገዛ እራሱ ወይንም በገዛ እራሱ ሥም የሚናገር ከገዛ እራሱ በመንደርደር በገዛ እራሱ የፈጠራ ብቃት ታምኖ በዚህ የተለያዩ መደናገርን የሚፈጥሩ ፍልስፍናዎች በሚነዛበት ዓለም ተደራራቢ ችግር የሚቀሰቅስ ሳይሆን፣ በክርስቶስ ስም እውነት የሆነው ክርስቶስን ቃሉን እና የመኖር እንዲሁም በሕይወት የመጓዝ አርአያነቱን የሚያቀርብ የሚመሰክር ነው።

በበረሃ እንደሚጮህ ድምጽ፣ እርሱም ነቢይ ባህርይ ያለው፣ ተጽእኖ ያለው የብዙሃን የበለጠ በሌሎች ባህሎች አመለካከቶች ላይ ተጫኝ የሆነ ጠቅላይ እና ገዥ ከሆነው ባህል እና አመለካከት ጋር አድነት ያለው ሳይሆን፣ አንድ አዲስ የተግባራዊነት ብቃት ያለው እውነተኛው እና ጥልቅ የሰውን ልጅ የሚለውጥ የሚያድስ እርሱም ሕያው ብሎም ቅርብ የሆነው እግዚአብሔር በሕይወት እና ለዓለም ሕይወት ድንቅ ሥራዎችን የሚፈጽም እውነትን እና የመኖር አብነት የሚሰጠን ኅያው የሆነው ክርስቶስን የሚያቀርብ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ጠቅሶታል።

እ.ኤ.አ. መጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ካህን ለዓለም ስለ እግዚአብሔር የሚናገር እግዚአብሔርን ለዓለም የሚያቀርብ እንጂ መሠረት ለሌለው ጊዚያዊ ብናኝ ለሆነው ባህል የሚገዛ ሳይሆን የእግዚአብሔር ከመሆን እና በመሆን የሚሰጠው ነጻነት ገዛ እራስን ለመስጠት የሚያበቃውን እውነት የመኖር ብቃት የተቀበለ ነው ሲሉ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 13 ቀን 2006 ዓ.ም. በሕማማት ሳምንት የጸሎተ ሐሙስ የሊጡርጊያ ሥነ ሥርዓት መርተው ባሰሙት ስብከት፣ የሕማማት ሳምንት በተለይ ደግሞ ጸሎተ ሐሙስ ሊጡርጊያ የካህን ማንነት እና መለያ የጎላበት ካህን ማለት ምን ማለት መሆኑ የተገለጠበት አቢይ ዕለት ነው፣ እርሱም እውነተኛ የክርስቶስ ጓደኛ መሆን በጥልቀት በመኖር በሐሳብ በተግባር በፍቃድ በፍላጎት ጭምር ከእርሱ ጋር ውህደት ፈጥሮ በሥነ እውቀት ደረጃ ሳይሆን በግብር መኖር ፍላጎትን ስሜት እና ተግባርንም ጭምር ከክርስቶስ ጋር የሚያዋህድ ማለት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

በመጨረሻም እ.ኤ.አ የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም. በትክክል እና በአገባብ ከሌሎች ጋር ለመሆን ከክርስቶስ ጋር መሆን እጅግ ወሳኝ ነው። ካህን በክርስቶስ እና በወንድሞች አባሪነት ታጅቦ ሲኖር ብቻ ነው ሌሎችን ለመደገፍ የሚያበቃው የሌሎች መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ጥያቄ የገዛ እራሱ በማድረግ ለመሸከም ኃይል የሚያገኘው። ከፍቅር የመነጩ ቃላቶች በመጠቀም በአዲስ ቃል የሰው ልጅ ጥማት የሆነው ዘለዓለማዊ የእምነት እውነት የሚያበስር ነው። እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ጠቅሶታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.