2011-06-22 15:28:18

የአንግሊካን እና የሉተራን አቢያተ ክርስትያን የጋራ ውይይት


የዛሬ አርባ ዓመት በፊት የአንግሊካን እና ሉተራን አቢያተ ክርስትያን መካከል የተጀመረው የጋራው ግኑኝነት መሠረት በማደግ ለውህደት/ለአንድነት አልመው የሚያደረጉት የጋራው ውይይት መቀጠል እንዳለበት የአንግሊካን እና የሉተራን አቢያተ RealAudioMP3 ክርስትያን ዓለም አቀፍ የጋራው ድርገት ባለፉት ቀናት በእየሩሳሌም ባካሄደው ስብሰባ ፍጻሜ ማሳሰቡ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አስታወቀ።

የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት ዲያኮኒያ-አገልግሎት በሚለው መሠረታዊ ቃል ላይ ያተኮረ እንዲሆን በማሳሰብ አገልግሎት የአቢያተ ክርስትያን መለያ እና ማእከላዊ ባህርይ መሆኑ ጠቅሶ፣ እ.ኤ.አ. ከ 1986 ዓ.ም. ጀምሮ በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን መካከል ውህደት/አንድነት አልሞ የተካሄደው የጋራው ውይይት ላይ ያተኮሩ ሰነዶች የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የጋራው ዓለም አቀፍ ድርገት በማሳተም በዚሁ በታተመ ሰነድ ዘንድ እንተመለከተውም ዲያኮኒያ-አገልግሎት እና ኮይኖኒያ-ማኅበረሰብአዊነት በአንድ መሠረታዊ ዓላማ እና አንዳዊ ራዕይ ላይ የጸና ሐዋርያዊነት እርሱም በእግዚአብሔር ምስል ላይ የተቀረጹ ተያይዘው የሚሄዱ የተካፋይነት እና የተሳታፊነት መለያ መሆናቸው በማሳሰብ፣ በእየሩሳሌም የተካሄደው የጋራው ውይይት በዚህ መለያ ላይ ያልጸና ከሆነ የአቢያተ ክርስትያን መሠረታዊ ተልእኮ እና ምስክርነት የተሰናከለ እና ሌላውን ለማሳመን ብቃት የሌለው ሆኖ እንደሚቀር ማረጋገጡ ከአንግሊካን እና ሉተራን አቢያተ ክርስትያን ፈደራላዊ ዓለም አቀፍ ድርገት የተሰጠ መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.