2011-06-17 14:41:46

ቫቲካን፦ ዓለም አቀፍ የተኅዋስ ሥርወ ግንድ ማእከል ያደረገ ዓወደ ጥናት


እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 9 ቀን እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን የተኅዋስ ሥርወ ግንድ፦ ሥነ ምርምር፣ የሰው ልጅ የመጪው ሕይወት እና ባህል በሚል ርእስ ሥር የተመራ ዓወደ ጥናት እንደሚካሄድ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

መርሃ ግብሩ በማስደገፍ ትላትና ጧት በቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ሕንጻ በመገኘት RealAudioMP3 ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ፣ በዚህ ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ምክር ቤት የስነ ምርምር እና የእምነት ጉዳይ ተጠሪ ኣባ ቶማስዝ ርራፍንይ የዚህ ዓወደ ጥናት ተባባሪ አዘጋጅ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የተኅዋስ ሥርወ ግንድ ምርምር እና ጥናት በማፋጠን የተለያዩ በሽታዎች በተኅዋስ ፍወሳ እንዲወገድ ያለመ የሥነ ሕይወት መድኃኒት ድርጅት ተጠሪ የሥነ ሕክምና ሊቅ ሮቢን ስሚዝ በተገኙበት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት፣ ሊካሄድ የተወሰነው ዓውደ ጥናት ተቀዳሚ ዓላማው፣ በተኅዋስ ሥርወ ግንድ ላይ በማነጣጠረ የሚደረገው ሥነ ምርምር በማኅበራዊ ባህል ጉዳይ ላይ ያለው ተጽእኖ ጥልቅ መሆኑ በመለየት የሥነ ሕክምና ጥናት እና ምርምር በላቀ ሁኔታ የሚያበረታታ የጥናት ዘርፍ መሆኑ ለማበከር ብሎም የሥነ ምግባር ፍልስፍናዊ እና ቲዮሎጊያዊ ክትትል እንዲታከልበት የሚጠይቅ በመሆኑም የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ይኸንን ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባት በተኅዋስ ሥርወ ግንድ የሚደረገው ሥነ ምርምር ለሥነ ምርምር እና የሕክምና ሊቃውንት ብቻ መተው ሳይሆን በቀጥታ ኅልውናን የሚመለከት ጉዳይ በመሆኑ፣ የሚጨበጠው የሥነ ምርምር ውጤት ሁሉም ሊረዳው በሚችል ቋንቋ መግለጥ ተገቢ መሆኑ የሚያሳስብ ዓወደ ጥናት ነው በማለት ሲገልጡ፣ የሥነ ሕክምና ሊቅ ሮቢን ስሚዝ የተኅዋስ ሥርወ ግንድ ላይ ያተኮረው ምርምር የተለያዩ በሽታዎችን ለማጥፋት እና በሽታ የሚያስከትለው ሥቃይ ለማቅለል ብሎም ለመፈወስ ያለመ ነው። ስለዚህ ይህ የሥነ ምርምር ዘርፍ ሕይወት ለማዳን በሚል ተገቢ ዓላማ ሌላ ሕይወት በማጥፋት የሚረጋገጥ እንዳይሆን መጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ባህል የሕይወት ባህል የሚጻረር መሆን የለበትም የሚለው መሠረታዊ ሃሳብ እንዲከተል እና እንዲያከብር ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚሻ ዓውደ ጥናት ነው በማለት ሲያብራሩ፣ አክለውም የተለያዩ ገና መድኃኒት ያልተግኘላቸው በሽታዎች ፈውስ ለማግኘት ለሚደረገው የሥን ምርምር ጥረት ለመደገፍ እና ለማበረታታት እና ድረስ የተገኙት የሥነ ምርምር ውጤቶች ቀርቦ የሚያጤን ዓወደ ጥናት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.