2011-06-19 13:42:31

የር.ሊ.ጳ ሐዋርያዊ ጉብኝት በሳን ማሪኖ ሞንተፈልትሮ ሃገረ ስብከት


ቅዱስነታቸው የአንድ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ጥዋት በሮም ሰዓት አቆጣጠር ልክ 8 ሰዓት ከሐዋርያዊ መንበራቸው በሄሊኮፕተር ወደ ቻምፒኖ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ተጉዘዋል።። ከቻምፒኖ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፍያ እንደገና በሄሊኮፕተር 8:30 ተነሥተው ከአንድ ሰዓት በረራ በኋላ ሳን ማሪኖ ገብተዋል፣ በሳን ማሪኖ በሚገኘው የቶራቻ ሄሊኮፕተር ማረፍያ ላይ እንደደረሱ የሪፓብሊክዋ አስተዳዳሪዎች ማርያ ልዊዛ በርቲ እና ፊሊፖ ታማኚኒ እንዲሁም የሳን ማርቲኖ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ነግሪ ከሌሎች ባለሥልጣኖች ደማቅ አቀባበል አደረጉላቸው። በሄሊኮፕተር ማረፍያ አጠገብ በሚገኘው ሰራቫለ ስታድዩም ብፁዓን ጳጳሳት ባለሥልጣናት ካህናትና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምእመናን ይጠባበቅዋቸው ስለነበር በእግር ለጥቂት ከተጓዙ በኋላ በታላቅ ደስታና ጭብጨባ ተቀበልዋቸዋል። ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ነግሪ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ካደረጉ ብኋላ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል፣
ልክ እኩለ ቀን ላይ ደግሞ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ አቅርበው ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር አሳርገዋል፣
ቅዱስነታቸው ጉብኝታቸውን በመቀጠል በቫልድራጎነ በሚገኘው ቤተ ቅዱስ ዮሴፍ ከሃገረ ስብከቱ ጳጳሳትና የቤተ ክህነት አባላት ጋር ተገናንተው አብረው ምሳ በልተዋል፣
ጥቂት ዕረፍት ካደረጉ በኋላ ወደ ሪፓብሊክዋ ምክር ቤት በመሄድ ከአስተዳዳሪዎችና ከዲፕሎማሲ አባሎች ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል ሰጥተዋል፣
ከምሽቱ 06።30 ከቶራቻ ሄሊኮፕተር ማረፍያ በሄሊኮፕተር ወደ ፐናቢሊ ስታድዩም በመሄድ የሳን ማሪኖ ካተድራልን ይጎበኛሉ። ቅዱስነታቸው ካተድራሉን ተሳልመው የግል ጸሎት ካሳረጉ ብኋላ በቪቶርዮ ኤማንወል በጉጉት እየተጠባበቅዋቸው ካሉ የሳን ማሪኖ ሃገረ ስብከት ወጣቶች ጋር ሊገናኙ ነው።
በምሽቱ ስምንት ሰዓት ከፐናቢሊ ስታዮም በሄሊኮፕተር ተነሥተው ከአንድ ሰዓት በረራ በኋላ ቫቲካን ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሳን ማሪኖ ሪፓብሊክ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተቋቋመች በሪፓብሊክ የኢጣልያ ኣገር ውስጥ የምትገኝ ትንሽ አገር ናት፣ 61.5 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሆን ስባት ያላትና 30 ሺ የሚሆኑ ነዋሪዎች ያልዋት በኤሚልያ ሩማኛና ማርከ በሚባሉ የጣልያን ክፍለሃግሮች መሃከል ትገኛለች።
ሳን ማሪኖ ከቅድስት መንበር ጋር እአአ በ1926ዓም ዲፕሎማስያዊ ግኑኝነት ማድረግዋ የሚታወስ ሆኖ የሰበካዋ ጳጳሳት ከኢጣልያ ረኪበ ጳጳስት በአንድነት ይሠራል፣
ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እአአ በ1982 ዓም ሐዋርያዊ ጉብኝት አድርገው እንደነበሩ የሚታወስ ነው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.