2011-06-20 15:41:33

የቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ሓዋርያዊ ጉብኝት በሳን ማሪኖ-ሞንተፈልትሮ


ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የዛሬ 30 ዓመት በፊት ሐዋርያዊ ጉብኝት በፈጸሙበት በሳን ማሪኖ - ሞንተፈልትሮ ሰበካዎች ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 እ.ኤ.አ. ትላትና እሁድ ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. “ጌታ ሆይ…እምነት ጨምርልን” (ሉቃስ 17፣ 5) በሚል ቃለ ወንጌል የተመራ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማከናወናቸው የቅድስት RealAudioMP3 መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስነታቸው በዚያች በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥንታዊት ረፓብሊክ አገር በሆነቸው ሳን ማሪኖ በሚገኘው የሰራቫለ የስፖርት አደባባይ እንደደረሱ በአገሪቱ በብፁዓን ጳጳሳት የውሉደ ክህነት አባላት ገዳማውያን እና የአገሪቱ የመንግሥት አበይት አካላት እና 22 ሺሕ በላይ በሚገመቱት ዓለማውያን ምእመናን አቀባበል ተደርጎላቸው፣ 25 ብፁዓን ካርዲናሎች 200 ካህናት ጋር በመሆን መሥዋዕት ቅዳሴ እንዳሳረጉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስ አባታችን ከቅድሳሴው ፍጻሜ በኋላ ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ደግመው እስተምህሮ ማቅረባቸውም ለማወቅ ሲቻል፣ በዚህ በአሁኑ ወቅት ግብረ ገብአዊ መመሪያ እና ሥነ ምግባርንም ጭምር የሚደልዝ የሰው ልጅ አእምሮ የሚያደበዝዝ መሠረታዊው ፍላጎት አለ ምንም ግብረ ገብ እና ሥነ ምግባር መመዘኛ ልቅ ደስታ መሻት እና መኖር በሚለው የልቅ ፍንጥዝያ ሥነ አመለካከት የሚያረማምዱ አመለካከቶች እና አብነት የሆኑት ሁሉ በማግለል ወደ እውነተኛው ሃብት ወደ ሆነው እምነት ይመለስ ዘንድ ባሰሙት ስብከት በማሳሰብ፣ ቀጥለውም ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባቀረቡት አስተምህሮ በዓለም የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ሰብአዊ ክብር እንዲርረጋገጥ ጥሪ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሳን ማሪኖ ጥንታዊት ሬፓብሊክ በክርስትናው እምነት ላይ የጸና ባህል ባላት አገር እንደደረሱ፣ በአገሪቱ የሚገኙት አድባራት እና አቢያተ ክርስትያን ደወል በመደወል ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሁሉም የአገሪቱ ዜጋ ይቀበል ዘንድ በመጋበዝ ሁሉም የአገሪቱ ዜጋ የዚህ ደስታ ተካፋይ መሆኑ እንዳረጋገጠም የሳን ማሪኖ - ሞንተፈልትሮ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ኔግሪ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሰራቫለ የስፖርት ሜዳ እንደደረሱ የእንኳን ደኅና መጡ መልእክት ሲያሰሙ በመመስከር፣ ስብከተ ወንጌል በሳን ማሪኖ 1700 ዓመታት ማስቆጠሩንም አስታውሰው ቀደምት የሳን ማሪኖ ሰባክያን ከክሮአዚያ የመጡ ቅዱሳት ማሪኖ እና ለዮነ መሆናቸው ዘክረው፣ የነዚህ ሁለት ቅዱሳት ስብከተ ወንጌል የአገሪቱ ባህል እና ኅብረተሰብ በክርስትናው መንፈስ ላይ የጸና እንዲሆን ማድረጉ ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በመግለጥ፣ የሳን ማሪኖ ሕዝብ ለእመ አምላክ ያለው አክብሮት በዚህች በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት በማያወላውል እምነት ላይ ታምኖ የእርሷ አብነት የሚከተል በእርሷ አማላጅነት ላይ የማይጠራጠር እምነት የሚኖር ነው ካሉ በኋላ፣ ሆኖም ግን በዓለማችን በተለያየ መልኩ በመዛመት ላይ ባለው እምነትን በሚቀናቀን ተዛማጅ ባህል በእምነት ላይ የተጠራጣሪነት መንፈስ በሚያዛምት ባህል እየተነካ ቢሆንም ቅሉ፣ በሳን ማሪኖ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በክርስትናው እምነት ላይ የተገነባ የአገሪቱ ባህል በተለያየ ዘርፍ በማንቃቃት ሕዝቡ ወደ እምነት ይመለስ ዘንድ እንደምታስተምር ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ቅዱስ አባታችን የሳን ማሪኖ ዜጎች እምነት እና መንፈሳዊነት እንዲያነቃቁ እና እንዲያርሙ ብሎም በአገሪቱ የምትገኘው ቤተ ክርስትያን እና ሕዝብን እንዲጸኑ ክርስትያናዊ መለያው እንዲጠበቅ ማኅበራዊው ሕይወት ላይ አወንታዊ ተጽእኖ የሚኖረው እውነተኛው አስፍሆተ ወንጌል ለማነቃቃት እዛው መገኘታቸው በቤተ ርክስትያኒቱ እና በመላ የሳን ማሪኖ ምእመናን እና ሕዝብ ስም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሊጎበኘን ስለ መጣ ዕድለኞች ነን በማለት ምስጋና አቅርበው፣ እምነታችንን እንዲያጸኑ እና ሐዋርያዊ ቡራኬ ይስጡን በማለት በውሉድ መንፈስ ላቀረቡት ልመና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመቀበል መሥዋዕተ ቅዳሴውን መርተው ባሰሙት ስብከት፣ ለአገሪቱ ሕዝብ እና ለቤተ ክርስትያን ቅርብ መሆናቸው በማረጋገጥ እና ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ምላሽ ከሰጡ በኋላ፣ ሁሉንም በእምነት በማጽናት መላ የአገሪቱ ሕዝብ እምነቱን አቅቦ ከክርስትናው እምነት ጋር የተስተካከለ ሕይወት እንዲመራ አሳስበው፣ በክርስትናው እምነት ላይ የተገነባው የአገሪቱ ባህል ክርስትያናዊ እና ሰብአዊ እሴቶችን በማንጸባረቅ በመኖር ኅያው የሆነው እምነቱን በሙላት ይኖር ዘንድ አደራ ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ርክስትያን ዕለቱ ቅድስት ሥላሴ የምታከብርበት ሰንበት መሆኑም ጠቅሰው፣ በዚህ የእምነታችን ጥልቅ ምሥጢር በሆነው ዘንድ ያለው ፍቅራዊ ግኑኝነት ሲያስተምሩ፣ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ ናቸው። ምክንያቱም እግዚአብሕር ፍቅር ነውና፣ አብ ለወልድ ሁሉን በሙላት ይሰጣል፣ ወልድ ሁሉንም ከአብ በምስጋና እና በእምነት ይቀበላል፣ መንፈስ ቅዱስ በአብ እና በወልድ መካከል ያለው የጋራው ፍቅር መግለጫ የመፋቀር ግኑኝነት ነው።

የዕለቱ የቅዳሴው መጽሓፍ ስለ ቅድስት ሥላሴ ሲናገር ይላሉ ቅዱስ አባታችን፣ ፍቅር እንጂ ስለ ቅድስት ሥላሴ እርሱም የሦስት አካል ምሥጢር አንድነት እና ኅብረት እንዲሁም ሦስትነት ላይ በማተኮር የሚተነትን ብቻ ሳይሆን፣ ይኸንን አንድነት እና ሥስትነትን የሚያጸና ፍቅር ላይ ያተኮረ መሆኑ ገልጠው፣ እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑ ቅዱስ አባታችን ሲያስረዱ፣ በኦሪት ዘ ጸዓት ላይ ያለው እርሱም በሲና ተራራ የተገባው ቃል ኪዳን እና ቆይቶም የሕዝቡ በእምነት መዛል እና በእምነት ላይ አለ ማመን ያሳየው ድካም፣ ሕዝቡ የሙሴ መዘግየት ባየ ጊዜ ወዲያውኑ አሮንን የሚታይ የሚጨበጥ ለሰው ልጅ ፍላጎት እና ፈቃድ የሚገዛ በፊታቸው የሚሄድ ጣዖት እንዲያቅርብላቸው በመጠየቅ፣ ከእግዚአብሔር መራቅ ሲጀምር እግዚአብሔር ሕዝቡ ከእውነተኛው አምላክ ፈቀቅ እንዳለ ባየ ጊዜ፣ ሙሴን ሂድ እና ያንን ሕዝብ እይ በማለት ከሲና ተራራ እንዲወርድ አዘዘው፣ ቀልጦ የተሰራው የጥጃ ምስል ባየ ጊዜ ልቡ በኃዘን ተሞልቶ ያንን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተራራው በታች ሰበረው። ይኸንን ስናነብ ሁሉ ያበቃለት ቢመስልም፣ ምንም’ኳ እንዲህ ያለ አቢይ ኃጢአት እርሱም እግዚአብሔርን መካድ ቢታይም፣ በሙሴ አማላጅነት እግዚአብሔር ልቡን ላደነደነለት ሕዝብ ምህረት በመስጠት ለሕዝቡ ኃጢኣት ስርየት በእግዚአብሔር ፊት ቀርቦ ለመነ፣ እግዚአብሔር ዳግም ቃል ኪዳኑን አጸና፣ ጽላቱንም ዳግም ሰጠው። እግዚአብሔር መልኩ ወይንም ገጹን እንዲያሳየው ሙሴ ላቀረበው ጸሎት እግዚአብሔር መልካም እና ደግ መሆኑ ገለጠለት። እግዚአብሔር ለቁጣ የዘገየ መሐሪ በፍቅር እና በእምነት የተሞላ መሆኑ ተመሰከረ። ይህ እግዚአብሔር የገለጠው የማንነት ርእሰ መለያ፣ ፍቅር በኃጢአት ላይ ድል የሚነሳ መሆኑ የሚያረጋግጥ የምኅረት አምላክ የሚያጎላ አምላክ መኃሪ መሆኑ ያረጋግጥልናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

የእኛ እግዚአብሔር ኃጢአተኛን የሚደመስስ የሚያጠፋ ሳይሆን በጥልቀት እና በሚያስደንቅ ሁኔታ ለኃጢአተኛው ዳግም የመለወጥ እና የምህረት እድል በመስጠት በኃጢአተኛው ፊት ጥልቅ ፍቅሩን የሚገልጥ አምላክ ነው።

የዕለቱ ወንጌል የእግዚአብሔር ምህረት ምን ያክል ትልቅ እና ጥልቅ መሆኑ፣ እግዚአብሔር አንድ ልጁን አሳልፎ እስከ መስጠት የሰውን ልጅ ምንኛ እንዳፍቀረ ወንጌላዊ ዮሐንስ የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር ማንነት ገልጦልናል፣ ስለዚህ በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት ይኖረዋል እንጂ አይጠፋም። እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፣ በዓለም ላይ ሊመፍረድ አይደለም” በማለት ያስተምረናል። በዓለማችን ክፋት ስግብግብነት ለእኔ ባይነት፣ መፍረድ በስፋት እንደሚታይ ቅዱስ አባታችን ገልጠው፣ እግዚአብሔር የሰው ልጅ ምንም’ኳ ኃጢአተኛ ቢሆንም፣ ፍቅሩን በመግለጥ የሚወደው አንዱ ልጁ የዚህ ፍቅር እውነተኛ መግለጫ በማድረግ የላቀው የዚህ ጥልቅ ፍቅር መግለጫ በሆነው በምሥጢረ መስቀል የሦስቱ መለኮታዊ አካላት ኅላዌ መረጋገጡ ሲያብራሩ፣ አንድ ልጁን የሚሠዋ እግዚአብሔር አብ፣ የአብን ፈቃድ በሙላት በመስቀል ተሰቅሎ በመሞት፣ መንፈስ ቅዱስ በዚህ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥቃይ አማካኝነት እኛን የዚህ የመለኮታዊ ሕይወት ተካፋዮች የሚያደርገን ነው ብለዋል።

የሳም ማሪኖ ሕዝብ ትልቅ ሃብት እምነት ነው። ይህ ደግሞ በእምነት ላይ የጸና የብቸኛው ሥልጣኔ መሠረት መሆኑ ገልጠው፣ ለእምነት ታማኝ መሆን ወሳኝ ነው፣ ሆኖም ግን ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚሄድ በሳን ማሪኖ የምተገኘው ካቶሊክ ቤተ ርክስትያን ካለ መታከት ለሮማ ጳጳስ ታማኝ በመሆን ለምትኖረው እምነት ጭምር ታማኝ መሆን እንደሚያስፈልግ ካሳሰቡ በኋላ፣ ለቤተ ርክስትያን ባህል እና ትውፊት ጭምር ታማኝ ሆኖ መገኘት ወሳኝ ነው ብለዋል። በዚህ የቤተ ክርስትያን ባህል የምታከብር እና የምትከተል የሳን ማሪኖ ቤተ ክርስትያን ለቅድስት ድንግል ማርያም ያላት አክብሮት የአገሪቱ ሕዝብ በተለይ ደግሞ ማኅበረ ክርስትያን ሳይዘነጋ በእምነት እንደኖረው ማሳሰባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በአሁኑ ወቅት ግብረ ገብአዊ መመሪያ እና ሥነ ምግባርን የሚደልዝ የሰው ልጅ አእምሮ የሚያደበዝዝ ለሰው ልጅ መሠረታዊው ፍላጎት አለ ምንም ግብረ ገብ እና ሥነ ምግባር መመዘኛ ልቅ ደስታ ብቻ ነው የሚለው ልቅ ፍንጥዝያ የሚያስፋፋው የሰው ልጅ እውነተኛው ኃብት እምነት ሳይሆን ግላዊ ማኅበራዊ ሥነ ምርምር የእደ ጥበብ ሂደት እና ማኅበራዊ ተግባሮች እውነተኛው ኃብት ናቸው ለሚለው ሥነ አመለካከት አብነት የሆኑትን በማግለል ሁሉ ወደ እውነተኛው ሃብት ወደ ሆነው እምነት ይመለስ ዘንድ በማሳሰብ፣ ምእመናን በዚህ በምንኖርበት ዘመን በቃል እና በተግባር የታነጸ እምነት በመኖር የምድር ጨው ሆነው እንዲገኙ አደራ ብለዋል።

በመጨረሻም ለሳን ማሪኖ ውሉደ ክህነት ገዳማውያን እና ካህናት ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ኅብረት ላላቸው ብፁዓን ጳጳሳት ታዛዦች በመሆን ለምእመናን በቃል እና በሕይወት ያንጹ ዘንድ አሳስበው እግዚአብሔር በሳን ማሪኖ ሰበካ የካህናት እና የገዳማውያን ጥሪ እንዲበዛ፣ ቤተ ሰብ የንቁ ክርስትያን መሠረት መሆኑም ጠቅሰው፣ ወጣቱ ትውልድ በእምነት በርትቶ እግዚአብሔር በሚመርጥለት መንገድ እምነቱን እንዲኖር፣ ዓለማዊው ምእመን የቤተ ክርስትያን ንቁ ተሳታፊ መሆኑ ተገንዝቦ፣ በሁሉም ሥፍራ እምነቱ እንዲመሰክር አደራ ብለው፣ ሳን ማሪኖ በቅዱሳት ጠባቂዎችዋ የሆኑት የቅዱስ ማሪኖ እና ሊዮነ ክርስትያናዊ አብነት በመከተል ለዚህ የክርስትናው ሃብት ታማኞች ሆነው በማቀብ ኅያው የሆነ እምነት እንዲኖርባት ጸልየው፣ የመንግሥት እና የፖለቲካ አካላት የሰው ልጅ ክብር በተለይ ደግሞ የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ሰብአዊ ክብር እንዲያረጋግጡ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.