2011-06-22 15:31:35

መካከለኛው ምሥራቅ፦ ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ጉባኤ


ከትላትና በስትያ በግሪክ ቫሎስ ከተማ ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ጉባኤ የመካከለኛው ምስራቅ ማኅበረ ክርስትያን ርእሰ ጉዳይ በማድረግ ስብሰብ እያካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ በመካከለኛው ምስራቅ የማኅበረ ክርስትያን ሁኔታ RealAudioMP3 ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ገጽታውን በመዳሰስ የዚያ ክልል ማኅበረ ክርስትያን የተጋረጠበት እክል በመዘርዘር በተለይ ደግሞ እ.ኤ.አ. የካቲት ወር ላይ ይህ ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ጉባኤ የመካከለኛው ምስራቅ ማኅበረ ክርስትያን በክልሉ ከሚገኙት ከተለያዩ ሃይማኖት ሕዝቦች እና ባህሎች ጋር በሰላም የመኖር ጥሪው ለአደጋ ተጋልጦ የገዛ እራሱን ደህንነት እና ሰላም የሃይማኖት ነጻነት ጭምር ለማረጋገጥ መሰደድ ብቸኛ መፍትሔ አድርጎ ክልሉን ለቆ ለመውጣት ተገዶ የተያያዘው ምርጫ በክልሉ የማኅበረ ክርስትያን ብዛት እንዲጎድል እያደረገ መሆኑ ባወጣው መግለጫ በመጥቀስ ለክልሉ ክርስትያን ማኅበረሰብ ደህንነት እና ሰላም ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ዋስትና ለማረጋገጥ መንግሥታት ያላሰለሰ ጥረት ያደረጉ ዘንድ ጉባኤው ጥሪ እንዳቀረበ ሲር የዜና አግልግሎት አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በስብሰባው ካይሮስ ፓለስቲና በሚል ርእስ ሥር የሊባኖስ የማስታወቂያ ጉዳይ ሚኒ. ታረክ ሚተሪ ተመርቶ የክርስትያን ማኅበረሰብ ሁኔታ በአረብ አገሮች በሚል ርእስ ሥር ሰነድ ለማጠናቀር በተደረገው እቅድ ኣባ ጃማል ካደር የጥናት ጽሑፍ በማቅረብ መሳተፋቸውም ሲገለጥ፣ ይህ በመካሄድ ላይ ያለው ጉባኤ እየሩሳሌም በተመለከተ እንዲሁም በአረብ አገሮች በመስፋፋት ላይ ያለው ተዛማጅ ባህል እና የዴሞክራሲ ሥርዓት የማረጋገጡ ሂደት እና ሕዝባዊ ንቅናቄዎች ላይ በማነጣጠር ባቀረቡት የጥናት ጽሑፍ ማኅበረ ክርስትያን በሶሪያ በቱርክ በዮርዳኖስ በእስራኤል እና በፍልስጥኤም ሁለ መናዊ ተጨባጭ ሁኔታው ላይ ባነጣጠሩ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እያካሄድ መሆኑ ሲር የዜና አገልግልቶ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.