2011-06-22 15:27:12

የመላ ኤውሮጳ አቢያተ ክርስትያን ጉባኤ፦ መለያየት የሚያስከትለው እንቅፋት በጋራ ለማስወገድ


የኤውሮጳ አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከሰኔ 7 ቀን እስከ ስኔ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. በስዊዘርላንድ በአቢያተ ክርስያን መካከል ያለው መለያየት የሚያስከትለው እንቅፋት በጋራ ለመቀረፍ በሚል ርእሥ ሥር የተመራ ስብሰባ ማካሄዱ ሲገለጥ RealAudioMP3 ፣ ይህ አቢያተ ክስትያን ለውኅደት አልመው የሚያደርጉት የጋራ ጉዞ ለማበረታታት የተካሄደው የጋራው ጉባኤ፣ አቢያተ ክርስትያን የአንድነት አድማስ በሆነው ላይ እንዲያስተነትኑ በማሳሰብ፣ ይኽ የላቀው ዓላማ በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መካከል ውህደት/አንድነት ታልሞ ለሚደረገው ወቅታዊው የጋራው ውይይት እጅግ የላቀ ኅያው ተጋርጦ መሆኑ እንዳሰመረበትም ለማወቅ ተችለዋል። የተካሄደው የጋራው ውይይት አቢያተ ክርስትያን የሚለያየው ገና መልስ ያላገኘው ክፍት ቲዮሎጊያዊ ጥያቄ ላይ ሳያተኩር በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ለአንድነት ታቅዶ የሚደረገው የጋራው ውይይት ሥርወ መሠረት ላይ በማነጣጠር፣ እያንዳንዱ አቢያተ ክርስትያን ባለው የግል መለያ በሆነው የክርስትናው ባህል ዘንድ ያለው የአንድነት ራዕይ ላይ ያነጣጠረ እንደነበርም ለማወቅ ተችለዋል።

በዚህ መሠረት በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መካከል የሚደረገው የጋራው ውይይት በተለይ ደግሞ በኤውሮጳ እያጋጠመው ያለ መሰናክል ለመሻገር የሚለውን ፍላጎት ያጎላ ሆኖ የጋራው ውይይት በአቢያተ ክርስትያን መካከል ያለው የጋራው አካፋይ የሆነው ክርስትያናዊ ባህል ላይ በማተኮር፣ ከዚህ አኳያ በመነሳት የጋራው ውይይት ለማነቃቃት ታቅዶ የተካሄደው መሆኑ ተገልጠዋል። በዚህ በተካሄደው የጋራው ውይይት እያንዳንዱ የዚህ የኤውሮጳ አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት እያንዳንዱ አባል ቤተ ክርስትያን ለአንድነት ታልሞ በሚያካሄደው ውይይት ያረጋገጣቸው አወንታዊ ውጤቶች ላይ ያተኮረ መግለጫ በማቅረብ፣ ማኅበረ ክስትያን በኤውሮጳ ተከስቶ በነበረው ልቅ ብሔራርተኝነት ወገናዊነት በጠቅላላ የውህደት ጸረ የሆኑት ምክንያቶች ለዘር ልዩነት እና ለአድልዎ መሠረት ባላቸው አመለካከቶች እየተጠቃች ለነበረችው ኤውሮጳ ከዚህ አቢይ ማኅበራዊ ሰብአዊ እና መንፈሳዊ ችግር ለመላቀቅ መጠራታቸው ተገንዝበው የሰጡት አስተዋጽኦ አቢያተ ክርስትያን እና ማኅበረ ክርስትያን ማህበራዊ ሰብአዊ ችግር መሠረት የሆኑት ምክንያቶች ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት የላቀ ሚና እንዲጫወቱ መጠራታቸው የሚያመለክት መሆኑ የተካሄደው ስብሰባ አስምሮበታል።

በመጨረሻም የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የሚያገናኛቸው ባህል እና የሚለያያቸው ቲዮግሎጊያዊ እና ሥነ ቤተ ክርስትያናዊ አመለካከቶች መሠረት በማድረግ በመወያየት ልዩነት ወደ አንድነት የሚያሸጋግር ሃብት መሆኑ ሲታመን ብቻ ነው ልዩነቶች በጋራ እንዴት ለመኖር እንደሚቻል በተለይ ደግሞ ለመወሃድ የሚያበቃ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሁነኛ የጋራ የውይይት ሥልት ለመቀበል የሚበቃው፣ ስለዚህ ስብሰባው የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ልዩነት የሚለው ቃል አንዳዊ የጋራ ትርጉም እንዲሰጠው እና አቢያተ ክርስያን ለውህደት የሚያደርጉት የጋራው ጉዞ ሁሉም አቢያተ ክርስትያን የሚያገናኝ ሆኖ ክርስትያን ምእመናን የእምነት መሠረታዊ እውነት ለመመስከር እና ለማበሠር መጠራታቸው የሚያስገነዝብ ሆኖ በሁሉም ዘንድ መቅረብ አለበት።

ሁለተኛው የዚህ በቦሰይ የተካሄደው የጋራው ውይይት እ.ኤ.አ. እስከ ስኔ 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጣይ ስብሰባውን በሃንጋሪ ርእሰ ከተማ ቡዳፐስት እ.ኤ.አ. ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2011 ዓ.ም እንደጀመረ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.