2011-06-17 14:43:01

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት አስከባሪ ድርጅት


ዋና መቀመጫው ጄኔቭ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ አስከባሪ ድርጅት የሠራተኛ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ በሚል ርእስ ተመርቶ ባካሄደው መቶኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ፣ በቤተ ሥራ የሚተዳደሩ ሠራተኞችን የሚያስተዳድር የእነዚህ ሠራተኞች ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ በተመለከተ የውሳኔ መመሪያ ማጽደቁ ተገለጠ። በዚህ በተካሄደው ስብሰባ RealAudioMP3 የተሳተፉት በድርጅቱ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅድስት መንበር እና የተለያዩ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ተሟጋች ብሔራዊ እና ዓለም አቀፍ ማኅበሮች፣ ዘወትር እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሥራ እና ሠራተኛ ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር እ.ኤ.አ ከ 1970 ዓመታት ወዲህ በቤት ሥራ የሚተዳደሩት ሠራተኞች መብት እና ፍቃድ ይቅር ስለ እነዚህ የሠረተኛው ማኅበረሰብ ክፍል የማይታዩ ተደርገው፣ ተቀጥረው ለሚሠሩበት ቤት ፈቃድ እና ውሳኔ ተትወው ወካይ የሠረተኛ ማኅበር የሌላቸው በብዛት ስደተኞች ከነዚህም ውስጥ አብላጫው ሴቶች የሚያጠቃልል ሥራ ሲሆን፣ የስደተኛው ለስደት የዳረገው ዘርፈ ብዙ ችግር ተገን በማድረግ ላሠሪው ፈቃድ እና ፍላጎት ተጋልጠው፣ አለ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ዕለታዊ ኑሮአቸው እንዲመሩ ሳይሆን እንዲገፉ ተገደዋል፣ ስለዚህ የነዚህ የሠራተኛው ኅብረሰብ ክፍል የሚያከናውኑት ሥራ በሕግ የተመራ በሠረተኛ የማስተዳዳሪያ ደንብ ሥር እውቅና አግኝቶ የመተዳደሪያ ደንብ ያለው እንዲሆን የተደረሰው ስምምነት ነው ካሉ በኋላ፣ ይህ የተደረሰው የውሳኔ ስምምነት ቅድስት መንበርን እጅግ እንዳረካት ገልጠው የሰጡት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.