2011-06-17 14:46:23

ጦርነት የሚፈራረቅባት ሱዳን


ደቡብ ሱዳን እና ሰሜን ሱዳን በሚያዋስነው የደቡብ ኮርዶፋን ርእሰ ከተማ ካዱሊ ክልል በሰሜን እና በደቡብ ሱዳን ወታደሮች መካከል በመካሄድ ላይ ያለ ግጭት የክልሉ ሕዝብ እያፈናቀለ ለተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያጋለጠ መሆኑ በክልሉ RealAudioMP3 አገልግሎት በመሰጠት ላይ የሚገኙት አንዲት የኮምቦኒ ደናግል ማኅበር አባል የሰጡት የዓይን ምስክርነት የጠቀሰ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በመካሂድ ላይ ያለው ግጭት ሳቢያ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ በጠቅላላ የክልሉ ሕዝብ ለመፈናቀል አደጋ እያጋለጠ ሲሆን፣ የሕክምና መስጫ ጣቢያዎች በመካሄድ ላይ ባለው ውጊያ የቆሰሉት ወታደሮች እና ሰላማዊ ሕዝብ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ተግባር ሳይገቱ የሰብአዊ እርዳታ እያቀረቡ መሆናቸውም ፊደስ የዜና አገልግሎት የኮምቢናውያን ደናግል ማኅበር አባል የዓይን ምስክርነት በመጠቅስ አክሎ በተለይ ደግሞ እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ያለው በጦር ሄሊኮፕተሮች ተሸኝቶ የሚፈጽመው ድብደባ የክልሉ ሕዝብ ለከፋ አደጋ እያጋለጠ መሆኑ፣ በክልሉ የሚገኙት ልኡካነ ወንጌል በመግለጥ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የት አለ በማለት ጥያቄ ለማቀረብ እንዳስገደዳቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ያለው ግጭት መፍትሔ እንዲያገኝ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል በማለትም ጥሪ ማቅረባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የግብረ ሰናይ ማኅበራትን የሚያቀፍ የእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን ተራድኦ ማኅበር መግለጫ እንደሚያመለክተውም ተከስቶ ባለው ግጭት ሳቢያ 60 ሺሕ ሕዝብ በማፈናቀል ለከፋ ሰብአዊ አደጋ እያጋለጠ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.