2011-06-22 15:32:45

ስሎቨኒያ፦ የሃይማኖት ነጻነት


በስሎቨኒያ አራቱ አበይት ሃይማኖቶች መንፈሳውያን መሪዎች በጋራ ከትላትና በስትያ የስሎቨኒያ 21ኛው የነፃነት ዓመት ምክንያት በማድረግ ስለ አገሪቱ የጸሎት እና የጾም ቀን አስበው በፈጸሙት መንፈሳዊ ሥን ሥርዓት ምክንያት፣ RealAudioMP3 በሉቢያና በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የአንዲት አገር ሕዝባዊ እና ብሔራዊ መሠረት የሆነው የሃይማኖት ነጻነት በማንም እና በምንም ምክንያት እንዳይጣስ በማሳሰብ የሰው ልጅ የቤተሰብ ክብር ለአንዲት አገር የተሟላ ብልጽግና ወሳኝ መሆኑ አስገንዝበዋል።

የጋራው ሰነድ የስሎቨኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የሉቢያና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶን ስትረስ የስሎቨኒያ የሉተራን ቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ መሪ ጳጳስ ገዛ ኤርኒሳ፣ የስሎቨኒያ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ሊቀ ካህናት ፐራን ቦስኮቪች የስሎቨኒያ እስልምን ሃይማኖት መሪ ሙፍቲ ነድዛድ ግራቡስ ፊርማ የሰፈረበት መሆኑ ሲር የዜና አገልግሎት ሲያመለክት፣ ይህ የጋራው ሰነድ የዚህ ዓይነት የጋራው መንፈሳዊ መርሃ ግብር እና ግኑኝነት ለአገሪቱ ኅብረተሰብ መንፈሳዊ ሰብአዊ እድገት እና ለተሟላ ብልጽግና አቢያ ሚና እንዳለው መንፈሳውያን መሪዎች እንዳሰመሩበት ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.